በ ረድኤት ወልደሩፋኤል 

(በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ህክምና ኮሌጅ የ4ኛ አመት የህክምና ተማሪ)

በቤተሰብ ውስጥ የኢኮኖሚ አቅምን እና የጤና ሁኔታን ያላገናዘበ የልጆች ቁጥር መብዛት በቤተሰቡም ሆነ ማህበረሰቡ ላይ የሚያመጣው አሉታዊ ተፅእኖ ከፍተኛ መሆኑ ይታመናል።ለዚህ ነው የልጆችን ቁጥር መመጠን እና አራርቆ መውለድ በጤና ባለሞያዎችና በህብረተሰብ ሳይንስ ተመራማሪዎች አፅኖት ተስጥቶት የሚመከረው።

የወሊድ መቆጣጠሪያ ወ መከላከያ ዘዴዎች፣ እርግዝናን ለማዘግየት ወይም ለማስቀረት የሚጠቅሙ ዘዴዎች ሲሆኑ የቤተሰብ ቁጥርን ለመመጠን አና ያልተፈለገ እርግዝናን ለመከላከል ያገለግላሉ። እነዚህን ዘዴዎች በአጠቃላይ ልማዳዊ ዘዴዎች እና ዘመናዊ ብለን በ2 ከፍለን መመልከት እንችላለን። በዚህ ፅሁፍ ላይ ለአረዳድ እንዲያመች በ3 ከፍለን እናያቸዋለን።

  • ልማዳዊ (ባህላዊ)  ዘዴዎች
  1. ከግብረ-ስጋ ግንኙነት መቆጠብ (Abstinence) 
  2. የወንድ ዘር ፈሳሽን ከሴት ብልት ውጪ መፍሰስ (Withdrawal/Coitus interrupts)
  3.  ጡት ማጥባት (Lactation)
  • ተፈጥሮአዊ ዘዴዎች
      1. የቀን አቆጣጠር (Calander-based method)
      2. ከማህፀን የሚወጣ ፈሳሽን መከታተል (Cervical mucus rhythm method)
      3. የሰውነት ሙቀትን በመከታተል (Basal Body Temperature method/ BBT)
  • ሰዉ ሰራሽ ዘዴዎች
    1. ከሆርሞን የተዘጋጁ
      • የወሊድ መከላከያ እንክብል(Contraceptive pills )
  • ጥምር እንክብል (Combined Oral contraceptive/poll)
  • ነጠላ እንክብል (Progestin only /Mini/ pill)
  • የድንገተኛ ጊዜ እንክብል (Post pill)
  • የወሊድ መከላከያ መርፌ (Injectable)
  • በየ2ወሩ የሚወሰድ (NET-EN)
  • በየ3 ወሩ የሚወሰድ (DMPA/Depot)
  • በክንድ ውስጥ የሚቀመጥ  የወሊድ መከላከያ (Implants)
  • Norplant
  • Implanon
  • Jadelle
  1. በማህፀን የሚቀመጥ ሉፕ (IUD)
  • ፐር የያዘ ሉፕ (Copper IUD)
  • ሆርሞን የያዘ ሉፕ (Progestin IUD)
  1. የወንድ ዘር ፈሳሽን ወደ ማህፀን እንዳይገባ የሚከላከሉ ዘዴዎች (Barrier methods)
  • ኮንዶም
  • የማህፀን ሽፉን (cervical cap)
  • ስፐርሚክሳይድ
  • ዲያፍራም
  1. ዘላቂ የመከላከያ ዘዴዎች
  • የወንድ  
  • የሴት

ከላይ እንደተጠቀሰው በአጠቃላይ ከ15 የሚበልጡ የወሊድ መቆጣጠሪያ ዘዴዎች ሲኖሩ በዚህ ፅሁፍ ላይ ከሰው ሰራሽ ዘዴዎች መካከል የተወሰኑትን እንዳስሳለን።

