በዶ/ር ትዕግስት ስለሺ (የውስጥ ደዌ እስፔሻሊስት እና የልብ ሰብ ስፔሻሊት ፌሎው)

በእርግዝና እና በወሊድ ወቅት ለህመም እና ብሎም ለህልፈተ ህይወት ከሚያጋልጡ ዋነኛ ምክንያቶች ውስጥ ከልብ ጋር የተያያዙ ህመሞች ተጠቃሽ ናቸው ፡፡ በአለበአመወደ 300,000 የሚጠጉ እናቶች በእርግዝና እና በወሊድ ተያያዥ ምክንያቶች ህይወታቸውን ያጣሉ፡፡ ከእነዚህ ውስጥ 75 በመቶ ያህሉ ከሰሀራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት ውስጥ የሚከሰቱ ናቸው ፡፡ የልብ ህመሞች ደግሞ ከእነዚህ ውስጥ 25 በመቶ የሚሆነውን ድርሻ ይይዛሉ ፡፡

 

በእርግዝና ወቅት በብዛት ከሚታዩ ህመሞች መካከል የደም ግፊት ከፍተኛ የሳምባ የደም ስር ግፊት የልብ ጡንቻ መድከም የዋናው የልብ የደም ቧንቧ መስፋት በተፈጥሮ የሚከሰቱ የልብ ክፍተቶችየቫልቭ (የልብ ውስጥ ማስተላለፊያ በሮች) ጥበት በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው ፡፡ ከእነዚህም መካከል ያልታከመ የቫልቭ ጥበት እና ከፍተኛ የሳምባ የደም ስር ግፊት በሀገራችን እና ከሰሀራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት በአብዛኛው የሚከሰቱ ሆነው ታይተዋል ፡፡

 

ከልብ ህመም ጋር ተያይዘው የሚመጡ እንደ የልብ ምት መዛባትየደም መርጋት እና የልብ ድካም የመሳሰሉት ጉዳቶች ከሌላው የማህበረሰቡ አካል በጣም በሚበልጥ ቁጥር በነሰጡር እናቶች ላይ ይከሰታሉ ፡፡ ይህም በእናት እና በጽንሱ ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ ከፍተኛ የሚባል ነው ፡፡ በጽንሱ ላይ ሊከሰቱ ሚችሉ ችግሮች መካከል ያለ ዜ መወለድ ያልተስተካከለ የጽንስ እድገት እና እናትየው ከምትወስዳቸው መድሀኒቶች ጋር ተያያዥነት ያላቸው የጎንዮሽ ጉዳቶች ዋነኞቹ ናቸው ፡፡

 

እናቶች የሚከተሉት ስሜቶች ማለትም ከፍተኛ የሆነ የድካም ስሜት የትንፋሽ መቆራረጥየሰውነት እብጠትፈጣን የሆነ የልብ ምት መሰማትየመሳሰሉት ከተሰማቸው ሀኪም ጋር በመቅረብ መመርመር እና መታከም ይኖርባቸዋል ፡፡

 

ከእርግዝና በፊት የሚታወቅ የልብ ህመም ያላቸው እናቶች ደግሞ ከማርገዛቸው በፊት ሀኪም ማማከር እና ቅድመ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርባቸዋል ፡፡ ይህም እርግዝና የሚከለከልባቸው እና በቅድመ እርግዝና ወቅት መስተካከል የሚችሉ ነገር ግን ባይታከሙ ከፍተኛ አደጋ በእናት እና በጽንሱ ላይ የሚያደርሱ ህመሞች በመኖራቸው ነው፡፡ እንደ ከፍተኛ የሳምባ የደም ስር ግፊትከፍተኛ ደረጃ የደረሰ የልብ ጡንቻዎች መድከም እና የልብ ቧንቧ መስፋት ያሉ ህመሞች በእናት እና በጽንሱ ላይ የሚያደርሱት የሞት እና የህመም አደጋ ከፍተኛ ስለሆነ እርግዝና ባይፈጠር ይመከራል ፡፡

 

በህክምና መስተካከል የሚችሉ እንደ የቫልቭ ጥበት ያሉ ህመሞች ከእርግዝና በፊት በመታከም የሚያደርሱትን የሞት እና የህመም ጉዳት መቀነስ በጣም አስፈላጊ መሆኑን መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ ከእነዚህ ውጪ ያሉት እና ባለሞያ ምክር መሰረት ማርገዝ እንደሚችሉ ያረጋገጡት እናቶች በጣም ቅርብ ክትትል ማድረግ ይኖርባቸዋል ፡፡   

 

  ያስታውሱ ፥

 የልብ ህመም የእናት ህይወት ላይም ሆነ የፅንስ ጤናማ እድገት ላይ ከፍተኛ አደጋ ሊፈጥር ስለሚችል  የህመሙ ምልክት ያላቸው ወይም የልብ ችግር እንዳለባቸው የተነገራቸው ሴቶች እርግዝና ከመፈጠሩ በፊት ሀኪም ዘንድ ቀርበው ምርመራ ማድረግ ይኖርባቸዋል።

 

ማጣቀሻዎች

 

  1. John Anthony, Ayesha Osman, Mahmoud U Sani. Valvular heart disease in pregnancy: Cardiovascular Africa Journal of Africa • Volume 27, No 2, March/April 2016

 

  1. David A Watkins1, Motshedisi Sebitloane2, Mark E Engel1, and Bongani M Mayosi. The burden of antenatal heart disease in South Africa: A systematic review: BMC Cardiovascular Disorders 2012, 12:23

 

  1.  Diana S.Wolfe, Afshan B. Hameed, Cynthia C. Taub, Ali N Zaidi, Anna E Bortnick: Addressing maternal mortality: the pregnant cardiac patient, Albert Einstein College of medicine and /Montefiore Medical Center, Bronx, NY,2018.
  1. Iris M. van Hagen, Sara A. Thorne, Nasser Taha, Ghada Youssef, Amro      Elnagar, Harald Gabriel, Yahia ElRakshy: Pregnancy Outcomes in Women With Rheumatic Mitral Valve Disease Results From the Registry of Pregnancy and Cardiac Disease Circulation. 2018;137: 806–816.
  2. Gizachew Assefa Tessema, Caroline O. Laurence, Yohannes Adama Melaku, Awoke, Misganaw, Sintayehu A. Woldie, Abiye Hiruye, et al: Trends and causes of maternal mortality in Ethiopia during 1990–2013: findings from the Global Burden of Diseases study 2013:BMC Public Health (2017) 17:160

 

  1. Tegene Legesse, Misrar Abdulahi, Anteneh Dirar: rends and causes of maternal mortality in Jimma specialized hospital, southwest Ethiopia: A matched case-control study: International Journal of Women’s Health 2017:9 307–313.

 

  1. Solomon Ali, Awoke Misganaw, Asnake Worku, Zelalaem Destaw, Legesse Negash, Abebe Bekele, et al: The Burden of cardiovascular diseases in Ethiopia from 1990 to 2017: evidence from the global burden of disease study: International Health 2020; 0: