በሲራክ ቢትወደድ (በአ.. /// የህክምና ተማሪ-C2)

መቅድምአንድየ43 ዓመት ጎልማሳወደ ጤና ጣቢያ የተመላላሽህክምናክሊኒክውስጥገብቷል እናም ላለፉት 2 ወራትበፊንጢጣው አነስተኛደምመፍሰስ እንዳጋጠመው ይናገራል።ደሙምሁልጊዜደማቅቀይ፣ከሰገራው የተለየእናወደመጸዳጃው ሳህንላይ ይንጠባጠባል ፣በተጨማሪምበፊንጢጣአካባቢማሳከክና አበጥ ያለ ነገር እንዳለ ይሰማዋል።  ውድ አንባቢያን የዛሬውን ጽሁፋችንን በ አንድ ታካሚ ታሪክ ጀምረናል። ይህ ታካሚ እርሶ ቢሆኑ ወደ ህክምና ተቛም ይሄዱ ነበር? ወይስ አጠገብዎት ላለ ለቤተ-ዘመድ  ወይም ለጓደኛዎ ያማክራሉ? ይህንን ጥያቄ ያነሳነው አብዛኛውን ጊዜ በሀገራችን በእንደዚህ አይነት ቦታዎች ማለትም በፊንጢጣና በመራቢያ አካባቢ የሚከሰቱ ህመሞችን የመደበቅና ወደ ህክምና ተቋማት ይዞ ያለመሄድ ልማድ ስላለብን ነው።  ሌላው በሀገራችን ጎልቶ የሚታየው ከህክምና ጋር የተያያዘ ችግር የበሽታ ስያሜዎች ፣ አሰያየምና በአንድ የሰውነት አካባቢ ላይ ለሚገኙ የተለያዩ ህመሞችን በአንድ ስያሜ የመጥራት ነው። ለዚህም ማሳያ እንዲሆን የኪንታሮት ህመምን እንውሰድ።   በተለምዶ  በሰውነታችን ላይ የሚከሰቱ ሁሉንም እባጮች ኪንታሮት የማለት ልማድ አለ። ከነዚህም ውስጥ ፊት ላይ፣እግር ላይ፣ መራቢያ አካላት ላይ እንዲሁም ፊንጢጣ ላይ የሚወጡትን ያካትታል። እነዚህ እባጮች ሁሉም የተለያየ አይነት ምክንያት የተለያየ አይነት ምልክትና የተለያየ አይነት ህክምና ነው ያላቸው። አብዛኛውን ጊዜ ህጻናት ፊት ላይ የሚወጣው ኪንታሮት (Molluscum contagiosum) ምክንያቱ ፖክስ ቫይረስ ሲሆን የሚነሳውም ከቆዳ ነው፤ ነገር ግን በፊንጢጣ ላይ የሚወጣው  ኪንታሮት የሚነሳው ከደም ስር ነው።  ሌላው ጎልቶ የሚታየው ችግር ደግሞ ሁሉም በፊንጢጣ አካባቢ ለሚወጡ እባጮች(Tumors) “የፊንጢጣ ኪንታሮት” ነው ብሎ መንስዔያቸውና የጉዳት መጠናቸው ለተለያዩ በሽታዎች ተመሳሳይ ስያሜ ሰጥቶ ተመሳሳይ ህክምናዎችን መቀበል ነው።  ህመሞቹ ግን የተለያዩ ሊሆኑ  ይችላሉ ። ለምሳሌ ፊንጢጣ አካባቢ የወጣ መግል( perianal abscess) ፣ የፊንጢጣ መሰንጠቅ(Anal fissure)፣ቂጥኝ(Anal condylomata) ና የፊንጢጣ ካንሰር(Anal cancer) ሊሆን ይችላል። ለ መግቢያ ያክል ይህንን ካልን ለዛሬ ወዳዘጋጀነው ስለ ፊንጢጣ ኪንታሮት ህመም እንመልከት። 