  • የወሊድ መከላከያ እንክብል

  • በአፍ የሚወሰ እንክብሎች ሲሆኑ በውስጣቸው የያዙአቸው ሆርሞኖች በተፈጥሮ በሰውነታችን ውስጥም የሚመረቱ እና ከወር አበባ እና እርግዝና ጋር የተያያዙ የአካልችንን ስራ የሚቆጣጠሩ ናቸው። የረጅም ጊዜ እንክብሎች በውስጣቸው ባለው የሆርሞን ብዛት ተመስርተን በተጨማሪ ጥምር እና ነጠላ ብለን እንከላቸዋለን።
  • እንክብሎቹ በየቀኑ በተመሳሳይ ሰዓት መወሰድ ይኖርባቸዋል። 
  •  ያለሀኪም ትእዛዝ ከመድሀኒት ቤቶች ገዝቶ መጠቀም የሚቻል ሲሆን ይህም ለአጠቃቀም ምቹ ያረጋቸዋል። 
  • በትክክለኛው መንገድ ከተጠቀሙት እርግዝና የመከሰት እድሉ  99% እርግዝናን መከላከል ይችላል ። ነገር ግን በአጠቃቀም ጊዜ ከሚኖ ስህተቶች ጋር ተያይዞ እርግዝና የመከሰት እድሉ እስከ 7/100 ድረስ ከፍ ሊል ይችላል
  • እንክብሎቹን መጠቀም ካቆሙ በኃላ ማርገዝ ቢፈለግ በ 3 ወር ጊዜ ውስጥ ወደ ቀድሞ የልጅ መውለድ  አቅም መመለስ ይቻላል፡፡
  • ጡት ለሚያጠቡ ሴቶች አመቺ ነው፡፡ 
  • እርግዝናን ከመከላከል በተጨማሪ የወር አበባ ህመምን እና መዛባትን ለማስተካክል እንጠቀመዋለን።ለረጅም ጊዜ መጠቀም በመሀፀን ግርግዳ ካንሰር የመያዝ እድልን ይቀንሳል።
  • ተጓዳኝ ጉዳቶች 
    • እንክብሉን መውሰድ የተጀመረበት የመጀመሪያ ወራት ላይ የወር አበባ ለውጦች ሊከሰት ይችላል። የወር አበባ ቀን መዛባት፣ የወር አበባ ደም መብዛት እና ማጠር። 
    • የራስ ምታት
    • ማቅለሽለሽ
    • አልፎ አልፎም እንደመድሀኒቱ  አይነት የሚወሰን ሆኖ ለደም መርጋት የማጋለጥ ባህሪ ሊኖረው ስለሚችል ለሁኔታው ተጋላጭ የሆኑ ሴቶች ከጤና ባለሞያ ጋር መማከር ይኖርባቸዋል።
  • በመርፌ የሚሰጥ የእርግዝና መከላከያ (ዴፖ) 

  • ይህ የእርግዝና መከላከያ በየሶስት ወራት የጤና ባለሙያ ጋር በመድ በክንድ ላይ በመርፌ መልክ የሚወሰድ ነው፡፡ 
    • በትክክለኛ አጠቃቀም ከተገለገልንበት እርግዝና መከሰት እድሉ 0.2/100 ይሆናል። ነገር ግን በአጠቃቀም ጊዜ ከሚኖ ስህተቶች ጋር ተያይዞ እርግዝና የመከሰት እድሉ እስከ 4/100 ድረስ ከፍ ሊል ይችላል፡፡
    • ይህን የእርግዝና መከላከያ የሚጠቀሙ ቶች ቀለል ያለ የወር አበባ ወይም ምንም የወር አበባ ላይታያቸው ይችላል፡፡መርፌውን መጠቀም ከቆ በኃላ ወደ ቀድሞ የልጅ መውለድ አቅም ለመመለስ ከ6ወር እስከ 1 አመት ጊዜ ሊወስድ ይችላል።          
    • ተጓዳኝ ጉዳቶች 
      • የክብደት መጨመር ሊታይ ይችላል።
  • የወር አበባ ቀን መዛባት ፣መቅረት ሊያጋጥም ይችላል። 


  • በክንድ ውስጥ የሚቀበር የእርግዝና መከላከያ (Implant)

