#

ስለ ጨጓራ በሽታ ማወቅ ያለብን ነገሮች። ቆይታ ከ ዶ/ር ኤርምያስ ጋር።

የጨጓራ ህመም አይነቶች ምንድናቸው ? ምን ያህል ሰው በዚህ ህመም ያያዛል? ለበሽታው የሚያጋልጡ ምክንያቶች ምንድናቸው? የህመም ምልክቶቹ ምንድናቸው? ምርመራው ምን ይመስላል? ህክምናውስ ምን ይመስላል? በራሳችን ልናደርጋቸው የሚገቡ ጥንቃቄዎች ምን ይመስላሉ? እነዚህን እና ሌሎች ጠቃሚ ጥያቄዎች ላይ እንወያያለን። Listen Here --- Send in a voice message: https://anchor.fm/yetenaweg/message

35 min
#

The Impact of War/Conflict on Mental Health, focus in Ethiopia በጦርነት ወቅት ስለሚፈጠሩ የአእምሮ ጤና ችግሮች

🧠ከጦርነትና ግጭቶች ጋር ተያይዞ ስለሚፈጠሩ የአእምሮ ጤና ችግሮችና ችግሩን ለመፍታት በኢትዮጵያ ምን እንደታሰበ 🧠ከአእምሮ ጤና ባለሞያ እና ከጤና ሚኒስቴር ሀላፊዎች ጋር የተደረገ ውይይት --- Send in a voice message: https://anchor.fm/yetenaweg/message

1 hr 52 min
#

ስለ ደም ግፊት ህመም ማወቅ ያለብን ምንድነው? What you need to know about high blood pressure?

በዚህ የጤና ወጋችን ፣ የደም ግፊት በምን ምክንያት ይከሰታል? የደም ግፊት እንዳለብን በምን እናውቃለን ? የደም ግፊት በቤተሰብ ይተላለፋል ወይ? ደም ግፊታችን ስንለካ ማድረግ ያለብን ጥንቃቄዎች ምንድናቸው? የደም ግፊት በምን ይታከማል? መድሃኒት ባቋርጥ ምን ችግር አለው ?/መድሃኒቱን ለስንት ግዜ መውሰድ አለብኝ ? እና የመሳሰሉ ጥያቄዎችን እንመልሳለን ። ተጨማሪ ጥያቄ ካላችሁ በፌስ ቡክ እና ትዊተር ገፆቻችን አድርሱን በሚቀጥለው ፕሮግራማችን ላይ የቻልነውን ያህል እንመልሳለን። Listen Here --- Send in a voice message: https://anchor.fm/yetenaweg/message

50 min
#

ስለ አዲሱ ኮሮና ቫይረስ ማወቅ ያለብን ነገሮች ምንድናቸው? What you need to know about the new Coronavirus #COVID19 ?

አዲሱ የኮሮና ቫይረስ (በአዲስ የሳይንስ ስሙ COVID-19) ፣ ከየት መጣ ?/ምን ምልክት አለው ?/ በብዛት በህመሙ የሚጠቁት ማናቸው ? በቫይረሱ ሲያዙ ለፀና ህመም ከዛም ባለፈ ለሞት የሚጋለጡት የትኞቹ ህሙማን ናቸው? በሽታው እንዳይዘን ምን ማድረግ አለብን ? በረራ ማቋረጥ የበሽታውን መስፋፋት ይገታዋል? ስለ እነዚህ ጥያቄዎች መልስ ለማግኘት ይህን የጤና ወጋችንን ተከታተሉን። ሌላ ጥያቄ ካላችሁ በተለያዩ የማህበራዊ ድረ ገፆቻችን ጥያቄይችሁን ላኩልን ፣ የቻልነውን ያህል በሚቀጥለው ወጋችን ለመመለስ እንሞክራለን ። Listen Here --- Send in a voice message: https://anchor.fm/yetenaweg/message

30 min
#

ስለ ኮሌስትሮል መጨመር ህመም ማወቅ ያለብን ነገሮች ምንድናቸው? What you need to know about high cholesterol?