                                         የፊንጢጣ ኪንታሮት

የፊንጢጣ መተላለፊያ ቱቦ(Anal canal) ሰገራ የሚያልፍበትና ወደ ውጪ የሚወጣበት ከፊንጢጣ የመጨረሻው  4 ሴንቲሜትር ርቆ የሚገኝ ስፍራ ነው። በዚህ አካባቢም በ 2 ደረጃ እርስ በእርስ ተያይዘው ያሉ የደም ስሮች ሲገኙ እነርሱም ሄሞሮይድ ቅንጅት(Hemorrhoid plexus) ይባላሉ። እነዚህ የደም ስሮች ወይም ሄሞሮይድስየፊንጢጣእናየታችኛውፊንጢጣ ክፍልመደበኛየሰውነትአካል ሲሆኑ ሁሉም ሰው ላይ ይገኛሉ።  እነዚህ የደም ስሮች ሁለት ጥቅም ሲኖራቸው አንደኛው የፊንጢጣቆዳንሰገራውተንተርሶ ሲወጣ ከጉዳት ለመጠበቅእንደትራስይሠራሉ። ሁለተኛው ጥቅም  ደግሞ ፊንጢጣ መውጫንና  መግቢያ ላይ የመቆጣጠር  ስራ አጋዦች ናቸው። ሄሞሮይድስአብዛኛውንጊዜችግርአይደሉም፣ነገርግንካበጡና ከደሙ ችግርሊሆኑይችላሉ። እነዚህ የደም ስሮች እና ሽፋናቸው ሲያብጥ የፊንጢጣ ኪንታሮት ይባላል።  የፊንጢጣ ኪንታሮት ማንኛውም ግለሰብ ላይ የሚከሰት ቢሆንም ያላግባብ ትልቅ የሚሆነውና  ችግር የሚፈጥረው 4% በሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ነው።  ችግሩ በሴቶችም በወንዶችም ላይ የመከሰት እድሉ እኩል  ሲሆን ዕድሜያቸው ከ 45 እስከ 65 ዓመት በሚሆናቸው የሕብረተሰብ ክፍሎች ላይ በብዛት ሲከሰት  ይታያል።

 

    ምስል1፡ የሄሞሮይድ ቅንጅት(Hemorroid plexus) ሚገኙበት ቦታ(ምንጭ; JaypeeDigital.com hemorrhoid location)

 

     የኪንታሮት ስነ- ህይወት ገለጻየሆድውስጥግፊትመጨመር እንደየሆድድርቀትእናረዘምላለጊዜማማጥሄሞሮይድስያስከትላልተብሎይታመናል።ምክንያቱምየደረቀሰገራ ለማስወጣት ታማሚው በሚታገልበት ጊዜ የፊንጢጣ ግድግዳው እየሳሳ ሊለጠጥ ይችላል።እርጅናንተከትሎ የሚመጣው ኪንታሮት ደግሞ ምክንያቱም እድሜ እየጨመረ ሲመጣ በደም ቧንቧ ዙርያ የሚገኙ ጡንቻዎች እየሳሱና እየላሉ ስለሚመጡ በቀላሉ ሊለጠጡ ይችላሉ። ሌሎቹ ምክንያቶች ደግሞ እንደ ጉበት በሽታና  ሆድ እቃ ውስጥ  የሚከሰቱ እጢዎች የሚፈጥሩት የሆድውስጥግፊትመጨመርየደም መልስደምመመለስን(Venous return)መዘጋትሲያስከትልየሄሞሮይድ ቅንጀት(Hemorrohid plexus) መጨናነቅእናውጥረትንበማምጣት ሲያብጡ ኪንታሮቱ ተፈጠረ እንላለን። 

የኪንታሮት ህመም አይነቶች

1. ውስ ኪንታሮት የሚባለው ከላይኛው የሰገራ መውጫ ክፍል ማለትም ከ ቋሚ መስመሮች(dentate line) በላይ ያበጡት የደም መልስ ስሮች ወደ ታች ሲሄዱ የሚፈጠር የኪንታሮት አይነት ነው። እነዚህን ውስጣዊየኪንታሮት አይነቶችን ከውጭ በኩል ማየት አዳጋች ነው። እያደር ግን ሰገራ በሚወጣበት ወቅት በውስጥ የተፈጠረውንኪንታሮት በመጫንና በመግፋት በፊንጢጣ በኩል ወደ ውጭ ሊያስወጣው ይችላል። ይህም ውጭ ያፈነገጥ ውስጣዊ ኪንታሮት ይባላል።

2.     ውጫዊ ኪንታሮት የሚባለው ከታችኛው የሰገራ መውጫ ክፍል የሚነሱ ያበጡ  የደም መልስ ስሮች ሲሆኑ በቀላሉ ከፊንጢጣ በኩል በአይን ብቻ በመመልከት መኖሩን ማወቅ ይቻላል።

