የጤና ወግ የህክምና ተማሪዎች ለ ህብረተሰቡ ጠቃሚ የሆኑ መረጃዎችን የመፃፍ ባህላቸውን እንዲያዳብሩ እና ከሌሎች የዘርፉ ባለሙያዎች ልምድ እንዲጋሩ በማሰብ ከ ኢትዮጵያ የህክምና ተማሪዎች ማህበር ጋር በመተባበር ያዘጋጀነው ትምህርታዊ ውድድር በጣም ውጤታማ ነበር።
በርካታ እውቀታቸውን እና ልምዳቸውን ማካፈል የሚፈልጉ፣ ከዛም በላይ ቀለል ባለ መልኩ ማስረዳት የሚችሉ በጣም ጎበዝ ተማሪዎች እንዳሉ አይተናል።
የፃፏቸውን የተለያዩ አስተማሪ መረጃዎች በ yetenaweg.com እና የተለያዩ የማህበራዊ ሚድያ ገፆቻችን ለ ህዝቡ እንዲደርሱ አድርገናል ።
ከዛም ባለፈ እያንዳዱ ተማሪ በፃፉት መረጃ አይነት ከዘርፉ ስፔሻሊስት ሐኪም በግል ሙያዊ የሆነ አስተያየት እንዲያገኙ ( review with feedback ) አድርገናል።
ሁላችሁንም እናመሰግናለን። ሁላችሁም በመሳተፋችሁ አሽናፊዎች ናችሁ ። ለ ትምህርታችሁ ያላችሁን ትጋት እና ለ ህብረተሰቡ ያላችሁን አክብሮት አስመስክራቿል ።
የጤናወግ ለሁላችሁም የዲጂታል ኦክስጂን መለኪያ (Digital Pulse oximeter ) ሽልማት ታበረክትላቹሃለች !!!
ከዚህ በተጨማሪ ከቀረቡልን ፅሁፎች ውስጥ – ከ ርእሱ አንፃር ፣ ምንጭ አጠቃቀስ እና የሀገራችንን ሁኔታ አካቶ በ ማቅረብ የ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የህክምና ተማሪ የሆነችው ህሊና ከበረ አጠቃላይ አሽናፊ ሆናለች። ያቀረበችው ፅሁፍ ርዕስ “የአዕምሮ ጤና እንክብካቤ በኢትዮጲያ” ነው። ለሷ ደግሞ የLittmann Classic 3M Stethoscope ሽልማት እንሰጣለን
የአሸናፊዎች የስም ዝርዝር እና ያቀረቡት የህክምና ፅሁፍ
1.አጠቃላይ አሽናፊ ህሊና ከበረ (3ኛ ዓመት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሕክምና ተማሪ)
ያቀረበችው ፅሁፍ Link >> : የአዕምሮ ጤና እንክብካቤ በኢትዮጲያ
Littmann Classic 3M Stethoscope
2. ሌሎች አሽናፊዎች በሙሉ የ Digital Pulse oximeter አሽንፈዋል
ሳሙኤል መስፍን (4ኛ ዓመት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሕክምና ተማሪ)
ያቀረበው ፅሁፍ : Link >> ስትሮክ (STROKE) ምንድነው
ቤቴል ዳዊት ደሣለኝ (ዶ/ር) (የመጨረሻ ዓመት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሕክምና ተማሪ)
ያቀረበችው ፅሁፍ :Link >> ስለ አስም በሽታ ማወቅ ያለብን ነገሮች
አብነት ተስፋዬ (2ኛ ዓመት የ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሕክምና ተማሪ)
ያቀረበው ፅሁፍ : Link >> ከፍተኛ የደም ግፊት (Hypertension )
ፌቨን ግርማ ( የአምስተኛ ዓመት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሕክምና ተማሪ)
ያቀረበችው ፅሁፍ : Link >> የምች በሽታ ምንድን ነዉ?
በኤልሳቤጥ አባይ ዓመት (የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የPC 1 ሕክምና ተማሪ)
ያቀረበችው ፅሁፍ : Link >> የድብርት ህመም ምንድን ነው?
መዋዕል ግርማ (የ አርሲ ዩኒቨርሲቲ የ አሰላ ሪፈራል ሆስፒታል ህክምና ተማሪ- Clinical Year 1
ያቀረበው ፅሁፍ : Link >> የምጥ መሠናከል (Obstructed Labor)
ኤልሳ ወልዴ (የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሕክምና ተማሪ)
ያቀረበችው ፅሁፍ : Link >> ከእርግዝና ጋር ተያይዞ የሚመጣ የደም ግፊት መጨመር (ፕሪኤክላምሲያ )