የፊት ጭንብል (Mask ) ማድረግ ያለበት ማነው? በ ቤት ውስጥ ከጨርቅ የሚሰሩ   ጭንብሎች ምን ያህል የመከላከል አቅም አላቸው?

ዶ/ር ብሩክ አለማየሁ (የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት)

ፊት ጭንብል (face mask) ማድረግ ያለበት ማነው?

  • ሆኖም ግን እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ሀገራት ካለው እጥረት አንፃር ሁሉም ማስክ እንዲለብስ ማድረግ በጣም አስቸጋሪ መሆኑ ግልፅ ነው።

የማስክ ዓይነቶችና ልዩነቶቻቸው

  • ብዙ ዓይነት የፊት ማሰክ አይነቶች ቢኖሩም በተለይ የምንጠቀምባቸውን ሁለት የማስክ አይነቶች ላይ ትኩረት እናደርጋለን፡፡ እነርሱም ሰርጂካል ማስክ እና N95 ማስክ ናቸው፡፡
  • ሰርጂካል ማሰክ
    • የተሻለ የሚጠቅመው ማስኩን ካደረገው ሰው የሚወጡ ፈሳሾችንና ድርፕሌቶችን ለመከላከል (Source Control) ነው፡፡
    • በአየር ላይ የሚንሳፈፉ ትልልቅ ፓርቲክሎችና ለማጣራት ይጠቅማል፡፡
    • በተለይ በድሮፕሌት ለሚተላለፉ በሽታዎችን ለመከላከል ይጠቅማል፡፡
    • ንፁህ አካባቢ ለመፍጠርም (ለምሳሌ በቀዶ ጥገና ወቅት) ይጠቅማል፡፡
    • ብዙ ጊዜ በተመሳሳይ ልኬት የሚመጣና ከፊት ጋር ጥብቅ ብሎ በደንብ የማይቀመጥ (noነ-tight fitting) ነው፡፡

በሰርጂካል ማስክና ቤት ውስጥ ከጨርቅ በሚሰሩ ማስክ መሀከል ምን ልዩነት አለ?

የፊት ጭንብል (face mask) የሚጠቀም ሰው ምን ይጠበቅበታል?

  • የፊት ጭንብል ማድረግ ብቻውን በቫይረሱ ከመጠቃት አያድንም፡፡
  • የፊት ጭንብል እንደውም ሰዎችን በተሳሳተ መልኩ እንዲረጋጉና እንዲዘናጉ (false sense of safety) መንገድ ሊከፍት ይችላል፡፡
  • አጠቃቀሙን ካላወቁበት ደግሞ ራሱ የኢንፌክሽን ምንጭም ሊሆን ይችላል፡፡
  • ማንኛውም ሰው የፊት ማሰክ ሲጠቀም መሰረታዊ የሆኑትን የእጅ መታጠብ/የአልኮል ሳኒታይዘር መጠቀምና አካላዊ መራራቅን ማክበር ይኖርበታል፡፡
  • በተጨማሪም ትክክለኛ አጠላለቅ፣ ከተደረገ በኃላ የሚደረጉ ጥንቃቄዎችንና ትክክለኛ አወጋገድን ማወቅ አለበት፡፡

ማጥለቅዎ በፊት ምን ማድረግ አለብዎት?

  • የፊት ጭንብል (face mask) ከማጥለቅዎ በፊት እጅዎን በሳሙናና ውሃ ቢያንስ ለ20 ሰከንዶች መታጠብ ወይም 60 በመቶ እና ከዚያ በላይ አልኮል ባለው ሳኒታይዘር እጅን ማፅዳት
  • ጭንብሉን ያልተቀደደ ወይም ያልተበሳ መሆኑን መመልከት

የማጥለቅ/አጠቃቀም ሂደቱ እንዴት ነው?

  •  ከላይ መሆን ያለበት ሲነካ ጠንከር ያለ ስስ ብረት ባለበት በኩል ነው (ስዕሉን ይመልከቱ)
  • አብዛኛውን ጊዜ ነጩ ክፍል ከውስጥ ሰማያዊው ደግሞ ከውጭ መሆን አለበት
  • መጀመሪያ ጭንብሉን ፊት ላይ ማስቀመጥ፣ በገመዶቹንም ጆሮዎችዎ ላይ ማያያዝ
  • አፍን፣ አፍንጫን እና አገጭን እንዲሸፍን አድርጎ ማስተካከል
  • ከዚያ የላይኛውን ጠንከር ያለውን ክፍል በአፍንጫ ቅርፅ ማስተካከል
  • መጀመሪያ ጭንብሉን ፊት ላይ ማስቀመጥ፣ በገመዶቹንም ጆሮዎችዎ ላይ ማያያዝ
  • አፍን፣ አፍንጫን እና አገጭን እንዲሸፍን አድርጎ ማስተካከል
  • ከዚያ የላይኛውን ጠንከር ያለውን ክፍል በአፍንጫ ቅርፅ ማስተካከል
  • በፊትዎና በጭንብሉ መሃል ክፍተት እንዳይኖር ማድረግ
  • ካጠለቁ በኃላ የውጨኛውን ክፍል አለመንካት፤ ተሳስተው ከነኩ ለ20 ሰከንዶች መታጠብ ወይም 60 በመቶ እና ከዚያ በላይ አልኮል ባለው ሳኒታይዘር እጅን ማፅዳት

የፊት ጭንብል (face mask) አወላለቅ/አወጋገድ

  • ማውለቅ ሲፈልጉ ከጆሮ ጋር የተያያዘበትን ገመዶች በማውለቅ (የውጨኛውን ክፍል ሳይነኩ) ከፊት ላይ ማንሳት
  • መዘጋት ወደሚችል የቆሻሻ መጣያ ውስጥ ማስወገድ
  • በተቻለ መጠን ደግሞ አለመጠቀም

በመጨረሻም በአለም የጤና ድርጅት (WHO) የተዘጋጀውን ይህንን ቪዲዮ መመልከት ተግባራዊ ሂደቱን ያሳያል፡፡ (https://www.youtube.com/watch?v=M4olt47pr_o)

የጤና ወግ

በመረጃ የተመሰረተ ሕክምና ብቻ ።  

………………………………………………………………………………………………………………………..

ይህ የጤና ወግ ድረ ገፅ ነው።
ስለ ጤንነታችሁ ማወቅ የምትፈልጉትን መረጃ የምታገኙበት ፣ በህክምና ባለሙያዎች የሚዘጋጅ የመረጃ ምንጭ ነው።
ሁልግዜም ከሀኪማችሁ ተማከሩ፣ ተጨማሪ መረጃ ከፈለጋችሁ የኛን ድረ ገፅ ጎብኙ።

በጥናት የተደገፈ መረጃ ብቻ እናቀርባለን።

የህክምና ባለሙያዎች ለህሙማኖቻችሁ የሚሆን የሚነበብ መረጃ ከፈለጋችሁ ይህን ግፅ ጠቁሟቸው። ህሙማኖቻችሁ እንዲያውቁት የምትፈልጉትን ነገር መረጃ ጠቅሳችሁ ፃፉልን፣ ስምችሁን ጠቅሰን እናወጣለን። የህክምና ተማሪዎች እንዲጽፉ እናበረታታለን።

በተጨማሪም በጤና ወግ ፖድካስት፣  በ ዩትዩብ ፣በ ትዊተር ፣ በ ፌስቡክ ፣ በቴሌግራም የተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ ገፆቻችን ታገኙናላችሁ ።