ለበሽታው መከሠት ዋና መንስኤዎቹ ምንድን ናቸው?
Tweet
ድንገተኛ የኩላሊት ጉዳት አንደ ስሙ በ አጣዳፊ ሁኔታ የሚከሰት የኩላሊት ህመም ነው። ጉዳቱ በደማችን ውስጥ በሚኖር የተረፈ ምርት ክምችት ምክንያት የሚከሠት ሲሆን ኩላሊት ትክክለኛ የፈሳሽ ማጣራት ተግባሩን እንዳያከናውን ያደርገዋል። ይህ በሽታ እንደ ልብ፣ ሳንባ እና አእምሮ የመሳሰሉትን የሠውነት አካሎች ይጎዳል። ተግቢውን ሕክምና ካገኘ አና ምክንያቶቹ ከተስተካከሉ አጣዳፊ /ድንገተኛ የ ኩላሊት ህመም ብዙ ጊዜ የመዳን አድል አለው ።
የድንገተኛ የኩላሊት ጉዳት ምልክቶች ምንድን ናቸው?
• የሽንት መጠን መቀነስ
• የሠውነት እብጠት በተለይ አግር አና አይናችን አከባቢ
• ከፍተኛ የሆነ የመዛል እና የድካም ስሜት
• የማዞር ስሜት
• የትንፋሽ ማጠር
• አንዳንድ ጊዜ ድንገተኛ የኩላሊት ህመም ምንም አይነት ምልክቶችን በህመምተኛው ላይ ሳያሳይ በሆስፒታል ውስጥ በሚደረግለት ምርመራ ሊታወቅ ይችላል።
ለበሽታው መከሠት ዋና መንስኤዎቹ ምንድን ናቸው?
1. ወደ ኩላሊት የሚሄደው ደም ማነስ
አንዳንድ በሽታዎች እና ሁኔታዎች ወደ ኩላሊት የሚሄደውን የደም መጠን ሊቀንሡት ይችላሉ። ለምሳሌ:-
•በጣም ዝቅ ያለ የደም ግፊት
• በተለያየ ምክንያት የሚከሠት በሠውነታችን ውስጥ ያለ ደም ወይም ፈሳሽ ማነስ (በደም መፍሠስ ወይም አንደ ተቅማጥ ያሉ በሽታዎች …)
• አንዳንድ የሠውነት ክፍሎች በአግባቡ አለመስራት (ልብ፣ ጉበት)
• የልብ ህመም
• የተላያዩ መድሃኒቶችን ከመጠን በላይ መጠቀም ( ለምሳሌ የ ህመም ማስታገሻ መድኃኒቶች NSAIDs-ዲክሎፈናክ አይቡፕሮፌን )
2. ኩላለት ላይ የሚኖር ቀጥተኛ ጉዳት
አንዳንድ መድኃኒቶች ፣ ከተለያዩ የ ካንሰር ህመሞች ጋር ተያይዞ ፣ ከፍተኛ ኢንፌክሽን …
3. የሽንት ቧንቧ መዘጋት
• የ ፕሮስቴት እና የ ስርቫይካል (ማህፀን በር ) ካንሰር
• የፕሮስቴት እጢ ማደግ በተለይ በ አዋቂ ወንዶች ላይ
• የኩላሊት ጠጠር
ድንገተኛ የኩላሊት ጉዳት እንዳለ ለማወቅ የሚረዱ ምርመራዎች ምንድን ናቸው?
በተቻለ መጠን ድንገተኛ የኩላሊት ጉዳት ቶሎ ቢታወቅ መልካም ነው። ምክንያቱም በአግባቡ ካልታከመ ለረጅም ጊዜ የኩላሊት ጉዳት ብሎም ለልብ ህመም እና ሞት ሊያጋልጥ ይችላል። አንድ ታካሚ የኩላሊቱን ጤንነት ለማረጋገጥ የሚከተሉት ምርመራዎች ይታዘዙለታል።
1. የሽንት ምርመራ: በሽንት ውስጥ ደም ወይም ፕሮቲን እንዳለ ለማረጋገጥ ይረዳል። ይህም የድንገተኛ የኩላሊት ህመም ካለ
ለማወቅ ይረዳል።
2. የሽንት ፍሠቱ ምን ያህል እንደሆነ ለማወቅ የሚደረግ ምርመራ
3. የደም ምርመራ: በደም ውስጥ የሚገኘውን የክሪአቲኒን መጠንን / ጂ.ኤፍ.አር (ኩላሊት በደቂቃ ምን ያህል ቆሻሻ ማጣራት እንደሚችል) ለማወቅ ይረዳል።
4. ከኩላሊትዎ ላይ በተለየ መርፌ ከሚወሰድ እና በማይክሮስኮፕ በሚመረመር ናሙና (Kidney Biopsy )
ለድንገተኛ የኩላሊት ጉዳት የሚደረገው ህክምና አብዛኛውን ጊዜ ህመምተኛውን በህክምና ስፍራ ላይ እንዲቆይ ያስገድዳል። በሆስፒታል ውስጥ ምን ያህል ይቆያል የሚለው ነገር ህመሙን ካመጣው መንስኤ እና ኩላሊቱስ በምን ያህል ፍጥነት ወደ ስራው ይመለሳል የሚሉት ነገሮች ላይ ይወሠናል። ህመምተኛው አስጊ ደረጃ ላይ ከሆነ በህክምና ባለሙያዎች ድያሊሲስ እንዲያደርግ ሊታዘዝለት ይችላል። ዲያሊሲስ በማሽን የሚደረግ የሠውነት ቆሻሻን የማጥራት ስራ ነው።
በድንገተኛ የኩላሊት ጉዳት ከተጠቁ በኋላ በሌሎች ተያያዥ ህመሞችን የመጠቃት እድል በጣም ከፍተኛ ነው።
ራሳችንን ከዚህ ጉዳት ለመከላከል የሐኪምን ምክር መከተል ፣ የኩላሊት ተግባርን ለመላካት የሚጠቅሙ ምርመራዎችን ማድረግ እና በተቻለ መጠን ራስን ለድንገተኛ የኩላሊት ጉዳት ከሚዳርጉ ነገሮች ማራቅ ይገባል ።
በ ሃይማኖት ግርማ
በቅዱስ ጳውሎስ ሕክምና ኮሌጅ 4 ተኛ አመት ተማሪ
ትዊተር @Haymana_ or Telegram channel https://t.me/G_hayma
ምንጭ National Kidney Foundation