የኮሮና ቫይረስን መስፋፋትን መከላከያ መንገዶች አንዱና ዋንኛው ማህበራዊ መራራቅን መፍጠር (social distancing) ኢትዮጵያ ውስጥ ካለው ነባራዊ ሁኔታ አንጻር በጣም ከባድ ነው። በመንግስት በኩል እየተደረጉ ያሉ አንዳንድ ጥረቶችን የሚበረታቱ ናቸው፤ ለምሳሌ የትራንስፖርት ሚኒስትሯ የፐብሊክ ሰርቪሶሽ ላይ የቅድመ ጥንቃቄ እርምጃዎችን መውሰድ መጀመራቸውን ገልጸዋል። እነዚህን መሰል ጥንቃቄዎች አስፈላጊነታቸው ለማንም ግልጽ ነው። የጤና ወግም ይህን የሚኒስትሩን እርምጃ በእጅጉ ያበረታታል። 

ይህ በዚህ እንዳለ ግን በከተማዎች በተለይ የታክሲና የአውቶብስ አጠቃቀማችንና ሰልፎች ማህበራዊ መራራቅን በጣም አስቸጋሪ ያደርጉታል። በዚህ አንጻር መንግስት በተቻለ መጠን ተጨማሪ የመጓጓዣ መንገዶችን እንዲያመቻች እንጠይቃለን፤ ይህ ችግር ካልተፈታ ቫይረሱን መከላከል ስለማይቻል። ነዋሪዎችም የድርሻችሁን እንድትወጡ በዚህ አጋጣሚ እንጠይቃለን ። 

ለምሳሌ ታክሲዎችና አውቶብሶች መስኮቶቻቸውን በመክፈት በቂ አየር እንዲገባ ማድረግ፣

በዚህ ሰአት ትምህርት ቤቶች ስለተዘጉ ተማሪዎች በተቻለ መጠን ከቤት እንዳይወጡ ማድረግ ይህም የመጓጓዣ ተጠቃሚውን ቁጥር ይቀንሳል የተማሪዎችንም በቫይረሱን የመያዝ እና የማስተላለፍ እድል በእጅጉ ይቀንሳል። 

ከዚህ በተጨማሪ ወክ ማድረግ የሚቻሉ ቦታዎች ወክ ማድረግ ሌላው አማራጭ ነው። 

ከዚህ በተጨማሪም ስራ እንደመሄድና አስቤዛ እንደማድረግ ያሉ በጣም አስፈላጊ ነገሮች ውጨ ከቤት አለመውጣት ።

ዝግ ቤት ውስጥ የሆኑ ካፌና ባሮች አለመሄድ ይመከራል።  

በተለይ ማንኝውም የሳል ምልክት ያለበት ወይም እድሜያቸው የገፋ ሰዎች የህዝብ ትራንስፖርት ለጊዜው መጠቀም የለባቸውም፤ ከነአካቴው ከቤት ባይወጡም ይመከራል። 

እነዚህ እርምጃዎች እርስ በርስ ይደጋገፋሉ፤ እኒህን ባደረን ቁጥር በሽታውን ስርጭት እንከላከላለን።  

መንግስት የእጅ መታጠብያ መንገዶችን ማበረታታቱ በጣም የሚደገፍ ቢሆንም በጣም ተቀራርቦ መታጠብ ቫይረሱን ለመከላከል አይረዳም፤ ስለዚህ አጅ በምንታጠብበት ጊዜ በቂ የሆነ ርቀትን መጠበቅ ኣለብን። 

ከዚህ በተጨማሪም እጅ መታጠብን በተለያየ መንገድ ታዋቂ ሰዎች እያበረታቱ እንደሆነ ተገንዝበናል። የእጅ አስተጣጠብን በተመለከተ የአለም የጤና ድርጅትን መመሪያ የተከተለ መሆን አለበት የእጃችንን ሁሉንም ክፍሎች ጣቶቻችንን መዳፎቻችንን የእጃችንን ጀርባ የጣቶቻችንን ጫፎች ጠፍራችን ስር በደንብ በሳሙና እሽት አርጎ ቢያንስ ለ20 ሰከንድ መታጠብ አለብን፤ ታጥበን ስንጨርስ የቧንቧውን እጀታ ወይ በሶፍት ካልተቻለም በክንዳችን መታጠፍያ (በክርናችን) መዝጋት አለብን። 