የኮሌስትሮል መጠን መጨመር በአለም ላይ የልብ፣ የስትሮክ ፣የደም ዝውውር መቀንስ ህመምን ከሚያመጡ ምክንያቶች ዋነኛው እንደሆነ ያውቃሉ ? በዚህ የጤና ወጋችን የ ኬሌስትሮል መጨመር ህመም ምንድነው? በምን ምክንያት ይከሰታል? የትኞቹ ምግቦች የበለጠ ለ ኮሌስትሮል መጨመር ህመም ያጋልጣሉ? መቼ ነው የ ኮሌስትሮል መጠናችንን መመርመር ያለብን? የኬሌስትሮል መጨመር በምን ይታከማል? የሚሉትን ነጥቦች አንስተን እንወያይለን ።ሌላ ጥያቄ ካላችሁ በተለያዩ የማህበራዊ ድረ ገፆቻችን ጥያቄይችሁን ላኩልን ፣ የቻልነውን ያህል በሚቀጥለው ወጋችን ለመመለስ እንሞክራለን ። Listen Here --- Send in a voice message: https://anchor.fm/yetenaweg/message

22 min
#

Sleep Hygiene and what you should know about some Sleep disorders. ስለ እንልፍ ማወቅ የሚገባን ንገሮች ምንድናቸው?

በዚህ የጤና ወጋችን ስለ እንቅልፍ እንወያያለን። በእንቅልፍ ሰአት ሰውነታችን ከመታደሱ በላይ ለሰውነት (በተለይ ለህፃናት) እድገት ቁልፍ የሆኑ ሆርሞኖች የሚመነጩበት ሰአት እንደሆኑ ያውቃሉ? የእንቅልፍ ማጣት እና የእንቅልፍ ማነስ ምንድናቸው? እንዴት ይታከማል? ምን ማድረግ ይገባናል? የእንቅልፍ ማጣት ለደም ግፊት ፣ ለስኳር ህመም ፣ ለሰውነት ከልክ በላይ ውፍረት ለካንሰር ህመም እንደሚያጋልጥ ያውቃሉ ? አልኮል ከመኝታ ሰአት በፊት መውሰድ እንዴት የእንቅልፍ ስረአትን እንደሚያዛባ ለመረዳት እና ሎችንም ጠቃሚ ነጥቦች ለመረዳት ይህን ወግ ያዳምጡ። Listen Here --- Send in a voice message: https://anchor.fm/yetenaweg/message

54 min
#

የሴቶች ጤና ክትትል። በዚህ የሴቶች ጤና ወጋችን በጡት ካንሰር እና በማህፀን በር ካንሰር ላይ እንወያያለን።

የዚህ ክፍል የሴቶች ጤና ውይይታችንን ዶ/ር ኤልሳቤጥ አሳረ እና ዶ/ር ማክዳ ካህሳይ ይመሩታል። ስለጡት ካንሰር እና ማህፀን በር ካንሰር ምልክቶች፣ የትኞቹ ሴቶች ለዚህ ካንሰር የበለጠ ተጋላጭ እንደሆኑ ፣ ምን ምርመራ እና ቅድመ ምርመራ እንደሚይስፈልገን እና ህክምናውስ ምን ይመስላል የሚሉት ርዕሶች ላይ ይወያያሉ። ዶ/ር ኤልሳቤጥ አሳረ በ በኒውዮርክ የሪችመንድ ዩኒቨርሲቲ የውስጥ ደዌ ህክምና ስፔሻሊስት ሬዚደንት ሀኪም ናት ። እና ዶ/ር ማክዳ ካህሳይ ደግሞ በኒውዮርክ ማውንት ሳይናይ ሆስፒታል የውስጥ ደዌ ህክምና ስፔሻሊስት ሬዚደንት ሀኪም ናት። Listen Here --- --- Send in a voice message: https://anchor.fm/yetenaweg/message

21 min
#

Updates on #COVID19. ስለ አዲሱ ኮሮና ቫይረስ አዳዲስ መረጃዎች እና ማወቅ የሚገባዎት ነገሮች

በዚህ የጤና ወጋችን ስለ አዲሱ የኮሮና ቫይረስ COVID19 እንወያያለን ። የኮሮና ቫይረስ ምልክቶች ምንድናቸው? ከጉንፋን እና ከኢንፍሉዬንዛ በምን እንለየዋለን ? የተለያዩ በማህበራዊ ሚዲያ ከኮሮና ቫይረስ ጋር የተሰራጩ ትክክል ያልሆኑ መረጃዋችን አንድ በአንድ እያነሳን እንወያያለን። የማህበራዊ መራራቅ ስንል ምን ማለታችን ነው ?እንዴት ነው የበሽታውን ስርጭት የሚቀንሰው ? ከእያንዳዳችን ምን ይጠበቃል? እነዚህና ሌሌች ሀሳቦችን አንስተን እንወያያለን። Listen Here --- Send in a voice message: https://anchor.fm/yetenaweg/message

39 min
#

Latest Updates on #COVID19Ethiopia , Dr.Belete (MD,MSc,PhD ) /Virologist answers your questions.

