የጤና ወግ የእለቱ መልእክት 2 ማርች 19 2020

በዶ/ር ትንሳኤ አለማየው

መጋቢት 9 ቀን 2012 አ.ም. የአለም የጤና ድርጅት ባስተላለፈው ሰርኩላር መሰረት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በ147 ሀገራት (25 የአፍሪካ ሀገራትን ጨምሮ) ተሰራጭቷል 

በኢትዮጵያ እስከ መጋቢት 9 ቀን 2012 አ.ም. ድረስ 6 ህመምተኞች ተለይተው ህክምና እየተደረገላቸው ሲሆን የሁሉም ህመም የከፋ ደረጀ አልደረሰም፡፡

የዛሬው ሌላው እለታዊ መልእክታችን ከህዝብ ትራንስፖርት ጋር ይያያዛል፡፡ በተለይ በከተሞቻችን በህዝብ ትራንስፖርት መገልገያዎቻችን ውስጥ የመስኮት ክፈቱ አትክፈቱ ክርክር የተለመደ ነው፡፡ በህዝብ ትራንስፖርቶች በቂ የአየር መናፈስ አስቀድሞም እንደ ሳንባ ነቀርሳ (Tuberculosis) ላሉ የትንፋሽ ህመሞች ሲያጋልጠን ኖሯል፡፡ በአዲስ አበባ ብቻ በአመት ከ 8200 በላይ ሰዎች በሳንባ ነቀርሳ (Tuberculosis) ይያዛሉ፡፡

ባሁኑ ሰአት እየተዋጋነው ያለው የCOVID19 ህመም ደግሞ ከሚተላለፍባቸው መንገዶች ውስጥ በቅርበት ያለ ትንፋሽ ይገኝበታል፡፡ ዛሬ መጋቢት 10 ቀን 2012 አ.ም. የታተመ ጥናት እንደሚያሳየው አንድ በCOVID19 ህመም የተጠቃ ሰው በሚያስነጥስበት ሰአት ቫይረሱ በቅርበት ባለ አየር ላይ እስከ 3 ሰአት ድረስ ይቆያል 

አረፋፍዶ 5 ሰአት ላይ ታክሲ ውስጥ የገባ ተሳፋሪ በመስኮት አለመከፈት ምክንያት ጠዋት 2 ሰአት ላይ ለተሳፈረ የCOVID19 ታማሚ ትንፋሽ መጋለጥ የለበትም፡፡

የግድ ሆኖ በዚህ ጊዜ ወደ ስራ መሄድ ካለብን ቅርብ ከሆነ ወክ በማድርግ አንሂድ ፣ በታክሲ ወይም በሌላ የህዝብ ትራንስፖርት የምንሄድ ከሆነ ደግሞ ከሌላው ሰው በጣም ሳንተጋግ በመቆየት አራሳችንን ከበሽታ አንጠብቅ። የታክስ ውይም የባስ መስኮት አንዲከፈት አንፍቀድ ። የሳል ህመም ትኩሳት ካለብን ሁልጊዜም አፍና አፍንጫችንን እንሸፍን ። የህመም ምልክት እያለብን በሕዝብ ትራንስፖርት አንጠቀም። 

Yetena Weg

We strive to provide up to date and Evidence based Medical Information