እንደ ኮሮና ቫይረስ ያሉ ወረርሽኞች በሚነሱበት ጊዜ ቀጥተኛ ጉዳታቸው ብዙ ነው ። በ ሚድል ኤጅስ ዘመን (Middle Ages ) የተነሳው ጥቁር ሞት (Black Death ) ከ 30-50 ሚልየን ሰዎች እንደሞቱ ይገመታል። በቅርብ ደግሞ የ HIV pandemic ምክንያት ከ1981 ጀምሮ ከ35 ሚልየን በላይ ሰዎች ሞተዋል። የኮሮና ቫይረስም አሁን በአለም ላይ ከአንድ ሚልየን በላይ ሰዎችን ይዟል። እና ከ 50000 በላይ ሰዎች ደግሞ ለሞት ተዳርገዋል። የኢኮኖሚ ጉዳቱ ደግሞ በጣም ከፍተኛ ነው። አሁን ማንሳት የፈለግነው ደግሞ በዚህ ወረርሽኝ ምክንያት እንዴት ሌሎች ዘላቂ ህመም ያላቸው ሰዎች በ ክትትል ማነስ ሊጎዱ እንደሚችሉ ነው። በ 2015 የተሰራ ጥናት እንደሚያሳየው ሰዎች በ ተላልፊ በሽታው ላለመያዝ ባላቸው ፍራቻ ፣ በ ሆስፒታሎች በአዲስ በሽተኞች መጣበብ ፣ የገንዘብ እና ሌሎች የህክምና ዕቃ መሳሪያዎች ለ ወረርሽኝ መቆጣጠሪያ መዋላቸው የ አነዚህን ህመምተኞች ሕክምና በጣም ይጎዳዋል። ለምሳሌ በ 2014 በ ምዕራብ አፍሪካ የተነሳው የ ኢቦላ ወረርሽኝ ቀጥታ ካመጣው ሞት በተጨማሪ ወደ 11,300 ሰዎች የህክምና ክትትል በማጣት ሞተዋል። በነዚህ ሃገራት ያለው የክትባት ስርጭት መጠን ከ 30% በላይ መቀነሱ ታይቷል። ስለዚህ እነዚህ ተጨማሪ ህመም ያላቸው ሰዎች ሕክምናቸውን የሚያገኙበት መንገድ መመቻቸት አለበት። የተለያዩ የህክምና ተቋማት ይሄንን ክፍተት ለመሙላት ምን እያደረጉ እንደሆነ በዚች አጭር የጤና ወግ ውይይታችን እናያለን ። በ ኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ሌላ ዘላቂ የሆነ የጤና ያለባቸው ሰዎች ሕክምና እንዳይቃረጥ መስራት አለብን Listen Here --- Send in a voice message: https://anchor.fm/yetenaweg/message
27 minOn our Episode today we will discuss #COVID19Ethiopia, Dr. Belete an expert on Viruses at NIH and Dr.Ermias a Pulmonary and Critical care fellow at Cornell will answer your questions about #COVID19Ethiopia. How it is transmitted, Is it Airborne? Who needs to wear masks? What are the common symptoms ? What is the clinical course when you get the virus? What treatment options are available? What are on the pipeline? Any Vaccines? How Clinate affects transmission of the virus in Africa? What human behaviors contribute to emergence of new viruses? How is #COVID19 affecting you individually and how are you coping with it? #COVID19Ethiopia #StayHome በዛሬው ፕሮግራማችን ዶ/ር በለጠን (የቫይረስ ጥናት ስፔሺያሊስት) ጋብዘን ተወያይተናል። ማስክ ማን መጠቀም አለበት? ምን መድኃኒቶች አሉ ?ክትባት ይኖር ይሆን በቅርብ? ምን አይነት ምርመራ ነው የሚደረገው? ላብራቶሪ ውጤቱ ሁልግዜ ልክ ነው ወይስ ሊሳሳት ይችላል? እና የመሳሰሉትን ጥያቆዎች መልሰናል ። Listen Here --- Send in a voice message: https://anchor.fm/yetenaweg/message
1 hr 36 minየዚህ ክፍል የሴቶች ጤና ውይይታችንን ዶ/ር ኤልሳቤጥ አሳረ እና ዶ/ር ማክዳ ካህሳይ ይመሩታል። ስለጡት ካንሰር እና ማህፀን በር ካንሰር ምልክቶች፣ የትኞቹ ሴቶች ለዚህ ካንሰር የበለጠ ተጋላጭ እንደሆኑ ፣ ምን ምርመራ እና ቅድመ ምርመራ እንደሚይስፈልገን እና ህክምናውስ ምን ይመስላል የሚሉት ርዕሶች ላይ ይወያያሉ። ዶ/ር ኤልሳቤጥ አሳረ በ በኒውዮርክ የሪችመንድ ዩኒቨርሲቲ የውስጥ ደዌ ህክምና ስፔሻሊስት ሬዚደንት ሀኪም ናት ። እና ዶ/ር ማክዳ ካህሳይ ደግሞ በኒውዮርክ ማውንት ሳይናይ ሆስፒታል የውስጥ ደዌ ህክምና ስፔሻሊስት ሬዚደንት ሀኪም ናት። Listen Here --- --- Send in a voice message: https://anchor.fm/yetenaweg/message
