እኛ ኢትዮጵ ቴክ የባህርዳር ዩኒቨርስቲ የ3ኛ አመት ተማሪዎች ስንሆን የኮሮና ቫይረስ ግንዛቤ ማስጨበጫ የሞባይል መተግበሪ ሰርተናል፡፡
ይህ መተግበሪያን በሁሉም አንድሮይድ ኦፕሬቲኝ ሲስተም ባላቸው ስልኮች በአማርኛ መጠቀም ያስችላል፡፡የምንጠቀመው ዳታቤዝ Real time ስለሆነ ሁልዜም የWHO ወይም የኢትዮጲያ ጤና ጥበቃ ሚኒስተር የሚወጡ ወቅታዊ መረጃዎችን ያቀርባል፡፡መተግበሪያውም ስለኮቪድ-19 የሚከተሉትን መረጃዎች ይዟል፦
ስለኮረና ቫይረሰ ምንነት፣
ምልክቶች ፣
መከላከያ ዘዴዎቸ፣
መተላለፊያ መነገዶች ፣
አለም አቀፋዊ አሃጉራዊ እና ሃገራዊ የኮቪድ-19 ስታስቲክስ
እንዲሁም በተደጋጋሚ የሚነሱ ጥያቄዎችን ሰፊ መረጃ(መልስ)
በተጨማሪም የጤና ጥበቃ ሚኒስተርና በተለያዩ ክልሎች በተዘጋጁት ቀጥታ የነጻ መስመር የስልክ ማእከሎች(ስልክ ቁጥሩን ማወቅ ሳይጠበቅብዎት ለመደዎል ያስችላል፡፡
ከላይ ለመግለጽ እንደሞከርነዉ መተግበሪያዉ በአማርኛ ብቻ ስለተሰራ በተለያዩ የኢትዮጲያ ቋነቋዎች ለመተርጎም(localized) lለማድረኛ፣ማየት እና ማንበበ ለማይችሉ በድምጽ የታገዘ መልክት ለማስተላለፍ ያሰችል ዘንድ ለማሻሻል እየተዘጋጀን እንገኛለን ።
……………………………………………………………………………………………….
በጤና ጥበቃ የሚነገረንን መግለጫዎች በአግባቡ እንከታተል።
ባለንበት ራሳችንን እንጠብቅ፡፡
የጤና ወግ
በመረጃ የተመሰረተ ሕክምና ብቻ ።
በጥናት የተደገፈ መረጃ ብቻ እናቀርባለን።
የህክምና ባለሙያዎች ለህሙማኖቻችሁ የሚሆን የሚነበብ መረጃ ከፈለጋችሁ ይህን ግፅ ጠቁሟቸው። ህሙማኖቻችሁ እንዲያውቁት የምትፈልጉትን ነገር መረጃ ጠቅሳችሁ ፃፉልን፣ ስምችሁን ጠቅሰን እናወጣለን። የህክምና ተማሪዎች እንዲጽፉ እናበረታታለን።
በተጨማሪም በጤና ወግ ፖድካስት፣ በ ዩትዩብ ፣በ ትዊተር ፣ በ ፌስቡክ ፣ በቴሌግራም የተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ ገፆቻችን ታገኙናላችሁ ።