On our Episode today we will discuss #COVID19Ethiopia, Dr. Belete an expert on Viruses at NIH and Dr.Ermias a Pulmonary and Critical care fellow at Cornell will answer your questions about #COVID19Ethiopia. How it is transmitted, Is it Airborne? Who needs to wear masks? What are the common symptoms ? What is the clinical course when you get the virus? What treatment options are available? What are on the pipeline? Any Vaccines? How Clinate affects transmission of the virus in Africa? What human behaviors contribute to emergence of new viruses? How is #COVID19 affecting you individually and how are you coping with it? #COVID19Ethiopia #StayHome በዛሬው ፕሮግራማችን ዶ/ር በለጠን (የቫይረስ ጥናት ስፔሺያሊስት) ጋብዘን ተወያይተናል። ማስክ ማን መጠቀም አለበት? ምን መድኃኒቶች አሉ ?ክትባት ይኖር ይሆን በቅርብ? ምን አይነት ምርመራ ነው የሚደረገው? ላብራቶሪ ውጤቱ ሁልግዜ ልክ ነው ወይስ ሊሳሳት ይችላል? እና የመሳሰሉትን ጥያቆዎች መልሰናል ። Listen Here --- Send in a voice message: https://anchor.fm/yetenaweg/message

1 hr 36 min
#

Herd Immunity ምንድነው?

በዚህ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ጊዜ Herd Immunity ከበሽታ ሊጠብቀን አይችልም። መኖሩንም ማወቅ አንችልም። የተነገሩንን የመከላከል እርምጃዎች እንከተል። Tweet Herd Immunity ማለት በአንድ ማህበረሰብ ያሉ ሰዎች ውስጥ ለ አንድ ተላላፊ በሽታ ምን ያህሉ በሽታውን የመከላከል አቅም አላቸው የሚለውን ነው የሚነግረን። ሰዎች ይሄን የመከላከል አቅም ወይ ታመው ከበሽታው ሲያገግሙ ያገኙታል ወይም በ ሕብረተሰብ ጤና የሚመረጠው ደግም ማህበረሰብ አቀፍ በሆነ የክትባት  ዘመቻ ሁልኑም ወይም አብዛኛውን ሕብረተሰብ ማዳረስ ሲቻል ነው።  Herd Effect የምንለው ደግሞ በ ማህበረሰብ ውስጥ ከፍ ያለ የ Herd Immunity በመኖሩ የ አንድ በሽታ ከ አንዱ ሰው ወደ ሌላ ሰው የመተላለፍ እድሉ ሲቀንስ ነው።  ምን ያህሉ ሰው ለ አንድ በሽታ የመከላከል አቅም ሲኖረው ነው ይሄን Herd Effect የምናየው የሚለው የሚወሰነው በሽታው ምን ያህል ተላላፊ ነው በሚለው ነው። Listen Here --- Send in a voice message: https://anchor.fm/yetenaweg/message

10 min
#

Care of Chronic diseases in a Pandemic. በ ኮቪድ 19 ምክንያት ከቤት መውጣት ያልቻሉ ሰዎች ህክምና እንዴት ማግኘት ይችላሉ?

እንደ ኮሮና ቫይረስ ያሉ ወረርሽኞች በሚነሱበት ጊዜ ቀጥተኛ ጉዳታቸው ብዙ ነው ።  በ ሚድል ኤጅስ ዘመን  (Middle Ages ) የተነሳው ጥቁር ሞት (Black  Death ) ከ 30-50 ሚልየን ሰዎች እንደሞቱ ይገመታል።  በቅርብ ደግሞ የ HIV pandemic  ምክንያት ከ1981 ጀምሮ ከ35 ሚልየን በላይ ሰዎች ሞተዋል።   የኮሮና ቫይረስም አሁን በአለም ላይ ከአንድ ሚልየን በላይ ሰዎችን ይዟል።  እና ከ 50000 በላይ ሰዎች ደግሞ  ለሞት ተዳርገዋል።  የኢኮኖሚ ጉዳቱ  ደግሞ በጣም ከፍተኛ ነው።    አሁን ማንሳት የፈለግነው ደግሞ በዚህ ወረርሽኝ ምክንያት እንዴት ሌሎች ዘላቂ ህመም ያላቸው ሰዎች በ ክትትል ማነስ ሊጎዱ እንደሚችሉ ነው።  በ 2015 የተሰራ ጥናት እንደሚያሳየው ሰዎች በ ተላልፊ  በሽታው ላለመያዝ ባላቸው ፍራቻ ፣ በ ሆስፒታሎች በአዲስ በሽተኞች መጣበብ ፣ የገንዘብ እና ሌሎች የህክምና ዕቃ መሳሪያዎች ለ ወረርሽኝ መቆጣጠሪያ መዋላቸው የ  አነዚህን ህመምተኞች ሕክምና በጣም ይጎዳዋል።    ለምሳሌ በ 2014 በ ምዕራብ አፍሪካ የተነሳው የ ኢቦላ ወረርሽኝ ቀጥታ ካመጣው ሞት በተጨማሪ ወደ 11,300  ሰዎች የህክምና ክትትል በማጣት ሞተዋል። በነዚህ ሃገራት ያለው የክትባት ስርጭት መጠን ከ 30% በላይ መቀነሱ ታይቷል።   ስለዚህ እነዚህ ተጨማሪ ህመም ያላቸው ሰዎች ሕክምናቸውን የሚያገኙበት መንገድ መመቻቸት አለበት። የተለያዩ  የህክምና ተቋማት ይሄንን ክፍተት ለመሙላት ምን እያደረጉ እንደሆነ በዚች አጭር የጤና ወግ ውይይታችን እናያለን ።   በ ኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ሌላ ዘላቂ የሆነ የጤና ያለባቸው ሰዎች ሕክምና እንዳይቃረጥ መስራት  አለብን Listen Here --- Send in a voice message: https://anchor.fm/yetenaweg/message