      ምስል 2 የፊንጢጣ ኪንታሮት ስነ-ህይወታዊ ገለጻና አይነቶች (ምንጭ፡ www.medicinenet.com/hemorrhoids/article.htm) የፊንጢጣ ኪንታሮት ታማሚው በሚያሳየው የህመም ምልክት ደግሞ በ4 ደረጃዎች ይከፈላል። ይህም ማለት አንድ ታካሚ ደረጃ 1 ጀምሮ  በጊዜ ሂደት ተገቢውን ህክምና ባለማድረግ ወደ ደረጃ 4 ሊደርስ ይችላል። የፊንጢጣ ኪንታሮትን በእንደዚህ አይነት ደረጃ መከፋፈል የሚጠቅምው እያንዳንዱ ደረጃየራሱ የሆነ ህክምና ስላላው ነው። ደረጃዎቹም የሚከትሉት ናቸው፣

 

ደረጃ 1: ታማሚው መጸዳጃ ቤት ተጠቅሞ ሲጨርስ የሚታይ የደም መፍሰስ ብቻ ካለ

ደረጃ 2፡ ታማሚው በሚፀዳዳበት ጊዜ የሚወጣ እባጭ ሲኖርና እባጩ በራሱ የሚመለስ ከሆነ

ደረጃ 3፡  የሚወጣው እባጭ በራሱ የማይመለስ ና ለመመለስ እርዳታ ሚሻ ከሆነ(በጣት የሚመለስ) ከሆነ

ደረጃ 4፡ የሚወጣው እባጭ  ውጪላይ አብጦ ከቀረ እና ወደ ውስጥ አልመለስም ካለ

የኪንታሮት ህመም መንስኤዎች

  • ማማጥና ማማጥን የሚያስከትሉ ሁኔታዎች፡ የሰገራ ድርቀት፣ ሀይለኛና አጣዳፊ ተቅማጥ፣ ለረጅም ጊዜያት መጸዳጃ ቤት መቀመጥ፣ በቂ ፋይበር አለመጠቀም እና ከበድ ያሉ ስራዎች መስራት
  • በተለያየ ምክንያት ሆድ ውስጥ እባጭ ካለ፡ የማህጸን ዕጢ፣ እርግዝናና የጉበት በሽታ
  • ዕድሜ
  • በቤተሰብ የዘር ሐረግ ውስጥ የችግሩ መኖር

የኪንታሮት ህመም ምልክቶች

  • በፊንጢጣ አካባቢ መቆጥቆጥ
  • ሰገራ ላይ የሚታይ ቀይ ደም
  • በፊንጢጣ አካባቢ እባጭ መሳይ ነገር መታየት
  • ሰገራ በሚወጣበት ወቅት የህመም ስሜት መኖር እና ማሳከክ
  • ደም ለብዙ ጊዜያት የፈሰሰ ከሆነ ደግሞ የደም ማነስ ምልክቶች

የኪንታሮት ህመምን በምን ልንከላከል እንችላለን?

የፊንጢጣ ኪንታሮት ዋነኛ ምክንያቱ የሰገራ ድርቀት ነው። የሰገራ ድርቀትን ለመከላከል ደግሞ የምንመገበውን ምግብ ማሰተካከል ማለትም በፋይበር የበለጸጉ የምግብ አይነቶችን መመገብ እነርሱም እንደ ቅጠላቅጠል ጎመንና ሰላጣ፣ ፍራፍሬዎች ሙዝ ብርቱካንና ፖም፣ የስንዴ ዳቦ፣ የበሰለ አተር፣ የበሰለ ምስርና ያልተፈተገ የገብስ ቆሎ ወይንም በህክምና ባለሞያ ትዕዛዝ የሰገራ ማለስለሻ መድሀኒት መጠቀም ድርቀትን ሊከላከሉ ይችላሉ።

በተጨማሪም የምንወስደውን የፈሳሽ መጠንን መጨመር፣ ለረጅም ጊዜያት ለማማጥ አለመሞከርና የመቀመጫ አካባቢ ንጽህና መጠበቅ የኪንታሮት ህመምን ሊከላከሉ ይችላሉ።

የኪንታሮት ህመም ከተከሰ እንዴት ልናክመው እንችላለን?