21 minበዚህ የጤና ወጋችን ስለ አዲሱ የኮሮና ቫይረስ COVID19 እንወያያለን ። የኮሮና ቫይረስ ምልክቶች ምንድናቸው? ከጉንፋን እና ከኢንፍሉዬንዛ በምን እንለየዋለን ? የተለያዩ በማህበራዊ ሚዲያ ከኮሮና ቫይረስ ጋር የተሰራጩ ትክክል ያልሆኑ መረጃዋችን አንድ በአንድ እያነሳን እንወያያለን። የማህበራዊ መራራቅ ስንል ምን ማለታችን ነው ?እንዴት ነው የበሽታውን ስርጭት የሚቀንሰው ? ከእያንዳዳችን ምን ይጠበቃል? እነዚህና ሌሌች ሀሳቦችን አንስተን እንወያያለን። Listen Here --- Send in a voice message: https://anchor.fm/yetenaweg/message
39 minበዚህ የጤና ወጋችን ስለ እንቅልፍ እንወያያለን። በእንቅልፍ ሰአት ሰውነታችን ከመታደሱ በላይ ለሰውነት (በተለይ ለህፃናት) እድገት ቁልፍ የሆኑ ሆርሞኖች የሚመነጩበት ሰአት እንደሆኑ ያውቃሉ? የእንቅልፍ ማጣት እና የእንቅልፍ ማነስ ምንድናቸው? እንዴት ይታከማል? ምን ማድረግ ይገባናል? የእንቅልፍ ማጣት ለደም ግፊት ፣ ለስኳር ህመም ፣ ለሰውነት ከልክ በላይ ውፍረት ለካንሰር ህመም እንደሚያጋልጥ ያውቃሉ ? አልኮል ከመኝታ ሰአት በፊት መውሰድ እንዴት የእንቅልፍ ስረአትን እንደሚያዛባ ለመረዳት እና ሎችንም ጠቃሚ ነጥቦች ለመረዳት ይህን ወግ ያዳምጡ። Listen Here --- Send in a voice message: https://anchor.fm/yetenaweg/message
54 minበዚህ የጤና ወጋችን ፣ የደም ግፊት በምን ምክንያት ይከሰታል? የደም ግፊት እንዳለብን በምን እናውቃለን ? የደም ግፊት በቤተሰብ ይተላለፋል ወይ? ደም ግፊታችን ስንለካ ማድረግ ያለብን ጥንቃቄዎች ምንድናቸው? የደም ግፊት በምን ይታከማል? መድሃኒት ባቋርጥ ምን ችግር አለው ?/መድሃኒቱን ለስንት ግዜ መውሰድ አለብኝ ? እና የመሳሰሉ ጥያቄዎችን እንመልሳለን ። ተጨማሪ ጥያቄ ካላችሁ በፌስ ቡክ እና ትዊተር ገፆቻችን አድርሱን በሚቀጥለው ፕሮግራማችን ላይ የቻልነውን ያህል እንመልሳለን። Listen Here --- Send in a voice message: https://anchor.fm/yetenaweg/message
50 minአዲሱ የኮሮና ቫይረስ (በአዲስ የሳይንስ ስሙ COVID-19) ፣ ከየት መጣ ?/ምን ምልክት አለው ?/ በብዛት በህመሙ የሚጠቁት ማናቸው ? በቫይረሱ ሲያዙ ለፀና ህመም ከዛም ባለፈ ለሞት የሚጋለጡት የትኞቹ ህሙማን ናቸው? በሽታው እንዳይዘን ምን ማድረግ አለብን ? በረራ ማቋረጥ የበሽታውን መስፋፋት ይገታዋል? ስለ እነዚህ ጥያቄዎች መልስ ለማግኘት ይህን የጤና ወጋችንን ተከታተሉን። ሌላ ጥያቄ ካላችሁ በተለያዩ የማህበራዊ ድረ ገፆቻችን ጥያቄይችሁን ላኩልን ፣ የቻልነውን ያህል በሚቀጥለው ወጋችን ለመመለስ እንሞክራለን ። Listen Here --- Send in a voice message: https://anchor.fm/yetenaweg/message
30 minየኮሌስትሮል መጠን መጨመር በአለም ላይ የልብ፣ የስትሮክ ፣የደም ዝውውር መቀንስ ህመምን ከሚያመጡ ምክንያቶች ዋነኛው እንደሆነ ያውቃሉ ? በዚህ የጤና ወጋችን የ ኬሌስትሮል መጨመር ህመም ምንድነው? በምን ምክንያት ይከሰታል? የትኞቹ ምግቦች የበለጠ ለ ኮሌስትሮል መጨመር ህመም ያጋልጣሉ? መቼ ነው የ ኮሌስትሮል መጠናችንን መመርመር ያለብን? የኬሌስትሮል መጨመር በምን ይታከማል? የሚሉትን ነጥቦች አንስተን እንወያይለን ።ሌላ ጥያቄ ካላችሁ በተለያዩ የማህበራዊ ድረ ገፆቻችን ጥያቄይችሁን ላኩልን ፣ የቻልነውን ያህል በሚቀጥለው ወጋችን ለመመለስ እንሞክራለን ። Listen Here --- Send in a voice message: https://anchor.fm/yetenaweg/message
22 min