27 min
#

Psychology of Pandemics. በዚህ ወጋችን የአእምሮ ጤናን በወረርሽኝ ወቅት እንዴት እንደምንጠብቅ እንወያያለን።

Yetenaweg invites Dr.MaJi Hailemariam (PhD) who is an assistant professor at Michigan State university and is a mental health epidemiologist to discuss mental health issues in the #coronavirus pandemic, particularly #COVID19Ethiopia. We discuss individual and communal coping mechanisms during Isolation and #SocialDistancing. We also invited Dr.Brook Alemayehu, internist in Ethiopia to share us his experience managing #COVID19 in Ethiopia. We also highlighted, how health care workers are particularly affected and what measures we can take to alleviate the stress they are going through. We also discussed effective communication skills to create trust and avoid unnecessary fear. Listen Here --- Send in a voice message: https://anchor.fm/yetenaweg/message

1 hr 7 min
#

COVID 19 -Current Strategies and Plans Ahead. የ ኮቪድ 19 የፖሊስ አማራጮችና ቀጣይ አርምጃዎች።

We Invited Dr.Tewodros Bekele (MD, MPH) Health Economist who has a rich experience in Health Care Policy and Financing and Dr. Belete Ayele (MD, PhD/Virologist at NIH)  to discuss the current #COVID19Ethiopia strategies , what needs to be done in the short and long term to limit the damage from the spread of the disease. Dr. Tewodros brings his experience from other low and Middle income countries on lessons Ethiopia can learn in fighting COVID-19. He set out his 8 steps plan used in other countries.  Also discussed why lockdown may not be a good option for Ethiopia , but working on Moderate social distancing with other steps excuted on a longer period can help curb the spread of disease and may give a cushion to economic fallout.  የ ኮቪድ 19 የፖሊስ አማራጮችና ቀጣይ አርምጃዎች። ከዶክተር ቴዎድሮስ በቀለ የጤና  ኢኮኖሚስት (MD, MPH ) እና ከዶክተር በለጠ (MD, Phd) በ አሜሪካ የጤና ምርምር ተቁዋም የ ቫይረሶች ተመራማሪ  ጋር ብዙ ጠቃሚ ነገሮች ላይ ተወያይተናል። 1. በኢትዮጵያ ውስጥ ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ ፣ የወቅቱ ስርጭት መጠን ፣ የኢትዮጵያ ትንበያ ፣በመካሄድ ላይ ያለው የመንግስት ምላሽ 2 ቫይረሱ እንዴት እንደሚሰራጭ ማወቅ በተለይም አዳዲስ መረጃዎች እንዴት ፖሊሲ ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩ  3 በኢትዮጵያ ለተከሰተው ወረርሽኝ ምላሽ ለመስጠት የህብረተሰባችን ፣ የወረዳ እና የሆስፒታል ደረጃዎች የጤና ስርዓታችንን ማደራጀት ያለበት እንዴት ነው? 4 መንግስት ፈጠራን በመፍጠር በአገልግሎት አሰጣጥ አዳዲስ አሰራሮችን በፍጥነት በማስተካከል ምን ያህል ደረጃ አያዋለ ነው ? 5 ሁሉን ነገሮች መዝጋት ? ለምን ? እና ለምን አይሆንም? ኢትዮጵያስ ይህን ማረግ ይኖርባታል? እና ሌሎችንም ነገሮች ተወያይተናል። እባካችሁ አዳምጡት። Listen Here --- Send in a voice message: https://anchor.fm/yetenaweg/message