  • ኢምፕላንት በክንድ ቆዳ ውስጥ በጤና ባለሙያ የሚቀበር የመከላከያ አይነት ነው። በክንድ ውስጥ የሚቀበሩት በውስጣቸው ሆርሞኖችን የያዙ የክብሪት እንጨት የሚያክሉ አንድ ወይም ሁለት የፕላስትቲክ ዘንጎች ናቸው።
  • እንደየመድሃኒቱ አይነት ለ 3 ወይም ለ5 ዓመታት ይቆያል  
  • 99% በላይ ውጤታማ ነው። ይህን ዘዴ ከሚጠቀሙ ከ1000 ሴቶች ውስጥ በአንድዋ ላይ ብቻ ያልተፈለገ እርግዝና ሊከሰት ይችላል።
  • በማንኛውም ጊዜ ከክንድ ውስጥ በባለሞያ ማስወት የሚቻል ሲሆን ከወጣ በኋላም ወዲያው ወደ ቀድሞ የልጅ የመውለድ አቅም መመለስ መቻሉ ተመራጭ ያደርገዋል።
  • ጡት ለሚያጠቡ ሴቶች ሊጠቀሙት ይችላሉ።
  • ተጓዳኝ ጉዳቶች 
    • የወር አበባ መዛባት
    • የክብደት መጨመር ወይም መቀነስ
  • የኮፐር የያዘ በማህጸን-ውስጥ የሚቀመጥ መሳሪያ (IUD)/የኮፐር ሉፕ) 

  • የኮፐር IUD በማህጸን ውስጥ በጤና ባለሙያ የሚቀመጥ የ”T” ቅርጽ ያለው የፕላስቲክ ቁስ ነው። ይህ ቁስ መጠኑ ትንሽ የሆ በላዩ ይ የኮፐር ገመድ የያዘ ነው። ከሆርሞን ነጻ እና እስከ 10 ዓመታት እርግዝናን መከላከል የሚችል  መከላከያ ዘዴ ነዉ። 

  • ይህን ዘዴ ሚጠቀሙ ሴቶች ውስጥ እርግዝና የመከሰት እድሉ 1/1000 ብቻ ነው።

  • ውለድ በተፈለገ ሰአት በቀላሉ የሚወጣ ሲሆን ከወጣ በኋላም በፍጥነት ወደ ልጅ የመውለድ አቅም መመለስ ያስችላል።

  • ጡት ለሚያጠቡ ሴቶችም ሊጠቀሙት ይችላሉ።

  • እንደ የድንገተኛ ጊዜ የእርግዝና መከላከያ ዘዴ ማገልገል ይችላል። ልቅ ከሆነ የግብረ ስጋ ግንኙነት በኃላ ከ5-7 ቀን ውስጥ ከገባ፣  99% ውጤታማ የድንገተኛ ጊዜ የእርግዝና መከላከያ ሆኖ ሊያገለግል ይችላል።

  • ተጓዳኝ ጉዳቶች 

  • የኢንፌክሽን ተጋላጭነት 

  • የወር አበባ ብዙ/ረዘም ያለ ሊሆን ይችላል 

  • ወር አበባ ወቅት የህመም ስሜት

  • ኮንዶም

  • ይህን የእርግዝና መከላከያ ዘዴ በግብረ ስጋ ግንኙነት ጊዜ እንዲደረግ የተዘጋጀ ነው። ለሴቶች እና ለወንዶች ተብሎ በሁለት ይከፈላል። በብዛት በገበያ ላይ የሚገኘው የወንዶች ኮንዶም ነው። 
  • የወንድ ኮንዶም 87% ውጤታማ ነው። ይህ ማለት አጋሮቻቸው ን ዘዴ  ከሚጠቀሙ 100 ሴቶች ከ 10 -15 ሚሆኑት ላይ ብቻ በተለያዩ ምክንያቦቨቶች ላይሳካ ይችላል።
  • ኮንዶምን ከሌሎች የእርግዝና መከላከያዎች የሚለየው በአግባቡ ከተጠቀሙት ከእርግዝና በተጨማሪ ኤች አይ ቪን ጨምሮ ከተለያዩ የአባላዘር በሽታዎች መከላከሉ መቻሉ ነዉ።

 

ንጭ

Family planning, A global handbook for providers 2018 ED, WHO

WHO fact sheet, November 2020