አንዳንድ ሰዎች ሳሙናን ገላን ከመታጠብ አና የተወሰነ ንፅህናን ከመጠበቅ ባለፈ በሽታ አምጭ ተሕዋስያን ለማጥፋት አንደሚያገለግል አያውቁም። አንደውም ሳሙና ከማንኛውም የእጅ ማፅጃ ሳንታይዘሮች የበለጠ በሽታን ይከላከላል ። እጅን በሳሙና እና ውሃ መታጠብ
በአሁኑ ጊዜ በዓለም ዙሪያ እየተዘዋወረ ያለውን አዲሱን ኮሮናቫይረስ ጨምሮ በርካታ የባክቴሪያ እና የቫይረስ ዓይነቶች ለማጥፋት እና ለመግደል እጅን በ ሳሙና በውሃ በቂ ነው።
ሳሙና አንዴት እነዚህን በሽታ አምጭ ተሕዋስያን አንደሚገል አና ከሰውነታችን አንደሚያጠፋ የሚከተለውን እንይ።
ትንሽ ስለበሽታ አምጭ ባክቴሪያዎች እና ቫይረሶችበአሁኑ ጊዜ በዓለም ዙሪያ እየተዘዋወረ ያለውን አዲሱን ኮሮናቫይረስ ጨምሮ አንዳንድ ባክቴሪያዎች እና ቫይረሶች ቅባትነት ባለው መሸፈኛ (Lipid Membrane )ውስጥ የተጠቀለሉ ናችው ። ከኮሮና ቫይረስ በተጨማሪ በዚህ አይነት ሽፋን ውስጥ የተጠቀለሉ ሌሎች ቫይረሶችም አሉ፤ ለምሳሌ ኤች.አይ.ቪ፣ የሄፕታይተስ ቢ እና ሲ፣ ሄርፒስ፣ ኢቦላ፣ ዚካ፣ እና አንጀትን እና የመተንፈሻ አካልን የሚያጠቁ በርካታ ባክቴሪያዎችን ያጠቃልላል።
ቀላል የሚመስለን ሳሙና አንዴት አነዚህን ተሕዋስያን ማጥፋት አና መግደል ይችላል?
ሳሙና የተሠራው ከ መርፌ ቅርጽ ባላቸው ሞለኪውሎች ነው፣ በአንድ በኩል የሃይድሮፊሊክ (ውሃ ወዳድ) ጭንቅላት አለው -ይህም ከውኃ ጋር በቀላሉ ይቀራረባል ፣ በሌላኛው ጫፍ ደግሞ የሃይድሮፎቢክ (ውሃ ጠል የሆነ -ዘይትን እና ቅባቶችን የሚመርጥ ጅራት አለው) ። እነዚህ የሳሙና ሞለኪውሎች በውሃ ውስጥ ሲጨመሩ ፣ አንዱ ጫፍ ከሌላኛው ጋር ለመለያየት ሲሉ እያንዳንዱ ጫፍ ተመሳሳይ ባሕሪ ወዳላችው ሌሎች ሞለኪውሎች ጋር ይወዳጃሉ።
ቀላል የሚመስለን ሳሙና አንዴት አነዚህን ተሕዋስያን ማጥፋት አና መግደል ይችላል?
እጅዎን በሳሙና እና በውሃ ሲታጠቡ በቆዳዎ ላይ የሚገኙ ማንኛውንም ረቂቅ ተሕዋስያን በሳሙና ሞለኪውሎች ይከበባሉ ፡፡የሃይድሮፎቢክ (ውሃ ጠል የሆነ -ዘይትን እና ቅባቶችን የሚመርጠው የሳሙና ሞለኪውሎች ክፍል (the hydrophobic tail) ውሃን ለማምለጥ ይሞክራሉ ፡፡ ይህ ሂደት የሳሙናው ሞለኪውሎች እራሳቸውን በተወሰኑ ጥቃቅን ተህዋሲያን እና ቫይረሶች የቅባት መሸፈኛ ውስጥ ሰርስረው በመግባት በቀላሉ አንዲሞቱ ያረጋቸዋል። ከዛ ደግሞ በደንብ አጃችን ላይ ውሃ በምናፈስበት ጊዜ የሞቱት ቫይረሶች ላይ ተጥርገው ይጠፋሉ።
በአጠቃላይ የእጅ ማፅጃ ሳሙናዎች እንደ ሳሙና ያህል አስተማማኝ አይደሉም ፡፡ የሳሙናን ያህል አንኳን ለመስራት ቢያንስ በውስጣችው ያለው የአልኮሆል መጠን ከ 60% በላይ መሆን አለበት። በዛ ላይ አንዚህን ሳኒታይዝሮች ስንጠቀም ያለውሃ ስለሆነ ቢሞቱ አንኳን ቆዳችን ላይ ሊቀሩ ይችላሉ ።
አንዳንድ ተሕዋስያን መሽፈኛ ቆዳቸው በጣም ጠንካራ አና ቅባት ላይኖረው ስለሚችል በሳሙናም ወይም አልኮሆል ባላቸው ሳንታይዘሮች ላይጠፉ ይችላሉ ። ነገር ግን በሳሙና እና በውሃ በንጹህ ውሃ በደንብ አድርጎ ማሸት አሁንም እነዚህን ረቂቅ ተህዋስያን ከቆዳ ሊያጠፋቸው ይችላል ፣ ለዚህም ነው እጅን መታጠብ ከሳኒታይዝር የበለጠ ውጤታማ የሚሆነው ፡፡ በአልኮል ላይ የተመሠረተ ሳኒታይዘር የንፅህና አጠባበቅ ሳሙና እና ውሃ ተደራሽ በማይሆኑበት ጊዜ ጥሩ አማራጭ ነው ፡፡
በአልኮል ላይ የተመሠረተ ሳንታይዘር የንፅህና አጠባበቅ ሳሙና እና ውሃ ተደራሽ በማይሆኑበት ጊዜ ጥሩ ምትክ ነው ፡፡
በሳሙናና በውሃ እጅን መታጠብ ወረርሽኙን በከፍተኛ ሁኔታ ሊቀንሱ እና የኢንፌክሽኖችን ብዛት ሊገድቡ ከሚችሉ ቁልፍ መንገዶች ዋነኛው ነው። ነገር ግን ዘዴው የሚሠራው ሁሉም ሰው እጆቻቸውን ደጋግመው እና በደንብ ከታጠበ ብቻ ነው:
ሳሙና በተለይ በአሁን ጊዜ ከግል ንፅህና መጠበቂያ በላይ ነው ። በአግባቡ ጥቅም ላይ ሲውል የጋራ የማህበረሰቡ የበሽታ መከላከያ ጋሻ ነው ፡፡ ያስታውሱ-የሌሎች ሰዎች ሕይወት በእጆችዎ ውስጥ ናቸው።
From Yetenaweg
We strive to provide up to date and evidence based medical Information