2 hr
#

Blood donations during #COVID19 በኮቪድ 19 ወቅት ደም ስንለግስ ማወቅ ያለብን ነገሮች።

Regular voluntary blood donations were not habitually seen in Ethiopia in pre-COVID19 times. With travel restrictions and social distancing measures, the Ethiopian blood bank service had faced depleted stores. Dr Brook and Dr Tinsae discuss how blood product shortages can be managed and what precautions to take in the current COVID19 outbreak and outline the huge benefits donors give with their voluntary acts. Listen Here --- Send in a voice message: https://anchor.fm/yetenaweg/message

28 min
#

Let’s Talk about Suicide. በዚህ የጤና ወጋችን ሰው ለምን ራሱን ወደ መግደል (ራስን ማጥፋት )/ይሄዳል ላይ እንወያያለን።

Yetenaweg Invites Dr.Maji Hailemariam a mental health epidemiologist and assistant professor at Michigan State University and Dr.Azeb Asaminew a Psychiatrist and advisor to Minstry of Health Ethiopia #COVID19 task force on Menatl health and Psycho Social issues to discuss about Suicide. How to discuss about Suicide, who are at risk for suicide, how culture influences how we deal with suicide, what are particular risk posed by COVID19 in incidence of Suicide and how we can particularly help health care professionals in this difficult times. በዚህ ፕሮግራማችን የአእምሮ ጤና ባለሙያዎችን ጋብዘን ስለ አእምሮ ጤና ፣ ራስን ለመግደል ስለሚዳርጉ ምክንያቶች ፣እና ማን የበለጠ ተጋላጭ እንደሆነ እንወያያለን ። Listen Here --- Send in a voice message: https://anchor.fm/yetenaweg/message

53 min
#

ስለ ኩላሊት ህመም ማወቅ ያለብን ነገሮች ምንድናቸው? ቆይታ ከ ዶ/ር ፍጹም ጥላሁን (የኩላሊት ህክምና ስፔሺያሊስት ) የጤና ወግ አዘጋጅ።

የጤና ወግ አዘጋጆች ዶ/ር ኤርምያስ ካቻ እና ዶ/ር ፍፁም ጥላሁን ስለ ኩላሊት ህመም ተወያይተዋል። የኩላሊት ስራ ምንድነው? አጣዳፊ የኩላሊት ህመም ምንድነው?ዘላቂ የሆነ የኩላሊት ህመም ምንድነው? በምን ምክንያት ይከሰታል? ምልክቶች ምንድናቸው? የኩላሊት ህመም እንዳይባባስ ምን ማድረግ እንችላለን? ኩላሊት አጠቃላይ መስራት ሲያቆም ምን አይነት አማራጭ ህክምናዎች አሉ? የኩላሊት ንቅለ ተከላ ህክምና ከዳያሊስስ የተሻለ አማራጭ ነው የምንለው ለምንድነው? አንድ የኩላሊት ህመም ያለበት ሰው መቼ ነው ዳያሊሲስ ያስፈልገዋል የምንለው?/ --- Listen Here Send in a voice message: https://anchor.fm/yetenaweg/message

36 min
#

በኮቪድ የተያዘ ሰው አራሱን ቤት ውስጥ ማስታመም ቢኖርበት ወይም በኮቪድ የተያዘን ሰው ማስታመም ቢኖርብን ልናውቅ የሚገቡን የጥንቃቄ እርምጃዎች ምንድናቸው?

ኮቪድ በሽታ እየተስፋፋ ከመምጣቱ አንፃር በቅርብ ጊዜ ውስጥ ሁሉንም ታማሚ በጤና ማዕከል መከታተል ላይቻል ይችላል። በኮቪድ የተያዘ ሰው አራሱን ቤት ውስጥ ማስታመም ቢኖርበት ወይም በኮቪድ የተያዘን ሰው ማስታመም ቢኖርብን ልናውቅ የሚገቡን የጥንቃቄ እርምጃዎች ምንድናቸው? በዚህ ፖድካስት 1 በሀገራችን ውስጥ አሁን ያለው የኮቪድ ሁኔታ አንዴት ነው? 2 ከአሜሪካ ተሞክሮ ምን አንማራለን 3 አራሳችንን ቤት ዉስጥ አግለን ስንከባከብ መከተል ያሉብን ነገሮች ምንድን ናቸው? 4 ድንገተኛና አደገኛ ምልክቶቹ ምንድን ናቸው? 5 ቤተሰብ ስንከባከብ መከተል ያለብን ነገሮች ምንድን ናቸው? 6 ቀብርንስ በተመለከተ ምን አዲስ ነገር አለ? ምን አይነት መከላከያዎችን መከተል አለብን? 7 አካል ጉዳተኞች አንዴት የበለጠ ተጋላጭ ሊሆኑ ይችላሉ? ምን ማድረግ ይገባናል? 8 አርጉዝ አናቶችን በተመለከተስ? ጡት ማትባትስ ? ሁሉንም አንስተን ተወያይተናል። --- Listen Here Send in a voice message: https://anchor.fm/yetenaweg/message

52 min
#

Health Risks of Smoking. ትምባሆ ማጨስ የሚያመጣቸው የጤና እክሎች ምንድናቸው ? እንዴትስ ነው የ ትምባሆ ማጨስን ሱስ መግታት የምንችለው ?

