የጤና ወግ የዕለቱ መልክት 1 ማርች 19 2020

ሰሞኑን አንዳየነው በተለያዩ ቦታዎች በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የተሳተፉበት ስልጠና አና ስብሰባ ሲደረግ አይተናል። በቀጣይ ቀናትም ይሄ ሁኔታም የሚቀጥል ይመስላል። የተቀረው አለምም ሆነ የአፍሪካ ሃገራት ጥብቅ በስብሰባዎች ላይና ሌሎች 

ቫይረሱን ከሚያስፋፉ ማናቸውም ነገሮች ጥብቅ የሆነ እገዳ እየሰጡ ባለበት እንዲሁም  በኛም ሀገር ይህን ከግንዛቤ በማስገባት የተለያዩ ትምህርት ቤቶችን እስከመዝጋት እርምጃዎች  ከወሰድን በጥቂት ቀናት ውስጥ እነዚህ ስብሰባዎች መደረጋቸው አሳሳቢ ነው። 

የቫይረሱ መስፋፋት የበለጽጉ ሃገሮችን በጣም እየፈተነ ይገኛል። የጀርመኗ ቻንስለር ወይዘሮ ማርክል በትናንትናው እለት የቫይረሱ መስፋፋት ከሁለተኛው የአለም ጦርነት የበለጠ ፈትኖናል በማለት ገልጸውታል። እንደ ኢትዮጵያ አይነት በቂ የህክምና ባለሞያና የሌላቸውን በኢኮኖሚ ያልበለጸጉ ሃገራትን ደሞ እንዴት ሊጎዳ እንደሚችል ማሰብ አይከብድም።

ይህን በማገናዘብ የጤና ወግ  የህብረተሰባችን ጤና እና ደህንነት ስለሚያሳስባት  ከዚህ በመቀጠል ያሉ ብዙ ሰው የሚካፈልባቸው ስብሰባዎች ለጊዜው እንዲቆሙ እና የማህበረሰቡ ጤና ቅድሚያ እንዲሰጠው ትጠይቃለች።  

የጤና ወግ