ራህዋ አምሀ (በአ.. /// የህክምና ተማሪ-C2)

“ማህበረሰቡ መድሃኒቱን በጣም በሚፈልግበት ወቅት መድሀኒቱን ያለአግባብ የሚጠቀበት ጊዜ ይመጣል”

                                                                                            –ሰር. አሌክሳንደር ፍሌሚንግ

መግ

በ20ኛው ክፍለ ዘመን ላይ በህክምናው ዘርፍ ከተገኙት ትልልቅ ግኝቶች ውስጥ የፅረ-ተውሃስያን መድሃኒቶች ግኝት ለህክምናው ዘርፍ መጠነ ሰፊ አስተዎጾ በማበርከቱ ይታወቃል። ከዚህም ውስጥ የአሌክሳንደር ፍሌሚንግ በ1928 የነበረው የመጀመሪያው የአንቲባዮቲክ ግኝት(ፔንሲሊን)  በፈር-ቀዳጅነት ይጠቀሳል። በዚህ ምክንያት ለህክምና አና ለቀዶ ጥገና ዘርፎች ቀላል የማይባል አስተዋጾ በማበርከት ሚሊየኖችን ከበሽታ እና ከሞት መታደግ ተችሏል። ይሁን እንጂ ከ1940`ቹ በኋላ አለም አቀፋዊ በሆነ መልኩ ቀደም ብለው በሽታ አምጪ ተህወሲያንን በመግደል ወይም እንዳይራቡ በማድረግ የተለያዩ በሽታዎችን ሲያክሙ የነበሩት መድሃኒቶች በጊዜ ሂደት ተህዋሲያኑ ባሳዩት መድሀኒትን የመላመድ ባህሪ ጥቅም አልባ ሲሆኑ ተስተውሏል። ይባስ ብሎ ደግሞ ከ1970`ቹ ጀምሮ አዲስ የሚገኙት የፀረ ተህዋሲያን መድሀኒት አይነቶች እየቀነሱ መምጣት ችግሩን የከፋ አድርጎታል።

ተህዋሲያን መድሀኒቶችን  መለማመድ ምን ማለት ነው?

በበሽታ እምጪ ተህዋሲያን አማካኝነት የሚፈጠሩ ህመሞችን ለማከምም ሆነ ለመከላከል የሚሰጡ መድሀኒቶች በቀድሞ  መጠን ወይም ከዛ በላይ በሆን መጥን ተስጥቶ ተህዋሲያኑ የማይሞቱ ወይም መራባታቸውን የማያቆሙ ሲሆን ተህዋሲያኑ መድሀኒቱን  መቋቋም ችለዋል ወይም ተለማምደዋል ይባላል።

 

ባክቴርያዎች አንቲባዮቲክን እንዴት ሊለማመ ይችላ?

 

ባክቴሪያዎች  የአንቲባዮቲክ መድሃኒቶችን የመቋቋም አቅም የሚያካብቱበት ምክንያቶች ምንድናቸው?

               

 

የባክቴሪያ መድሃኒቶችን መለማመድ (Antibiotic Resistance) ከተከሰት በኋላ ምን አይጉዳቶች ሊያስከትል ይችላል?

የባክቴሪያ የአንቲባዮቲክ መድሃኒቶችን መለማመድ እና መቋቋም ከሚያመጣቸው ጉዳቶች ውስጥ የጤና እክል (ህክምናውን ጥቅም አልባ ከማድረግ እስከ ህልፈተ ህይወት)፣ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ (የህክምናውን ወጪ በማስወደድ እና የታካሚዎች የህክምና ላይ ቆይታን በመጨመር) ጥቂቶች ናቸው። የበሽታው  ጽኑነት ፣ የባክቴሪያው በሽታ አምጪነት እና  የታካሚው ለተላላፊ በሽታዎች በልዩ ሁኔታ ተጋላጭ መሆን ጉዳቱ እንዲጨምር ያደርገዋል።

 

ከአሁኑ ተገቢው እርምጃ ካልተወሰደ አንቲባዮቲክን የተለማመዱ ባክቴሪያዎች በሚፈጥሩት ህመም ምክንያት በ2050  የ10 ሚሊዮን ሰዎችን ህይወት በአመት እንደሚቀጠፍ እና በኢኮኖሚው ደግሞ 100.2 ትሪሊየን ዶላር ኪሳራ እንደሚያስከትል ይገመታል።

 

ባክቴሪያዎች  የአንቲባዮቲክ መድሃኒቶችን መለማመድን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር  ምን  ማድረግ አለበት?