ትምባሆ ማጨስ የሚያመጣቸው የጤና እክሎች ምንድናቸው ? እንዴትስ ነው የ ትምባሆ ማጨስን ሱስ መግታት የምንችለው ? በዚህ ፖድካስታችን ስለ ትምባሆ (ሲጋራ ) ማጨስ ጉዳቶች በሰፊው እንወያያለን ።   የ ምናነሳቸው ሃሳቦች 📍 *የትንባሆ አይነቶች ምንድን ናቸው?  አጠቃቀማቸውስ? 📍 * አንዱ ከሌላው በሚፈጥሩት ጉዳት ይለያያሉ ወይ? *📍 መደበኛ ሲጋራ ፣ ሺሻ ወይም ሁካ እና የ ኤለክትሮንክ ሲጋራ ያላቸውን ልዩነት እናያለን  📍*ሺሻ /ሁካህ ከ ተለመደው ሲጋራ በባሰ መልኩ እንዴት የጤና ችግር እንደሚያመጣ እንነጋገራለን 📍 *በ እርግዝና ጊዜ የሚያጨሱ ሴቶች ወይም ለሲጋራ ጭስ በተዘዋዋሪ የሚጋለጡ እናቶች በራሳቸው እና በሚወልዱት ልጅ ላይ የሚያስከትለውን ጉዳት አንስተን እንነጋገራለን  📍ከሁለተኛ እጅ የተጎዳኘ ጭስ መጋለጥ የሚፈጥራቸው የጤና ችግሮች ምንድን ናቸው? 📍አጫሾች ማጨስ ቢያቆሙ ምን የጤና ጥቅሞች ሊያገኙ ይችላሉ? 📍ከዚያ በኋላ ሲጋራ ማቆም ጥቅም የለውም የሚባልበት አድሜ አለ አንዴ? 📍ለአጫሾች ለምን ማቆም ይከብዳል? ለማቆም ምን ማረግ አለባቸው? Listen Here --- Send in a voice message: https://anchor.fm/yetenaweg/message

47 min
#

ከልክ ያለፈ ውፍረት (Obesity) – ምክንያቶቹ፣ በጤና ላይ የሚያስከትለው ችግሮች እና እንዴት ከልክ ያለፈ ውፍረትን መቀነስ እንደምንችል እንነጋገራለን።

ከልክ ያለፈ ውፍረት (Obesity) ምን ማለት ነው? መቼ ነው ለጤና ጠንቅ መሆን የሚጀምረው ? ውፍረትን በተመለከተ በማህበረሰባችን ውስጥ ያሉ የተዛቡ አመለካከቶች ፣ ከፍተኛ ውፍረትን የሚያስከትሉ ምክንያቶች ምንድናቸው? ውፍረትን ለመቀነስ የሚጠቅሙ ውጤታማ መንገዶች የትኞቹ ናቸው ? --- Listen Here Send in a voice message: https://anchor.fm/yetenaweg/message

45 min
#

የደም ማነስ በሽታ ምንድነው ?

በዚህ የጤና ወግ ዝግጅታችን ስለ ደም ማነስ እናወራለን። የደም ማነስ በሽታ የሚከሰተው በሰውነታችን ውስጥ የሚገኙ ቀይ የደም ህዋሳት ቁጥር ሲያንስ ወይም በውስጣቸው የሚገኘው ሄሞግሎቢን የሚባለው ሞለኪውል መጠን ሲያንስ ነው።  የደም ማነስ በምን ምክንያት ይፈጠራል ? የደም ማነስ ካለብን ምን ምልክቶች እናያለን?  በላብራቶሪ የደም ምርምራ የደም ማነስ አለ ምንለው መቼ ነው ? የደም ማነስ እንዴት ይታከማል ? በእርግዝና ጊዜ የሚከሰት የደም ማነስ እና ምክንያቶቹ ፣    የአይረን ይዘታቸው ከፍተኛ የሆኑ ምግቦች የትኞቹ ናቸው? እና ስለ ደም መለገስ አንስተን እንወያያለን። --- Listen Here Send in a voice message: https://anchor.fm/yetenaweg/message

26 min
#

ስለ አስም በሽታ ማወቅ ያለብን ነገሮች ?

