የምች በሽታ ምንድን ነዉ?

በ ፌቨን ግርማ የአምስተኛ ዓመት የህክምና ተማሪ (AAU)

ምች(cold sore) በተለምዶ ከሚከሰቱ የቇዳ ኢንፌክሽኖች መካከል ዋነኛዉ ሲሆን በተለይም  የላይኛዉ ወይም የታችኛዉ  የከንፈር ጠርዝ ከፊታችን ቇዳ ጋር በሚገናኝበት አካባቢ ላይ በሚወጡ  ውሃ  የቋጠሩ ጥቃቅን ቁስለቶች ይታወቃል።

ከምች በሽታ በሰተጀርባ ምን አለ?  

በተለምዶ የምች በሽታ የምንለው (Cold sores ) የሚከሰተው የኸርፒስ (Herpes) ቫይረስ 1 በሚባሉ በሽታ አምጭ ተዋህስያን ነው። 

የኸርፒስ (Herpes) ቫይረስቤተሰቦች በቫይሮሎጂ የተምሀርት ዘርፍ በስፋት ከተጠኑ የቫይረስ

ቤተሰቦች መካከል አንዱ ነዉ። በዉስጡም ከ100 በላይ የቫይረስ ዝርያዎች ሲኖሩ 8ቱ በሰዉ ልጅ

ላይ በሽታ ያስከትላሉ። ከነዚህም መካከል የምች አምጪ ተህዋስያን ኤች.ኤስ.ቪ- 1

ይገኙበታል።

የኸርፒስ (Herpes) ቫይረስ ቤተሰቦች ቆዳን ጨምሮ በኣይን፣በመራብያ አካላት እንዲሁም የተለያዩ የሰዉነት ክፍሎች ኢንፌክሽኖች ያስከስታሉ።

ግዙፉ የምርምር መረጃ ቋት ፕብ ሜድ በገጹ እንዳሰፈረዉ በአለም ላይ ከ90% በላይ በአዋቂ እድሜ

ላይ ያሉ ጝለሰቦች በአንድ ወይም ከአንድ በላይ የኸርፒስ ቫይረስ ተለክፈዉ ይገኛሉ።

የምች አምጪ ተህዋስያን ኤች.ኤስ.ቪ- 1 (HSV-1) እንዲሁም ኤች.ኤስ.ቪ -2 (HSV-2)

ከጨቅላ ህጽፃናት እስከ የእድሜ ባለፅጋ የእድሜ ክልል ኢንፌክሽን መፍጠር የሚችሉ ሲሆን

ኤች.ኤስ.ቪ- 1 (HSV-1) በምች አምጪ ባህሪዉ ይታወቃል። ኤች.ኤስ.ቪ -1(HSV-1) ከሰዉ ወደሰዉ በቆዳ-ቆዳ እና በቆዳ-የሚውከስ ሽፋን(የአፍ ዉስጥ ለስላሳ ሸፍን መሰል) ንክኪ የሚተላለፍ ሲሆን ኤች.ኤስ.ቪ -2 (HSV-2)  ደግሞ በግብረ ስጋ ግንኙነት ወቅት እንዲሁም ከመራቢያ አካላት-ፊት በሚደረግ ንክኪ

ይተላለፋል።

የኸርፒስ (Herpes) ቫይረስ ዝርያዎች በነጭ የደም ሴሎቻችን ተጠቅተዉ

ከሰዉታችን ሙሉ በሙሉ በመወገድ ፈንታ በሰዉነታችን የነርቭ አካላት ዉስጥ በመሸሸግ

የሰዉነታችን ዉስጣዊ ሁኔታዎች ምቹ እስኪሆኑ በመጠባበቅ ከተሽሽጉበት በመዉጣት በድጋሜ

የምቸ በሽታን ያስከትላሉ።

የምች በሽታ ምልክቶች ምንድን ናቸዉ

የምች በሽታ ተህዋስያን ለመጀመርያ ጊዜ በሰዉነታችን ኢንፌክሽን ስያስከስቱ በአብዛኛዉ ምንም  ምልክት አይኖራቸዉም ነገር ግን በሚከተሉት ጊዜያት ሲከሰቱ የሚከተሉትን የመሳሰሉ ምልክቶች ልያሳዩ ዪችላሉ።