ከዚህ በተጨማሪም ከእጃችን በተጨማሪ ብዙ ግዜ የምንነካካቸውን እንደ ሞባይል ስልኮች የኮምፒውተር ኪቦርዶችን የበር እና የፍሪጅ እጀታዎችንና መሰል ነገሮች በየግዜው ማጽዳት አለብን። 

ትላልቅ ፎቆች የምንጠቀም፤  በተቻለ መጠን ደረጃዎችን አንጂ ሊፍቶችን አለመጠቅም፤ ሌሎች ተጠቃሚዎች ጋር ሊፍት ውስጥ ከተገናኘን በጠባብ ሊፍት ውስጥ የሚያስል ሰው ሊኖር ይችላል፤ ያንን መከላከል አይቻልም። እንዲሁም የሊፍት ቁጥሮችን ብዙ ሰው ስለሚነካው ለበሽታ ሊያጋልጠን ይችላል። ግድ ሆኖ ሊፍት ከተጠቀምን ግን ፤ ከተጠቀምን ብኋላ እጃችንን በሚገባ መታጠብ አለብን።

እነዚህና መሰል ጥንቃቄ በማድረግ እራሳችንንና አካባቢያችንን እንጠብቅ።

እንደ ኮሮና ቫይረስ ያሉ ቶሎ ተዛማች በሽታዎች ሲፈጠሩ በህብረተሰቡ ውስጥ መደናግጥን ይፈጥራሉ። የተዛቡ መረጃዎች ይበዛሉ። በተለይ በዚህ የማህበራዊ ሚዲያ ዘመን በአንድ ቦታ የተነሳ የተሳሳተ መረጃ በአጭር ጊዜ ውስጥ ብዙ ቦታ ይዳረሳል ። አሁንም አያየነው ያለነው ነገር ይሄ ነው 

በተለይ የህክምና ባለሙያዎች ፣ ታዋቂ ሰዎች ፣የሚዲያ ሰዎች፣የመንግስት ባለስልጣናት ፣ በህዝቡ ዘንድ ተደማጭነት ስላላችሁ የምታጋሩት መረጃ ትክክለኛ መሆኑን ሁሌም አጣሩ።

የጤና ወግ የሁልጊዜም አላማ በጥናት አና በ መረጃ የተደገፈ የህክምና ትምህርት ለህብርተሰቡ ማዳረስ አና የበኩላችንን አስተዋፆ ማድረግ ነው ። ስለዚህ ዛሬ  እስካሁን በብዛት በማህበራዊ ሚዲያ በስህተት አና ባለማወቅ በ ኮሮና ቫይረስ ዙሪያ አየተሰራጩ ያሉ የተዛቡ መረጃዎችን ለማስተካከል አንሞክራለን ።

የጤና ወግ የሚከተሉትን መረጃ የማረጋግጥ ምክሮች ትጠቁማለች 

መረጃዎን ከ ታመነ መንጭ ብቻ ይከታተሉ።

በዚህ በኮሮና ቫይርስ ዙሪያ ሁሉም ሰው የራሱን ሃሳብ ሊፅፍ ይችላል አርስዎ ግን ከጤና ጥበቃ አና ከተመረጡ ትክክለኛ ምንጮች ብቻ ዜናዎን ያግኙ

ለሌሎች የሚያጋሩትን መረጃ ከመላክዎ በፊት አውነታኛነቱን ያረጋግጡ ።

ከብዙ ያልተረጋገጠ ዜና ይልቅ የሚያምኑት ጥቂት ተዓማኒ የመረጃ ምንጭ ይበቃዎታል ።

ሰበር ዜና ማካፈልን ልምድ ላለችው ጋዜጠኞች ይተዉ ።  

ሁሌም ጥያቄ ካላቹ አድርሱን። ምንም ነገር ያለ ጥናት አና ማስረጃ አናጋራችሁም ። አላማችን በህክምና ትምህርት ውስጥ መረጃ የመጠቀም ባህልን ማዳበር ነው ።