በዚህ የጤና ወግ ፕሮግራማችን ስለ አስም በሽታ እንንጋገራለን። የአስም በሽታ ምንድነው? ከሌሎች በተለምዶ አለርጂ ፣ ሳይነሳይቲስ ከሚባሉት ህመሞች ያለው ልዩነት ምንድነው? ምልክቶቹ ምንድናቸው? አጣዳፊ ህክምና የሚያስፈልገው መቼን ነው? ዘላቂ ህክምናው ምን ይመስላል? አስምን የሚቀሰቅሱት ነገሮች ምንድናቸው ? እንዴት መከላከል እንችላለን ?/እና ሌሎችንም የመሳሰሉትን ጥያቄዎች አንስተን እንወያያለን ። --- Listen Here --- Send in a voice message: https://anchor.fm/yetenaweg/message

51 min
#

የስትሮክ በሽታ ምንድነው? እንዴት ይታከማል?/እንዴትስ መከላከል ይቻላል?

በዚህ ብፖድካስታችን የምናነሳቸው ነገሮች  • ስትሮክ ምንድን ነው? • ለስትሮክ ተጋላጭነትን የሚጨምሩ ነገሮች ምንድናቸዉ? • በስትሮክ የተያዙ ሰዎች ሊያሳያቸዉ የሚችሉ ምልክቶች ምንድናቸዉ? • አንድ ሰው ስትሮክ እንዳለበት እንዴት ማወቅ ይችላል? • አንድ ሰዉ ስትሮክ እንዳለበት እንዴት ማረጋገጥ ይቻላል? • ስትሮክ እንዴት ሊታከም ይችላል? • ስትሮክ ከመከሰቱ በፊት አስቀድሞ መከላከል ይችላል? • ከስትሮክ ቡሃላ ሊከሰቱ የሚችሉ ጉዳቶች ምንድናቸዉ? • የስትሮክ የመልሶ ማቋቋም (Stroke Rehab) • ከስትሮክ በኋላ ሙሉ በሙሉ የማገገም እድሎች በምን ይወሰናሉ? • በሌላ ስትሮክ በድጋሚ ላለመያዝ ምን ማድረግ አለብኝ? --- Listen Here Send in a voice message: https://anchor.fm/yetenaweg/message

39 min
#

ትምህርት ቤቶችን መቼ እንክፈት ? የልጆቻችንን፣ የመምህራንን እና የወላጆችን ደህንነት እንዴት እንጠብቃለን? ዶ/ር ትንሳኤ አለማየሁ ይመልሳሉ።

በዚህ ፖድካስታችን የህፃናት ህክምና እና ተላላፊ በሽታዎች ስፔሺያሊስት ሐኪም ዶ/ር ትንሳኤ አለማየሁ ትምህርት ቤቶችን እንዴት የልጆቻንን ደህንነት በጠበቀ መልኩ መክፈት እንደምንችል ፣ ምን አይነት ስጋቶች አሉ? ልጆች ትምህርት ቤት በመቅረታቸው የሚያጡት ነገር ምንድነው? የወላጆችንን ፣የመምህሮቻችንን ጤና እና ደህንነት እንዴት መጠበቅ እንችላለን? እና ሌላም ከአድማጮቻችን የደረሱንን ጥያቄዎች ይመልስልናል። --- Listen Here Send in a voice message: https://anchor.fm/yetenaweg/message

51 min
#

ጫት በጤናችን ላይ ምን ተፅዕኖ አለው? በኢትዮጲይ እና በአከባቢው ሀገራት የተሰሩ ጥናቶችን እንመለከታለን።

ምን ያህል ሰው ጫት ይጠቀማል? በጫት ውስጥ ያለው ኬሚካል ምንድነው? ሁሉም ጫት አንድ አይነት ነው? በጤናችን ላይ የሚያመጣው ጉዳት ምንድነው? ጫትን ለጥናት የሚጠቀሙ ሰዎች ውጤታማ ናቸው? በእርግዝና ግዜ ጫትን የሚጠቀሙ ሰዎች በፅንሱ ላይ ምን አይነት ጉዳት ያደርሳሉ? በማህበረሰብ ጤና ጫት እንዴት ይታያል? እና ሌሎችንም ነገሮች እንወያያለን ። --- Listen Here --- Send in a voice message: https://anchor.fm/yetenaweg/message

38 min
#

What we know so far about COVID 19 Vaccines? ተገኙ በተባሉት ኮቪድ 19 ክትባቶች ዙሪያ ቆይታ ከዶ/ር በለጠ ጋር

