በ ዶ/ር ትንሳኤ አለማየሁ / የሕፃናት እና የተላላፊ በሽታዎች ስፔሻሊስት, (የጤና ወግ )
እስካሁን ባለ መረጃ የCOVID19 ህመም የበለጠ ሞት እያስከተለ የሚገኘው እድሜያቸው ከ65 አመት በላይ የሆኑት ላይ ነው (ይህ የበለጠ የመያዝ እድልን አያመላክትም)፡፡
በጣልያን በ2018 አ.ም. እነዚህ እድሜያቸው የገፉ ነዋሪዎች (ከ65 አመት በላይ) ከህዝቡ 21.7% ነበሩ ።
ይህም ጣልያንን እድሜያቸው ከ65 አመት በላይ ነዋሪዎችን በመያዝ ከአለም ከጃፓን ቀጥሎ ሁለተኛ ያደርጋታል
ባሁኑ ሰአት በCOVID19 የሞቱ ጣልያናውያን በህመሙ ከተያዙት 7.2% ነው፡፡ ይህን ከቻይና አንፃር ስናየው 3 እጥፍ ሆኖ እናየዋለን፡፡ እነዚህ ቁጥሮች እድሜያቸው ከ65 አመት በላይ ቻይናውያን ከአጠቃላይ ህዝቡ 11% መሆናቸውን ስንገነዘብ ልዩነቱን የበለጠ ገላጭ ያደርጋል፡፡ (ምንጭ -JAMA )
በጣልያን እድሜያቸው ከ 80 እና ከ 90 በላይ የሆኑ ሰዎች መብዛታቸው ትልቅ አስተዋፃኦ ቢኖረውም በ COVID19 ምክንያት ሞቱ የተባሉት ሰዎች አቆጣጠር Criteria ከ ቻይና የተለየ መሆኑም አስተዋፃኦ ሳይኖረው እንዳልቀረ ይሄው ጥናት ያመላክታል።
ምን እንማራለን?
በኢትዮጵያ በ2018 አ.ም. እድሜያቸው ከ65 አመት በላይ ነዋሪዎች ከአጠቃላይ ህዝቡ 4% ነበሩ ፡፡ ምንም ያህል ቁጥሩ አናሳ ቢመስል፣ በተለይ አዛውንቶችን የሚንከባከቡ ተቋማት ለCOVID19 ተጋላጭ እንደሆኑ እንማራለን፡፡ ምሳሌ – የመቄዶንያ እና የጌርጌሴኖን የእርዳታ ድርጅቶች”
ስለዚህ ለነዚህ ለበሽታው ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰቡን ክፍሎች በተለየ ደግሞ የመጠበቅ ኃላፊነት ይኖርብናል። ያን ማረግ የምንችለው ደግሞ በሽታውን ለሌሎች ላለማስተላለፍ በቤት በመቀመጥ ፣ እጃችንን ሁልጊዜ በአግባቡ በመታጠብ እና ሌሎች በጤና ጥበቃ የተነገሩንን እርምጃዎች በአግባቡ በመቀጠል ነው።
የጤና ወግ
በመረጃ የተመሰረተ ሕክምና ብቻ ።
………………………………………………………………………………………………………………………..
ይህ የጤና ወግ ድረ ገፅ ነው።
ስለ ጤንነታችሁ ማወቅ የምትፈልጉትን መረጃ የምታገኙበት ፣ በህክምና ባለሙያዎች የሚዘጋጅ የመረጃ ምንጭ ነው።
ሁልግዜም ከሀኪማችሁ ተማከሩ፣ ተጨማሪ መረጃ ከፈለጋችሁ የኛን ድረ ገፅ ጎብኙ።
በጥናት የተደገፈ መረጃ ብቻ እናቀርባለን።
የህክምና ባለሙያዎች ለህሙማኖቻችሁ የሚሆን የሚነበብ መረጃ ከፈለጋችሁ ይህን ግፅ ጠቁሟቸው። ህሙማኖቻችሁ እንዲያውቁት የምትፈልጉትን ነገር መረጃ ጠቅሳችሁ ፃፉልን፣ ስምችሁን ጠቅሰን እናወጣለን። የህክምና ተማሪዎች እንዲጽፉ እናበረታታለን።
በተጨማሪም በጤና ወግ ፖድካስት፣ በ ዩትዩብ ፣በ ትዊተር ፣ በ ፌስቡክ ፣ በቴሌግራም የተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ ገፆቻችን ታገኙናላችሁ ።