ዶ/ር ብሩክ አለማየሁ (የውስጥ ደዌ ስፒሻሊስት)
1.rRT-PCR (real time Reverse Transcriptase Polymerase Chain Reaction)
- .rRT-PCR (real time Reverse Transcriptase Polymerase Chain Reaction)
- ይህ ምርመራ የቫይረሱን ዘረ-መል (genetic material) በመለየት ቀጥተኛ በሆነ መንገድ የቫይረሱን መኖር ያረጋግጣል፡፡
- ኮቪድ19ን ጨምሮ ሌሎች መሰል ቫይረሶችን ለመመርመር የምንጠቀምበት ዋነኛ ምርመራ ይህ ነው፡፡ በአገራችንም የምንጠቀመው ይህንን ምርመራ ነው።
- የሚወሰደው ናሙና፡
- ከአፍንጫ፣ ጉሮሮ
- አክታ፣ ከመተንፈሻ አካል ከሚወጡ ፈሳሾች (secretions)፣ በብሮንኮስኮፒ ከሚወሰዱ ናሙናዎች (BAL)
- ደም፣ ሰገራ፣ ሽንትና ሌሎችም የሰውነት ፈሳሾች
- ውጤት የሚደርሰው፡ በትንሹ 24 ሰዓት ነገር ግን እስከ 48 ሰዓትና ከዚያም በላይ ሊወስድ ይችላል፡፡
GeneXpert (Xpert/Xpress SARS-CoV-2)
- GeneXpert (Xpert/Xpress SARS-CoV-2)
- አዲስና በዚህ ሳምንት ከ አሜሪካ የምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን (FDA) ልዩ አስቸኳይ ፈቃድ ያገኘ ምርመራ ነው፡፡
- ይህም ምርመራ የቫይረሱን ዘረ-መል የሚለይ ነው፡፡
- ውጤት የሚደርሰው፡ የተሻለ ፈጣንና ውጤቱ በ45 ደቂቃ ውስጥ አስተማማኝ በሆነ ደረጃ የሚታወቅ መሆኑን አምራቹ (Cepheid) ገልፅዋል፡፡
- ነገር ግን ገና አዲስና ገና እስካሁን ያልተጠቀምነው ከመሆኑ አንጻር ስለዚህ ምርመራ ብዙ መናገር አይቻልም፡፡
- የዚህ ዓይነት ምርመራዊች ቲቢን እና ሌሎችንም በሽታዎች ለመለየት በዓለም ዙርያ በጥቅም ላይ የዋሉና ጥሩ ውጤት ያሳዩ ከመሆናቸው አንጻር ሲታይ ተስፋ ሰጪ ነው፡፡
Serologic (Antibody) Test
- Serologic (Antibody) Test
- ይህ ምርመራ ሰውነታችን ቫይረሱን ለመዋጋት የሚያመርተውን ኬሚካል (አንቲቦዲ) በመመርመር በተዘዋዋሪ መንገድ ቫይረሱ በሰውነታችን ውስጥ እንዳለ ወይም እንደነበር የሚነግረን ነው፡፡
- በዚህ መንገድ ኮቪደ19ን ለመመርመር ግን ሁለት ችግሮች አሉ፡-
- እስካሁን ባለው መረጃ መሰረት እነዚህ አንቲቦዲዎች (antibodies) በደማችን ውስጥ መታየት የሚጀምሩት ከ10ኛው ቀን ጀምሮ መሆኑ በሽታውን ቀድሞ ለማወቅ አያስችሉንም፡፡
- እስከዛሬ በተለይ ኮቪድ19ን ለመመርመር የተረጋገጠና ፈቃድ (Validation and Approval) ያገኘ የአንቲቦዲ ምርመራ አለመኖሩ ናቸው፡፡
Viral Culture & Sequencing
- Viral Culture & Sequencing
- ይህ ምርመራ በተለመደው የህክምና ሂደት ውስጥ ሳይሆን አብዛኛውን ጊዜ በጥናትና ምርምሮች ጊዜ የምንጠቀምበት ነው፡፡
- ናሙና ከተወሰደ በኋላ ለቫይረሱ እድገት በሚስማማ ህዋስ ውስጥ እንዲቀመጥ (innoculate) የሚደረግበትና የቫይረሱ መኖር አለመኖር የሚታይበት ነው፡፡
- በተጨማሪም ቫይረሱ ከተገኘ በኋላ ስለቫይረሱ አካላዊ፣ ዘረ-መላዊ እና ሌሎች ባህሪዎች ጥናት ለማድረግ እድል የሚሰጥ ነው፡፡
Sources
1. https://apps.who.int/iris/handle/10665/331329
2. https://www.cdc.gov/coronavirus/2019-ncov/lab/index.html
4. https://www.cepheid.com/coronavirus
5.http://www.slh.wisc.edu/clinical/diseases/covid-19/
6. Handbook of COVID-19 Preventionand Treatment; The First Affiliated Hospital, Zhejiang University School of Medicine
*Compiled According to Clinical Experience