የኪንታሮት ህመም አንዴ ከተከሰት ደረጃው እየጨመረ እንዳይሄድ ከላይ እንዳልነው የሰገራ ድርቀትን መከላከል እና እባጩ እንዲኮመሽሽ እና ህመሙ እንዲጠፋ ደግሞ በቤት ውስጥ ለብ ያለ ውሀ በማዘጋጀት ጨው በመጨመር  ለ 10-15 ደቂቃ  በቀን ከ2-3ጊዜ መዘፍዘፍ (Sitz bath)  ኪንታሮትን የማከም አቅም አለው።

ይህን ሁሉ ተጥቅሞ ህመሙ ካልተሻለ የጤና ባለሞያ በማማከር የተለያዩ የሚቀቡ ክሬም(Anti-Hemorrhoidal cream) ወይም በፊንጢጣ በኩል የሚገቡ መድሃኒቶች ሊታዘዙ ይችላሉ። እነዚህም መድሀኒቶች ፊንጢጣ አካባቢ የሚገኙትን የደም ስሮች በማጥበብ እብጠቱን፣ማቃጠሉንና ማሳከኩን ይቀንሳሉ።  አንድ ታካሚ ይህንን ህክምና በአግባቡ ከተጠቀመ እስከ 80% የመዳን እድል አለው።  ሆኖም ግን ይህንን ሁሉ ተጠቅሞ ህመሙ ከበረታ ወደ ቀጣይ የህክምና አማራጭ መሄድ ይኖርበታል።

ይህም  ስክሌሮቴራፒ(Sclerotherapy) ሲሆን በህክምና በተመረጡ ኬሚካሎች ደምስሩ በሚወጣበት ቦታላይ በመርጨት እንዲኮመሽሽና እንዲኮማተር በማድረግ ማከም ይቻላል። ሌላኛው አማራጭ  ደግሞ ደምስሩን ከመነሻው በመቋጠር  ከ7-10 ቀን ውስጥ በ ራሱ እንዲወድቅ በማድረግ የሚደረግ የህክምና ዘዴ ረበር ባንድ ላይጌሽን(Rubber band ligation) ይባላል። የመጨረሻው የፊንጢጣ ኪንታሮት መፍትሔ ኪንታሮቱን በኦፕሬሽን(Operative hemorrhoidectomy ) ማስወገድ ነው።

የፊንጢጣ ኪንታሮት ካልታከመ ምን ሊያስከትል ይችላል?

የኪንታሮት ህመም ካልታከመ ከ ደረጃ 1 እየጨመረ እስከ ደረጃ 4 ደርሶ ለህክምና ከባድ መሆን ፣ ኪንታሮቱ ከመጠን በላይ በማበጥ ሃይለኛ የደም መፍሰስ አምጥቶ  ለ ደም ማነስ በሽታ መጋለጥ። እንዲሁም ደም በመቋጠር ከፍተኛ ህመም ማምጣትና ኪንታሮቱ ተጠምዝዞ በመታነቅና የደም ዝውውር መገታት(Strangulated) የመጥቆርና ጋንግሪን መፍጠር። በሰገራ መውጫ አካባቢ ደግሞ ብዙ ባክቴሪያዎችስለሚኖሩ ከፍተኛ ኢንፌክሽን በመፍጠር እና ወደ መላው የሰውነት ክፍል በመሰራጭት እስከ ሞት ሊያደርስ ይችላል።

 

ዋቢ

1.      Norman S.Williams, P. Ronan O’Connell, Andrew McCaskieBailey & Love’s Short Practice of Surgery, 26th Edition ;P1250-1257
2.      Food, Medicine and Healthcare Administration and Control Authority of Ethiopia;
Standard Treatment Guidelines For General Hospital Third Edition, 2014 ; P92
3.      Anteneh Ayelign Kibret ,Mohammed Oumer, Abebe Muche Moges. Prevalence and associated factors of hemorrhoids among adult patients visiting the surgical outpatient department in the University of Gondar Comprehensive Specialized Hospital, Northwest Ethiopia.  April 20, 2021 https://doi.org/10.1371/journal.pone.0249736
 
ይህ ፅሁፍ በዶ/ር የአብስራ መኮነን (የቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት) እና የጤና ወግ ኤዲተሮች የተገመገመ ነው።