  • የላይኛዉን ወይም የታችኛዉን የከንፈር ጠርዝ በ ቀኝ ወይም  ግራ በበኩል ከፊት ቆዳ ጋ የሚያገናኘዉ ቦታ አካባቢ የመለብለብ፣የማሳከክ ወይም ጨምድዶ የመያዝ ስሜት ሊሰማዎት ዪችላል  
  • ከዚህም ከ 24 ሰአታት በኋላ ከስራቸው  ቀልተዉ  ዉሃ የቋጥሩ ጥቃቅን የቁስለቶች ስብስብ ዪፈጠራል 
  • በምች የሚመጡ  ቁስለቶች ከተፈጠሩበኋላ በቀላሉ በመፈንዳት    ፈሳሽ ሊያፈልቁ ይችላሉ ከዛም ወድያዉ በመድረቅ በቅርፊት ዪሸፈናሉ
  • ከላይ ከተጠቀሱት ምልክቶች በተጟዳኘ የራስ ምታት፣ትኩሳት፣የድካም ስሜት እንዲሁም በአንገት ወይም በብብት ዉስጥ የሚገጙ ሊምፍ ኖድ የሚባሉ እጢዎች እብጠት ሊያስከትል ይችላል።ቁስለቶቹም በተለምዶከ2-4 ሳምንታት ጊዜ ዉስጥ ያለ ጠባሳ ይድናሉ።

 የምች በሽታን በተደጋጋ የሚ ሊቀሰቅሱ ሁኔታዎች ምንድን ናቸዉ?

  • ለሰዉነት በሽታ መከላከል አቅም የመዉረድ የሚያጋልጡ ሁኔታዎች(የኤች.አይ.ቪ፣የካንሰር ህመሞች)
  • በየወር አበባ ጊዜየሚከሰቱ ሆርሞናዊ ለውጦች 
  • በተለምዶ በቫይረስ በሚመጡ እንደ ጉንፋን ያሉ ኢንፌክሽንዎች መጠቃት  
  • ለጸሃይ ጨረር እና ነፋስ መጋለጥ 
  • ጭንቀት እና የአእምሮ ዉጥረት 

  በምች ለሚመጡ ቁስለቶች በቤታችን ምን ማድረግ እንችላለን?

  • የ ህመም ማስታገሻ

     በምች በሽታ ሚመጡን ቁስለቶችበተያያዘየሚሰማዎትን ህመም ለመቀነስ ያለ ሃኪም ትዛዝ በፋርማሲ የምናገኛችውን አይቡፐሮፈን(Ibuprofen) እና አሴታሚኖፈን(Paracetamol) በፋርማሲ ባለሙያው ትዛዝ መሰረት መጠቀም

  • ቅዝቃዜ

ከምች በሽታ ጋር ተያይዞ የሚመጣዉን በቁስላቶቹ ዙርያ የሚከሰት የቆዳ መቅላት እና መቆጣትን ለመቀነስ በቀዝቃዛ ዉሃ በተነከረ ጨረቅ ወይም በበረዶ ቁራጭ  በከቀን ዉስጥ ለተወሰኑጊዘያት ለ5-10 ደቂቃ በቦታዉ ላይ መያዝ እንደሚረዳ የቆዳ ሃኪምዎች ዪናገራሉ።

  • እራስን ከ ጭንቀት ነጻማድረግ 

   የአእምሮ ዉጥረትንመቅነስ የሰዉነትን በሽታ መከላከል አቅም እንደሚጨምር በጥናትዎች ተረጋግጥዋል። ስለዚህም የሚያዝናኑን ነገሮችን በመፈለግእናየአካል ብቃት አንቅስቃሴዎችን በማድረግ ከዚህም በዘለለ የባለሙያ ምክር በማግኘት ልንከላከለዉ  ይገባ

ለምች በሽታ የባህል ህክምናንመጠቀም ተገቢ ነዉ? 

የባህል ህክምናየአንድ አካባቢ ተወላጆችለዘመናት ያካበትዋቸዉ እንስሳን እና እጸዋት ነክ እዉቀቶችን አንዲሁም ማህበረሰባዊ አስተሳሰቦችን መሰረት ያደረገየህክምና ዘርፍ ነዉ።ጆርናል ኦፍ እስያ-ፓሲፊክ ባዮዲቨርሲቲ(Journal of Asia-Pacific Biodiversity) በወጣዉ ጥናት መሰረት የአለማችን64% የሚሆነዉ ማህበረሰብ ለሚገጥሙት የጤናእክሎች  የባህል ህክምናን እንደ መጀመርያ አማራጩ  ይጠቀማል።በአገራችን ኢትዮጺያደገሞ ከ80% በላይ የሚሆነዉ ማህበረሰብ የባህል ህክምና ተጠቃሚ እንደሆነትለያዩ አገር በቀልጥናቶችያመለክታሉ። 

