በ ዶ/ር ኤርሚያስ ካቻ

የዓለም ጤና ድርጅት እ.ኤ.አ. በዓለም አቀፍ ደረጃ COVID-19 ወረርሽኝ መከሰቱን ካወጀ በኃላ እንዲሁም አገራችን ትምህርት ቤቶች ከተዘጉ በኃላ  ፣ አብዛኞች በቫይረሱ ያልተጠቁትም እንኳ ፣ በቤታቸው ውስጥ ተገልሎ ለመቆየት መርጠዋል። በተለይ የህመሙ ምልክት ያለባቸውና ህክምና ለመሄድ ምልክቱ ያልባሰባቸው ሰዎች፣ ቤት ውስጥ መቀመጡ ብቻ ጭንቀት ሊፈጥር ይችላል ፡፡ በየሰኣቱ የሚቀያየረውም መረጃ የበለጠ ሊያሳስብ ይችላል። ስለዚህ አንዚህን ጊዜ ማሳለፊያ ሃሳቦችና ተግባሮች ቢያረጉ፣ ይህንን ኣስጨናቂ ሰኣት ለጥሩ ነገር ሊጠቀሙበት ይችላሉ። 

1.)  “በመጨረሻ በቤቴ እና በራሴ ላይ ማተኮር እችላለሁ” 

ይህን ኣጋጣሚ ጊዜ ኣጥተው ቤት ውስጥ አሰራዋለው ብለው ያሰቡት ነገር ያከናውኑበት። የቤት አቃዎችን አንደ ኣዲስ ማደራጀት፣ መጽሃፍ ማንበብ የመሳሰሉት። ይህም ሃሳቦት በስራ አንዲያዝ ያረጋል። 

2.)  በተቻለ መጠን ከለት የለት ተግባር ኣይራቁ።

በተቻለ መጠን ከቅድመ መገለል በፊት የነበሮትን የ እለት ተለት ተግባር ለመጠበቅ ይሞክሩ። ይህ ምናልባት ልጆች ላላቸው ቀላል ሊሆን ይችላል። ከቤት ሆነ መስራትም ኣላስፈላጊ የሆኑ ሃሳቦችን ሊፈጥር ይችላል፡፡ ከእንቅልፍ በተመሳሳይ ሰዓት ተነስተው ወደ መኝታ በተመሳሳይ ሰዓት ይሂዱ። ምግብ ይበሉ ፣ ገላዎን ይታጠቡ ፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ  የሚያረጉ ከኖነ ጊዜዎን ያስተካክሉ፡፡ 

3.) ማለቂያ በሌለው የኮሮናቫይረስ የዜና ሽፋን ላይ ከማተኮር ተቆጠቡ

ከስራ ወይም ከማኅበራዊ ግዴታዎች ነፃ ማውጣትዎ ለማሰላሰል ብዙ ጊዜ ይሰጡዎታል፡፡ በተለይ ከዚህ በፊት ባስነጠሰዎትና ጉንፋን በያዞት ቁጥር ጎግል (google) የሚያረጉ ከሆነ፣ ይሄ ጊዜ ለርሶ ኣደገኛ ነው። የተወሰኑ የተዓማኒነት ያላቸው ድር ጣቢያዎችን ብቻ በመምረጥ (who.int ወይም cdc.gov ) ለተወሰነ ጊዜ (ምናልባትም ለ 30 ደቂቃዎች ) ብቻ ይከታተሉ ፡፡ 

4.) ሁከት ያለበት ቤት ወደ ሁከት አእምሮ ሊመራ ይችላል

ውጭ የሚሆነው ነገር ኣሳሳቢ በሆነበት ሁኔታ በተቻለ መጠን ቤትን ማደራጀትና ንጹህ ማረግ የማረጋጋት ተጽኖ ኣለው። ቀኑን በሰኣትና በሚሰራው ስራ  መከፋፈል ያስፈልጋል። በአልጋ ላይ ላለመብላት ወይም ሶፋ ላይ ላለመሥራት ይሞክሩ – ልክ እንደበፊቱ በኩሽና ጠረጴዛው ላይ ይበሉ እና በጠረጴዛዎ ላይ ይስሩ ፡፡ በተጨማሪም ፣ የተዝረከረከ ቤት በአካባቢዎ የማይመቹ እና የመረበሽ ስሜት እንዲሰማዎት ሊያደርግ ይችላል – ስለሆነም በጥሩ ሁኔታ ይያዙት ፡፡

5.) አዲስ የኳራንቲን ሥነ ሥርዓት ይጀምሩ

በዚህ አዲስ ጊዜ በእነዚህ በተገለሉ ቀናት ለምን ልዩ ነገር አይሰሩም? በቀኑ የተወሰነ ሰዓት ይራመዱ። ለጓደኞች እና ለቤተሰብ ይደውሉ ፡፡ ለመመልከት የፈለጉት የቴሌቪዥን ተከታታይ  ድራማ ወይም ሁልጊዜ ማዳመጥ የፈለጉትን የድሮ ዘፈኖችን ይኮምኩሙ ፡፡

6) የሚሰማዎት ጭንቀት በነዚህ መንገዶች ካልተፈታ ባለሙያን በ ስልክ ለማማከር አያመንቱ ።  

Source: https://adaa.org/