 

 እንደ ታካሚ

  • የአንቲባዮቲክ መድሃኒቶችን የጤና ባለሙያ በሚያዝበት ጊዜ እና አግባብ ብቻ መውሰድ ።
  • መድሃኒት ተጠቅመው የሚተርፈውን ለሌሎች ሰዎች አለማጋራት። ለራስም በሌላ ጊዜ ያለ ሃኪም ትዕዛዝ አለመውሰድ።
  • እጅ በመታጠብ፣ ተላላፊ በሽታ ከተያዙ ሰዎች ጋር ቅርበት ያለው ንክኪ ባለማድረግ እና ክትባቶችን በመከተብ የኢንፌክሽኖችን ስርጭት መግታት።
  • ምግብ በንጽህና ማዘጋጀት እና ከተቻለ ደግሞ አግባብ በሌለው መልኩ አንቲባዮቲክ አየተሰጣቸው ያደጉ እንስሳትን አለመመገብ።

 

እንደ የጤና ባለሞያ

  • የእጆቻቸውን፣ የምርመራ መሳሪያዎችን እና የምርመራ ክፍሎችን ንጽህና በመጠበቅ የኢንፌክሽን ስርጭትን  መቀነስ።
  • አንቲባዮቲክ መድሃኒት ሲያዙ ለትክክለኛው በሽታ መድሃኒት በትክክለኛው መጠን እና ጊዜ እንዳዘዙ ማረጋገጥ።
  • የአንቲባዮቲክ መድሃኒቶችን ትክከለኛ አወሳሰድ ለታካሚዎች ማሳወቅ።
  • ስለ አንቲባዮቲክ እና ባክቴሪያ መለማመድ ግንዛቤ ማስጨበጥ።
  • ስለተላላፊ በሽታዎችና ስርጭታቸው እንዲሁም የመከላከያ መንገዶችን በበቂ ሁኔታ ማስተማር (ለምሳሌ፦ ክትባት መከተብ፣ እጅ መታጠብ፣ ሲያስነጥሱ አፍ እና አፍንጫ መሸፈን፣ጥንቃቄ ይጎደለው የግብረ-ስጋ ግንኙነት አለማድረግ )

 

 

ማጠቃለያ

 

ተህዋሲያን መድሀኒቶችን ለመቋቋም የሚያስችላቸው ለውጥ ማደበራቸው  አይቀሬ በመሆኑ አግባብ ያለው የፀረ ተህዋሲያን መድሀኒቶችን በመጠቀም ጉዳቱን ከወዲሁ መቀነሱ ተገቢ ነው።

 

 

 

ምንጭ

  1. World Health Organization (2020). Antibiotic resistance. [online] World Health Organization. Available at: https://www.who.int/news-room/fact-sheets/detail/antibiotic-resistance.
  2. Friedman, N.D., Temkin, E. and Carmeli, Y., 2016. The negative impact of antibiotic resistance. Clinical Microbiology and Infection, 22(5), pp.416-422.
  3. Courvalin, P. (2016). Why is antibiotic resistance a deadly emerging disease? Clinical Microbiology and Infection, 22(5), pp.405–407.
  4. ‌ካሣዬመታሰቢያ (n.d.). በሽታና መድሃኒቶች ሲለማመዱ… – Addis Admass Newspaper | Amharic news | Ethiopian news. [online] www.addisadmassnews.com.

ይህ ፅሁፍ በዶ/ር ትንሳኤ አለማየሁ (የህፃናት ህክምና ስፔሻሊስት/የተላላፊ በሽታዎች ሰብ ስፔሻሊስት) እና የጤና ወግ ኤዲተሮች የተገመገመ ነው።