Written by ሲ/ር መቅደላዊት ወርቁ (ነርስ፣ በዳግማዊ ምኒልክ ህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የኤምፒኤች ጤና አገልግሎት አስተዳደር የ2ኛ ዓመት ተማሪ፣እና የ4ኛ ዓመት የኢኮኖሚክስ ተማሪ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ንግድ ስራ ኮሌጅ ) Sr. Mekdelawit Worku,BSC Nurse, 2nd year MPH in Health Service Management student at Menelik II Medical and Health Science College, and 4th year Economics student at Addis Ababa University School of Commerce

Reviewed by Dr. Mahlet Mitiku (Internist)

የስኳር ህመም አመጋገብ

የስኳር ህመምተኞች ማድረግ ያለባቸው ነገሮች

  1. በሳምንት ሶስት (3) ቀናት ቢያንስ 150 ደቂቃ (ለ 2፡30) መጠነኛ የሆነ (moderate intensity) እንቅስቃሴ ወይም ቢያንስ  ለ 75 ደቂቃ ከፍተኛ የሆነ (moderate intensity)እንቅስቃሴ  ማድረግ :: 
  2. የሰውነት ክብደትን መቆጣጠር 
  3. በእያንዳንዱ የምግብ አይነቶች የጨው መጠንን መቀነስ 

 

በትክክለኛው መጠንና በጥንቃቄ መወሰድ የሚችሉ የምግብ አይነቶች

  1. ከእህል ዘር ስንዴ፣ ሩዝ፣ የአትክልት ሾርባ
  2. የስራ ስር ስር ቆጮ፣ ቡላ፣ የመሣሠሉት

የስኳር መጠን በሚቀንስ ወቅት ብቻ መወሰድ ያለባቸው ምግቦች

  1. ስኳር፣ ማር፣ ከረሜላ፣ ብስኩት፤ ቴምር፤ ማርማላታ፣ ቸኮሌት፣ ኬክና ሌሎች ስኳር ነክ ምግቦች
  2. የለስላሳ መጠጦች

ፈፅሞ የተከለከለ

  1. የአልኮል መጠጦች ለምሳሌ ውስኪ፣ ቢራ፤ አረቄ፣ ጠጅ፣ጠላ
  2. ሲጋራ ማጨስ
  3. የታሸጉ ምግቦች እና መጠጦች 
  4. ሌሎች አደንዛዥ ዕፆች

ማሣሠቢያ

ለእርሶ በተለየ የሚስማማዎትን የአመጋገብ ዘዴ ከሐኪም በመጠየቅ ይረዱ በተለይም ከስኳር ህመም በተጨማሪ ሌላ ህመም አንደ ደም ግፊት የሪህ በሽታ የልብ ህመም የጉበት ካለዎት በአመጋገብ በኩል መውሰድ ስለሚያስፈልገዎ ተጨማሪ ጥንቃቄ ሐኪምዎን ያማክሩ፡፡ ስኳር ህመምተኛ በተለመደው ሰዓት ሁሌም መመገብ ይሮርበታል እንዲሁም በደም ውስጥ የስኳር መጠን መቀነስ ወይም ማነስ (Hypoglycemia) ምልክቶችን ጠንቅቆ ማወቅ እና ተገቢውን እርምጃ መውሰድ ያስፈልግዎታል!

 

በተወሰነ ቀናት ልዩነት የሚወጉበትን ቦታ መቀየር አለቦት፡፡ 

በተደጋጋሚ አንድ ቦታ መውጋት መድሀኒቱ የሚፈለገውን ወጤት አንዳያመጣ ሊያደርግ ይችላል፡፡እንዲሁም የሚወጉበትን ቦታ የቆዳ መደደር እና የቀለም ለውጥ ያመጣል፡፡ 

የኢንሱሊን መርፌዎን በየ2 እስከ 3 ቀኑ መቀየር ይኖርቦታል፡፡  

 

FOOT CARE FOR PEOPLE WITH DIABETES 

የስኳር ታካሚዎች የእግር እንክብካቤ ማሳያ

 

እግሮትን በንፁህ ውሀ በየቀኑ ይታጠቡ፡፡

እግሮትን በደንብ ያድርቁ፡፡ በተለይ ጣቶት መሀል፡፡

የቆዳዎትን ልስላሴ ይጠብቁ፡፡ ነገር ግን የሚቀቡትን ማለስለሻ በእግር ጣቶች መካከል አይጠቀሙ፡፡

በየቀኑ እግሮትን በጥንቃቄ ይመልከቱ፡፡አብጠት ጠባሳካለ ለሐኪሞት ያሳውቁ፡፡

የእግሮትን ጥፍር እንዴት መንከባከብ እንዳለቦት ሀኪሞን ያማክሩ ፡፡

ንፁህ ለስላሳ እና የማይዞትን ካልሲ ይጠቀሙ፡፡

ሁልጊዜ እግሮት ደረቅ መሆኑን እና የጫማዎት መጠን ትክክል መሆኑን ያረጋግጡ፡፡ 

በፍፁም በባዶ እግሮ አይሂዱ፡፡

ሁልግዜ ጫማዎትን ከማድረጎ በፊት በጥንቃቄ ይመልከቱ፡፡