ዶ/ር በለጠ አየለ በ አሜሪካው የጤና ምርምር ተቋም ለረጅም አመት የቫይረሶች ጥናት ተመራማሪ ነበሩ። አሁን ደግሞ የውስጥ ደዌ ስፔሻሊት ህክምናቸውን ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ይገኛሉ። በዚህ ፖድካስታችን በቅርቡ ውጤታማ ናቸው የተባሉት የኮቪድ 19 ክትባቶች ዙሪያ መልስ ይሰጡናል። እነዚህ ክትባቶች ምን ያህል ውጤታማ ናቸው ? በፊት ከነበሩ ሌሎች ክትባቶች አንፃር እንዴት ይታያሉ? የክትባቶች መገኘት የበሽታውን ስርጭት ያቆመዋል ወይ? መቼ ከበሽታው መስፋፋት በፊት ወደ ነበረው አኗኗር ልንመለስ እንችላለን? እናንሌሎችንም ጥያቄዎች አንስተን እነጋገራለን ። --- Listen Here --- Send in a voice message: https://anchor.fm/yetenaweg/message

49 Min
#

ስለ ቲቢ በሽታ ማወቅ ያለብን ነገሮች ! መተላለፊያው ፣ምርመራው ፣ሕክምናው ምን ይመስላል ?

ንደ አለም ጤና ጥበቃ መረጃ በተለምዶ የሳንባ በሽታ የምንለው (ትበርክሎሲስ/ቲቢ ) በ2019 ዓመተ ምህረት በ ዓለም ላይ ከ 1.4 ሚልየን በላይ ሰዎች ሞት ምክንያት ነው። በ ዓለም ላይ ሞትን ከሚያስከትሉ ታላላፊ ተላላፊ በሽታዎች ቁጥር 1 ገዳይ በሽታ ነው ። ኢትዮጵያ በዓለም ላይ ከፍተኛ የቲቢ ታማሚ እና በቲቢ ምክንያት ሰዎች ከሚሞቱባቸው 30 አገራት አንዷ ነች። በዚህ ፖድካስታችን ስለ ቲቢ በሽታ እንወያያለን በሽታው ከአንድ ሰው ወደ ሌላ ሰው እንዴት ይተላለፋል? የበሽታው ዋና ምልክቶች ምንድናቸው? የቲቢ በሽታ በምን አይነት ምርመራ ይረጋገጣል? ሕክምናው ምን ይመስላል ? ሕክምናው ለምን ያህል ጊዜ ይቆያል? ቤት ውስጥ የታመመ ሰው ካለ ምን አይነት ጥንቃቄ ነው ማድረግ ያለብን ? እነዚህን እና ተያያዥ ጥያቄዎችን እንመልሳለን። --- Listen Here --- Send in a voice message: https://anchor.fm/yetenaweg/message

51 Min
#

Updates on COVID-19 Infection and Vaccinations. የ ኮቪድ 19 በሽታ እና ክትባቶቹ ላይ ማወቅ የሚገባችሁ መረጃዎች

አሁን በሽታው ያለበት ስርጭት ምን ይመስላል ? በ ሀገራችን እና በ አለም ላይ የተለያዩ አይነት የኮቪድ ዝርያዎች (Variants ) አሉ ? ልዩነታቸው ምንድነው ? በክትባቱ ላይ የሚያመጡት ተፅእኖ ምንድነው? በኮቪድ የተያዘ ሰው ክትባቱን መውሰድ ይችላል ወይ? መቼ ( በምንያህል ጊዜ ውስጥ ?) በ ዓለም ላይ የሚታየው ፍትሓዊ ያልሆነ የክትባት ስርጭት የሚፈጥረው ችግር ምንድነው? እና ከናንተ የደረሱንን ጥያቄዎች መልሰናል ። --- Listen Here --- Send in a voice message: https://anchor.fm/yetenaweg/message

54 Min
#

የሪህማቶይድ የ መገጣጠሚያ ህመም ምንድነው?

What you should know about Rheumatoid arthritis ? የሪህማቶይድ የ መገጣጠሚያ ህመም ምንድነው?

What you should know about Rheumatoid arthritis ? የ ሪህማቶይድ የ መገጣጠሚያ ህመም ምንድነው? ለህመሙ የሚያጋልጡ ምክንያቶች ምንድናቸው ? ምልክቶቹ ምንድናቸው ? ምርመራዎቹ ምንድናቸው ? ሕክምናው ምን ይመስላል ? በዚህ ፖድካስት በዝርዝር እንወያያለን --- Listen Here --- Send in a voice message: https://anchor.fm/yetenaweg/message

54 Min

Subscribe