የትልቁ አንጀት ካንሰር የምንለው ከካንሰር አይነቶች አንዱ ሲሆን ከትልቁ አንጀት እስከ ፊንጢጣ ድረስ ያለውን አካል የሚያጠቃ ነው። የትልቁ አንጀት ካንሰር በአሁኑ ጊዜ በሀገራችን ውስጥ ቁጥራቸው እየጨመሩ ከመጡ የካንሰር አይነቶች አንዱ ሲሆን በዓለም አቀፍ የካንሰር ጥናት ኤጀንሲ(IARC) መሠረት እንደ እኤአ በ2020ዓ.ምበተደረገውዓለም አቀፋዊ ጥናትቀዳሚከሚባሉየካንሰርአይነቶች3ኛውን ደረጃ ይይዛል። ይህ ካንሰር በሀገራችንም ውስጥ በተደረገ ጥናት በተመሣሣይ ደረጃ ላይ ይገኛል። ለትልቁ አንጀት ካንሰር መከሰት ይህ ነው ተብሎ የሚጠቀስ አንድ ብቻ ምክንያት የለም። በአብዛኛውም ጊዜ በዘር መልላይ በሚመጡ ለውጦች ስብስብ እንዲሁም ደግሞ ከአካባቢያችን ጋር በሚኖረን መስተጋብር የሚፈጠር ነው።
ለትልቁ አንጀት ካንሰር አጋላጭ ተብለው ከሚጠቀሱት ውስጥ፣
መለወጥየማንችላቸው
. በእድሜመግፋት- ከ40-50ዓመትጀምሮ
. በዘር የሚተላለፍ- ከአንድ በላይ በቅርብ የቤተሰብ አካላት ላይ የትልቁ አንጀት ካንሰር ከተገኘ በዘር የሚተላለፍ አይነት መሆኑ ከፍተኛ ነው።
መለወጥየምንችላቸው
. አትክልት፣ፍራፍሬ እና ጥራጥሬ አብዝቶ አለመመገብ
. የታሸጉ ምግቦች፣ከፍተኛ ስብ እና ቅባት ያላቸውን ምግቦች አብዝቶ መጠቀም
. ከመጠን ያለፈ ውፍረት፣የአካል እንቅስቃሴ አለማድረግ
. ማጨስ
. ከመጠንያለፈየአልኮልመጠጥመጠቀም
. ከዚህቀደምየሆድእብጠትበሽታከነበረ
ምልክቶቹ
. የደም ማነስ ምልክቶች – ቶሎ የመድከም ስሜት፣ እይታብዥየማለት፣ ራስንማዞር
. ደም የቀላቀለ ትውከት
. ደም የቀላቀለ ሰገራ የሆድ ህመም
. የተቅማጥ ወይም ድርቀት መፈራረቅ
. ክብደት መቀነስ፣ድካምድካም ማለት
ወደ ሌላ አካላት የመሠራጨት ምልክቶች
የጉበት ስርጭት
. ሆድ አከባቢ አብጠት እንዲሁም ህመም
. የሆድ ውሃ መቋጠር፣የሆድመነፋት
የሳንባ ስርጭት
. ትንፋሽ ማጠር
. ሳል
. ደም የቀላቀለ አክታ
አደገኛ የሚባሉት ምልክቶች
. ደም የቀላቀለት ውከት
. ደም የቀላቀለ ሰገራ
. የሆድ ፀባይ መለዋወጥ
. ያልተገባ የክብደት መቀነስ
. የደም ማነስም ልክቶች
ምርመራ
በጣት በፊንጢጣ በኩል የሚደረግ ምርመራ
ይህ ምርመራ በፊንጢጣ በኩል የጤና ባለሙያዎች በጓንት የተሸፈነ ጣት በማስገባት የተለየ እብጠት፣ ህመም ፣ ደምመፍሰስ ካለ ለመለየት ይሞክራል። ይህምርመራቀላልእናወጪየሚቀንስነው።
ኮሎኖስኮፒ
በዚህ ምርመራ በቀጭን ቱቦ መሰል መሣሪያ ላይ ካሜራ በማድረግ በፊንጢጣ በኩል እስከ ትልቁ አንጀት ያለውን አካል ለማየት ይሞከራል። ይህ ምርመራ የትልቁ አንጀት ካንሰርን ለመመርመር ተመራጭ ነው። ከላይ ከተጠቀሱት ምርመራዎች በተጨማሪ በደም ምርመራ በመጠቀም የዕጢ ጠቋሚ ምርመራ፣ የሰገራ ምርመራ እና የሲቲስካን ምርመራ ሊደረጉ ይችላሉ።
ህክምና
የትልቁ አንጀት ካንሰር ህክምና የብዙ ባለሙያዎች ትበብር የሚጠይቅ ነው። የቀዶጥገና፣ የውስጥደዌ፣ የጨረር እንዲሁም የሌሎችን ሙያ እገዛ የሚጠይቅ ነው። ህክምናው በካንሰሩ የስርጭት ደረጃ ይወሰናል። በሽታው ወደ ሌሎች አካላቶቻችን ካልተዛመተ በቀዶጥገና ሊታከም ይችላል።ከዚህም በተጨማሪ የኬሞቴራፒ እና የጨረር ህክምና እንደ አስፈላጊነቱ ይሰጣል።
ከህክምና በኋላ ክትትል
ከትልቁ አንጀት ካንሰር ቀዶጥገና በኋላ መደበኛ የሆነ ክትትል ያስፈልጋል። በየጊዜው የዕጢ ጠቋሚ ምርመራን በመከታተል መጠኑ ከሰውነታችን መቀነሱን ማረጋገጥ አለብን። እንዲሁም ህክምናውን በጨረስን እስከ ሶስተኛው ዓመት ድረስ በየዓመቱ የደረት ራጅ እና የሆድ ሲቲስካን ምርመራ፣ ከዚያም ቀጥሎ በየ5 ዓመቱ እነዚህን ምርመራዎች ማድረግ ይጠቅማል። ይህም ካንሰሩ ካገረሸ በቶሎ በህክምና ለማግኘት ይረዳል።
ቅድመ-ምርመራ የሚያስፈልጋቸው ተጋላጭ ሰዎች
. ከላይ የተጠቀሱትን አደገኛ ምልክቶች የሚያሳዩ ሰዎች
. የሆድ እብጠት በሽታ ያለባቸው ሰዎች
. በቅርብ የቤተሰብ አካል ተጠቂ ካለ
ዋቢማጣቀሻዎች
Colorectal Cancer: Risk Factors and Prevention | Cancer.Net, 2018
Deressa BT, Cihoric N, Tefesse E, Assefa M, Zemenfes D. Multidisciplinary Cancer Management of Colorectal Cancer in TikurAnbessa Specialized Hospital, Ethiopia. J Glob Oncol. 2019 Oct;5:1-7. doi: 10.1200/JGO.19.00014. PMID: 31589543; PMCID: PMC6825246.
- Zemenfs B. KotissoA Two- year review of Colorectal Cancer at TikurAnbessa Specialized Hospital, Addis Ababa, Ethiopia 2015
Memirie S, Habtemariam M, Asefa M, Deressa B, Abayneh G, Tsegaye B, et al. Estimates of Cancer Incidence in Ethiopia in 2015 Using Population-Based Registry Data. Journal of Global Oncology. 2018. pmid:30241262
https://www.iarc.who.int/featured-news/ccam2021/
ይህ ፅሁፍ በዶ/ር የአብስራ መኮነን (የቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት) እና የጤና ወግ ኤዲተሮች የተገመገመ ነው