የእርስዎንና የኩላሊትዎን ጤና አጠባበቅ

Source : The National Kidney Foundation.

የሰውነትዎን አካላት ስራቸውን በሚገባ እንዲያከናውኑ መምረጥ የርስዎ ፋንታ ነው። ሰውነትዎ ጤናማና ጠንካራ እንዲሆን እንዴት ሊረዱት ይችላሉ?

የአመጋገብ ስርአት

የአካልዎ ጤንነት እንደሚመገቡት ምግብና እንደሚወስዱት መጠጥ ይወሰናል። ፍራፍሬዎችን፣ አትክልት፣ ዳቦ፣ ስጋና የወተት ተዋጽኦችን አመጣጥነው ይውሰዱ። የኩላሊት ህመም ካለብዎት ኩላሊትዎ ንጥረነገሮችን መመጠን ስለሚያስፈልገው እንደ ጨውና ፖታሲየም ያላቹውን ምግቦች መጠን መቀነስ ሊኖርቦት ይችላል። ። ሃኪምዎን በማማከር አመጋገብዎን ያስተካክሉ።

የሰውነት እንቅስቃሴ

ሰውነትዎ መሮጥ መዝለልና መጫወት ይፈልጋል። የሰውነት እንቅስቃሴ ማድረግ ጥሩና ጤናማ አቋም ለማድረግ ይረዳል። በቂ እንቅስቃሴ በማድረግ ለሰውነትዎ ውጫዊና ውስጣዊ ጥንካሬ ይጠቅማል።

መድሃኒቶች

ሃኪምዎ ወይም ወላጆች (ለህጻናት) የሰጡትን መድሃኒት ብቻ ይውሰዱ።በምንም አይነት መድሃኒቶችን ከሌላ ሰው ጋር አይጋሩ። የአንድ ሰው አካል ክሌላኛው ሰው አካል በፍጹም ሙሉ በሙሉ አንዳይነት ሊሆን አይችልም። ሃኪሞች እንደሰውነታችን ሁነታ የተለያየ መድሃኒት ስለሚሰጡን የተሰጠዎትን መድሃኒት ሃኪሙ ባዘዘው መሰረት ይውሰዱ።

የአልኮል መጠጥና እጽ (ሃሽሽ?)

ሲጋራ፣አልኮል መጠጦች፣ሃሺሽና ሌሎች እጾች ለሰውነት ጎጂ ናቸው። በተለይ የኩላሊት ህመም ካለብዎት ወደ ሰውነትዎ ውስጥ ምን እንደምያስገቡ ጥንቃቄ ማድረግ አልብዎት። የታመሙ ኩላሊትትዎች ደም በሚገባ ማጣራት አይችሉም።

 መጠጥና የተለያዩ እጾችን አልወስድም የማለት ምርጫው የርስዎ እንደሆነ አይዘንጉ።

Source : The National Kidney Foundation.

ይህን የጤና መረጃ ከአሜሪካን የኩላሊት ህክምና ማህበር ድረ ገፅ ላይ ምንጭ አድርገን ስናቀርብ ፅሁፉን በመተርጎም የ ተባበረችንን ሄዋን አለማየሁን  ( Twitter: @Hewanoch ከልብ እናመሰግናለን ።

If you want to read the original article in English please Click here.