   የምእራባዉያን ባህል ህክምና በምች ለሚመጡ  ቁስለቶችበቫይታሚንሲ የበለጸጉ እንደ ሎሚ፣ብርቱካን፣ኪዊ እና ፓፓያ ያሉ ምግቦችን እንድንጠቀም ዪመክራል። የአገራችን የባህል ህክምና ደግሞ  ዳማከሴ(Ocimum Lamiifolium) የተባለዉ ሃገርበቀል ተክል ቅጠሎችጭማቂ በመጠጣት ወይም ቅጠሎቹን አንድ ላይ በመጨፍለቅ ቁስለቶቹ ላይ በማድረግ እንድንጠቀም  ይመክራል። በዳማከሴ(Ocimum Lamiifolium) ጠቅላላ አጠቃቀም እንዲሁም ስለጸረ ምች አምጪ ትህዋስያን ባህሪያቱ የተደረጉ ጥናቶች ባይኖሩም ስለ አጠቃላይ ጸረ-ህዋስ እና ጸረ-የሰዉነትመቆጣት (Anti-inflammatory)ባህሪያቱየሚያወሱ አንዳንድ የ ሃገር በቀል ጥናቶችብቅ ብቅ ብለዋል።  

ለምች በሽታ ሃኪም ማማከር ተገቢ ነዉ?

በምች በሽታ የሚመጡ  ቁስለቶች በአብዛኛዉ ጊዜበራሳቸዉ የ ሚድኑ በመሆናቸዉ የሃኪም ምክር መሻት ላያስፈል ዪችላል።ነገር ግን ከታች የተዘረዘሩትሁኔታዎች በሚከሰቱበት ጊዜ የሃኪም መክር ማግኘት የግድ ይላል። 

  • የኤች.ኣይ.ቪ ወይም የካንሰር ተጠቂ ከሆንን
  • የምች በሽታ ቁስለቶች አይናችን አካባቢ ከተከሰቱ 
  • ከ2 ሳምንታት በላይ ሳይድኑ የሚቆዩቁስለቶች
  • የአቶፒክ ደርማታይቲስ(Atopic dermatitis) ታማሚከሆንን 
  • በተደጋጋሚ  ቁስለቶቹ የሚ ያጋጥሙ  ከሆነ ሃኪም ማማከር ግድ ይላል።

ሃኪምዎ ምን ሊረዳዎት/ልትረዳዎት ዪችላል/ትችላለች?   

 ሃኪምዎ ቁስለቶቹን አጢኖ ከተመለከተ/ች በኋላ አሳይክሎቪር(Acyclovir) እና ቫልሳይክሎቪር(Valcyclovir) የመሳሰሉ ጸረ ምች አምጪ ተህዋስ መድሃኒትዎችን እንዲሁም የትለያዩ የህመም ማስታገሸ መድሃኒትዎችን  ልያዝሎ ይችላል።ጸረ- ምች አምጪ ተህዋስ መድሃኒትዎቹ በቆዳ ላይ የሚቀቡ ወይም በ ኣፍ የሚዋጡ ሊሆኑ ይችላሉ።  

ዉድ አንባብያን፣ የምች አምጪ ተህዋሲያን እጅግ ተላላፊ በመሆናቸዉ  የምች በሽታ በሚከሰትብን ጊዜ የፊታችንን እና የእጃችንን ንጽህና በአግባቡ መጠበቅ ያስፈልገናል። ቁስለቶቹ ባጋጠሙን ጊዜ የምንጠቀምባቸዉን የከንፈር ቀለሞች እና ቅባቶች ሌሎች እንዳይጠቀሙ  በአግባቡ ማስወገድ ወይም ለይቶ ማስቀመጥ  ብልሃት ነዉ።

 

ይሄ አስተማሪ  የህክምና ፅሁፍ የቀረበው  የጤና ወግ እና የ ኢትዮጵያ ሕክምና ተማሪዎች ማህበር ባዘጋጁት የህክምና ተማሪዎችን የመረጃ አስበሰብ እና ህብረተሰቡን የማስተማር አቅማቸውን ለማዳበር ለታለመ የበጎ ፍቃድ ውድድር ነው። እያንዳንዱ ፅሁፍ በዘርፉ ባለሙያ ስፔሺያሊስት ሀኪም የታየ እና እርማት ተደርጎበት የቀረበ ነው ።

Editor Dr. Tinase Alemayehu