በ አሁኑ ሰአት በአለም አቀፍ ደረጃ ትኩረት ሁሉ ወደ COVID19 ዞሯል። የህክምና ተቋማትም ይህን የመጣውን ፈተና ለመቋቋም የተለያዩ ጥረቶች ን እያረጉ ይገኛሉ። ዋናው የ COVID19 ወረርሽኝ ሲሆን ሌላውና ከዚህ ከወረርሽኝ ባልተናነሰ መልኩ ከባድ ፈተና ከ COVID19 ውጪ ያሉ ህመምተኞች ክትትል ነው፡፡ አብዛኛው ትኩረት ወደ COVID19 መሆኑ ሌሎች አገልግሎቶች ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ተጽእኖዎች ፈጥራል ።
በ 2015 የተሰራ ጥናት እንደሚያሳየው እንደዚህ አይነት Pandemic በሚፈጠሩበት ሰዓት – ሰዎች በ ተላልፊ በሽታው ላለመያዝ ባላቸው ፍራቻ ወደ ሕክምና ተቋማት አይሄዱም ፣ ሆስፒታሎች በአዲስ በሽተኞች ይጣበባሉ ፣ የገንዘብ እና ሌሎች የህክምና ዕቃ መሳሪያዎች ለ ወረርሽኝ መቆጣጠሪያ ይውላሉ -ይሄ ደግሞ የሌሎች ታካሚዎችን ክትትል በጣም ይጎዳዋል።
የህክምና ተቋማት ከድንገተኛ ህክምና ውጪ በጣም ብዛት ያለው አገልግሎት ይሰጣሉ ከነዚህም ውስጥ በጥቂቱ – የተመላላሽ ህክምና ፣ የክትትል ክፍል ፣የአስተኝቶ ማከም ፣ የቀዶጥገና ፣ የወሊድ፣ የክትባት አገልግሎት ከአብዣኛው ጥቂት ናቸው።
አሁን ባብዛኛው ሆስፒታሎች ውስጥ ወይም በሌሎች የጤና ጥቃማት እንዳየነው የታካሚው ቁጠር በጣም ቀንሷል። አብዛኛው ትኩረት ወደ COVID19 ወረርሽኝ መሆኑ ሌሎቹን አገልግሎቶች በጣም ያዳክመዋል።።
ለዚህም ምክንያት ብለን መጥቀስ የምንችላቸው
በ COVID19 የመያዝ ስጋት ነው፡፡ ስለዚህ እንደወትሮው ወደ ጤና ተቋማት ታካሚዎች አይመጡም።
ሌላኛው ምክንያት የህክምና ተቋማት ለወረርሽኝ ዥግጅት ሲባል አገልግሎት ያቆሙ ብዙ ክፍሎች መኖራቸው ናቸው፡፡
ለምሳሌ ያህል አዲስአበባ ውስጥ የሚገኙ አብዣኛው ሆስፒታሎች ድንገተኛ ያልሆኑ ቀዶ ጥገናዎችን ላልተወሰነ ጊዜ አቁመዋል፡፡
የተመላላሽ ህክምና ክፍሎች በቀን ውስጥ የሚያዩትን የታማሚ ቁጥር ገድበዋል።
የአስተኝቶ ማከም ክፍል ውስጥ ያሉ አልጋ ቁጥሮችን ቀንሰዋል። ይህም ከ COVID19 ውጪ ያሉ ህመምተኞች ተጋላጭነት ለመቀነስ በማሰብም ጭምር ነው፡፡
ከጤና ጣቢያዋች ጋር በመተባበር በቀድሞ ወደ ሆስፒታሎች ይላኩ የነበረ አላስፈላጊ ማለት እዛው ጤና ጣቢያዋች ውስጥ ሊታከሙ የሚችሉ ህመምተኞች ሪፈራል መቀነስ።
ከህመምትኛ መቀነስ ውጭ የሰው ሀይል በከፍተኛ ቁጥር መቀነስ በተለምዶ እነዚህ ክፍሎች ላይ ይውል የነበረው ባለሙያ ለወረርሽኝ በተዘጋጁ ቦታዎች ላይ ተመድቧል፡፡ ከጓንት ጀምሮ እስከ ventilator machine ድረስ አቅርቦት በከፍተኛ ሁኔታ ወደ ወረርሽኝ ትኩረት አንዲያደርግ አስገድዶታል፡፡
ሌላው በየግዜው በሀገር ውስጥ ሆነ በውጪ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች የሚደርጉ የነበሩ እርዳታዎች ትኩረት ሙሉለሙሉ ወደ ወረርሽን የመቆጣጠር ሥራ መዞር ነው፡፡
በህክምና ተቋማት ውስጥ የታማሚ አለመምጣት የሚያመጡት ችግሮች
በአብዛኛው ከ COVID19 ውጪ ያሉ ህመምተኞ ስንል ለምሳሌ እንደ (የስኳር ህመም ፣ የደም ግፊት፣ የልብ ህመም ፣ የካንሰር ፣ የኩላሊት ፣ የHIV የTB እና የመሳሰሉት በሽታ ያለባቸውን ሰዎች ያጠቃልላል።
ከነዚህም በተጨማሪ የወሊድ የህፃናት የክትባት አገልግሎት ይገኙበታል፡፡
የነዚህ የህክምና አግልግሎት ፈላጊዎች ወደ ሆስፒታል እና ሌሎች ሕክምና ተቃማት አለመምጣት የሚያስከትሉትን ችግሮች ምሳሌ ወስደን ብናይ፣ ለምሳሌ በ 2014 በ ምዕራብ አፍሪካ የተነሳው የ ኢቦላ ወረርሽኝ ቀጥታ ካመጣው ሞት በተጨማሪ ወደ 11,300 ሰዎች የህክምና ክትትል በማጣት ሞተዋል። በነዚህ ሃገራት ያለው የክትባት ስርጭት መጠን ከ 30% በላይ መቀነሱ ታይቷል።
የስኳር እና የደም ግፊት ህመምተኞች በየጊዜው ክትትል ካላደረጉ የስኳር እና የደም ግፊት መጠናቸውን በአግባቡ ላይቆጣጠሩ ይችላሉ። ያም አደገኛ ለሆኑ እንደ ስትሮክ እና የድንገተኛ የልብ አደጋ አልፎም ለሞት ሊዳረጉ ይችላሉ፡፡
ተገቢውን የወሊድ ክትትል አለማድረግ.እናቶች በወሊድ ጊዜ የሚገጥማቸውን ችግሮች በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራል፡፡
የልጆች በጊዜው ክትባት አለማግኘት ለብዙ ህመሞች ተጋላጭ ያደርጋቸዋል፡፡
የ HIV ህመምተኞች መድሀኒቶቻቸውን ማቋረጥ ወይም በአግባቡ አለመውሰድ የ HIV የበሽታ መከላከልን አቅምን መቀነስ ተጓዳኝ አድርገው ለሚመጡ ብዙ በሽታዎች ይጋለጣሉ፡፡
በሀገራችን በዚህ ሰዓት ይህ እንዳይፈጠር ምን ማድረግ እንችላለን
በአቅራቢያዎቻችን ያሉ ጤና ጣቢያዋች የቆየ ህመም ያለባቸውን ታካሚዎቻቸውን በስልክ ከሀኪም ምክር እና ክትትል የሚያገኙበት አሰራር መዘርጋት።
በዚህ ረገድ ለምሳሌ እንደ ጥቁር አንበሳ ባሉ አንዳንድ መዲናችን ውስጥ ያሉ ሆስፒታሎች በተለያዩ ክትትል ክፍሎች የስልክ መስመር ተዘጋጅቶ ታካሚዎች እየደወሉ ሕክምናቸውን እንዲያገኙ ተደርጓል።
መድኃኒቶችን ረዘም ላለ ጊዜ ማዘዝ ፣ ታካሚዎች በየወሩ ከመመላልለስ ያድናቸዋል።
ታካሚዎች በራሳቸው ቤታቸው ውስጥ የደም ግፊታቸውን እና የስኳር መጠናቸውን እንዲለኩ ትምህርት መስጠት።
ከ COVID -19 ውጭ ያሉ ታካሚዎች ለብቻ አገልግሎት የሚያገኙባቸውን ተቋማት መለየት።
በአሁኑ ሰዐት ለተማሪዎች ዝግ የሆኑ ትምህርት ቤቶችን ሙሉ በሙሉ ወረርሽኝ ለመከላከል የሚችሉ ተቋማትን ማድረግ
ለነዚህ መፍትሄዎች በዚህ ሰዓት ከፍተኛ አስተዋጾ ሊኖረው የሚችለው ድርጅት የኢትዮጲያ ቴሌኮሚኒኬሽን ነው፡፡
ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በየተቋሟቱ ለጊዜው ከክፍያ ነጻ የሆኑ ስልኮችን ማዘጋጀት
በዚህ አጋጣሚ ይህ ጊዜ አልፎ ነገሮች ሲስተካከሉ በቀላል ክፍያ በማድረግ ብዙም አስፈላጊ ሳይሆን ወደ በጤና ተቋሟት የሚመጡ የነበሩ ህመምተኞችን በስልክ ከባለሙያዎች ጋር ማገናኘት ይቻላል፡፡
እነዚህን ስልኮች ማንኛውም ሰዉ ቤት ውስጥ ሆኖ የሀኪም ምክር ሲያስፈልገው እንዲሁም ድንገተኛ የህክምና ችግሮች ሲገጥሙት መጠቀም ይችላል፡፡
በዚህ ርዕስ ላይ በጤና ወግ ፖድካስታችን ላይ ያደረግነውን ውይይት ለማዳመጥ ከስር ያለውን ሊንክ ይጫኑ
የጤና ወግ
በመረጃ የተመሰረተ ሕክምና ብቻ ።
………………………………………………………………………………………………………………………..
ይህ የጤና ወግ ድረ ገፅ ነው።
ስለ ጤንነታችሁ ማወቅ የምትፈልጉትን መረጃ የምታገኙበት ፣ በህክምና ባለሙያዎች የሚዘጋጅ የመረጃ ምንጭ ነው።
ሁልግዜም ከሀኪማችሁ ተማከሩ፣ ተጨማሪ መረጃ ከፈለጋችሁ የኛን ድረ ገፅ ጎብኙ።
በጥናት የተደገፈ መረጃ ብቻ እናቀርባለን።
የህክምና ባለሙያዎች ለህሙማኖቻችሁ የሚሆን የሚነበብ መረጃ ከፈለጋችሁ ይህን ግፅ ጠቁሟቸው። ህሙማኖቻችሁ እንዲያውቁት የምትፈልጉትን ነገር መረጃ ጠቅሳችሁ ፃፉልን፣ ስምችሁን ጠቅሰን እናወጣለን። የህክምና ተማሪዎች እንዲጽፉ እናበረታታለን።
በተጨማሪም በጤና ወግ ፖድካስት፣ በ ዩትዩብ ፣በ ትዊተር ፣ በ ፌስቡክ ፣ በቴሌግራም የተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ ገፆቻችን ታገኙናላችሁ ።