Dr. Nuhamin Weinaferahu. Medical intern at Myungsung medical College.
Reviewer: Dr. Nafkot Girum ( Assistant professor of Dermatovenereology)
ሰውነታችን በሽታን በሚከላከልበት ሂደት ላይ ሳለ ጤናማ ሕዋሶችን ሊያጠቃ ይችላል:: ከእነዢህም ጤናማ ሕዋሶችን ውስጥ ሜላኖሳይት የሚባለውን ለቆዳ, ለፀጉር እና ለዐይን ቀለም የሚያመርቱ አካል ሲያጠቃ “ለምፅ” የሚባለውን በሽታ ያስከትላል::
ለምፅ በቤተሰብ ውስጥ ተመሳሳይ የሕክምና ታሪክ ባላቸው ወይም ሰውነት በሽታን በመከላከል ሂደት ላይ ሳለ ጤናማ ሕዋሶችን የሚጎዳ (autoimmune) በሽታዎች ባለባቸው ሰዎች ላይ ሊከሰት ይችላል ነገር ግን ብዙውን ጊዜ ይሄነው የሚባል ምክንያት ሳይኖርም ሲከሰት ይስተዋላል።
ምልክቶች
- በሽታው በማንኛውም የቆዳ አካባቢ ላይ ሊወጣ ይችላል ፣ ነገር ግን በአብዛኛው ጊዜ፡
- በፊት ፣ አንገት ፣ እጅ እና በቆዳ እጥፋቶች ላይ ይከሰታል።
- የተገለጡ የቆዳ ቦታዎች ለፀሀይ ቃጠሎ ይበልጥ ተጋላጭ ናቸው፡ ስለዚህ በፀሐይ ውስጥ ሲሆኑ የበለጠ ጥንቃቄ ማድረግ እና ከፍተኛ የፀሐይ መከላከያ (SPF) ያለው ክሬም/መድሃኒት መጠቀም አስፈላጊ ነው። ይህን ስንል ግን ከፀሀይ መራቅ አለብን ማለት አይደለም ምክንያቱም በአንዳንድ ሁኔታዎች ላይ የፀሀይ ተጋላጭነት ወይም ፎቶ ቴራፒ (phototherapy) መሻሻልን አሳይቷል።
- አንዳንድ ጊዜ የፀጉር ሥሮች ባሉበት (ለምሳሌ፡ የራስ ቆዳዎ) ላይ ሊዳብር ይችላል፡ የዚህን ጊዜ የተጎዳው አካባቢ ላይ ያለው ፀጉር ነጭ ወይም ግራጫ ሊሆን ይችላል።
- ለምፅ በቆዳዎ ላይ ድርቀት አይፈጥርም፡ ነገር ግን ንጣፎቹ አልፎ አልፎ ሊያሳክኩ ይችላሉ።
- ለምፅ ከዓይን ችግሮች ጋርም ሊዛመድ ይችላል፣
መንስኤዎች
ለምፅ አብዛኛው ጊዜ አካላችን እራሱን በራሱ ሲያጠቃ (autoimmune) የሚፈጠር በሽታ ነው።
ለምፅ በኢንፌክሽን የተከሰተ አይደለም ስለዚህም ከሰው ወደ ሰው አይተላልፍም ።
ምርመራ
ምርመራው ብዙውን ጊዜ የተጎዳውን አካል በመመልከት የሚደረግ ነው:: ተጨማሪ ካስፈለገ:
- የእንጨት መብራት (Woods lamp) በሚባል አልትራቫዮሌት (UV) መብራት ቆዳን በበለጠ ዝርዝር ለመመልከት ይጠቅማል።
- በጨለማ ክፍል ውስጥ መብራቱ ከቆዳው ከ10 እስከ 13ሴ.ሜ ርቀት ላይ ተይዞ ይመረመራል.።
- አስፈላጊም ከሆነ የቆዳ ናሙና እና የደም ምርመራዎች ሊታዘዙም ይችላሉ።
ሕክምና
በለምፅ ምክንያት የሚከሰቱትን ነጭ ሽፋኖች ምንም እንኳን መልካቸውን ለመቀነስ የሕክምና አማራጮች ቢኖሩም አብዛኛውን ጊዜ ረዘም ላለ ጊዜ የሚወሰዱ ናቸው ምክንያቱም በሽታው ምን ያህል ቆዳ እንደሚጎዳ ለመተንበይ ምንም መንገድ ስለሌለ::
- ሽፋኖቹ በአንጻራዊ ሁኔታ ትንሽ ከሆኑ የቆዳ ክሬም በመጠቀም መሸፈን ይቻላል።
- አንዳንድ ቀለሞችን ለመመለስ የስቴሮይድ (steroid) ክሬሞችን በቆዳው ላይ መጠቀም ይቻላል፣ ነገር ግን ለረጅም ጊዜ ጥቅም ላይ ከዋለ የቆዳ መለጠጥን እና መሳሳትን ያስከትላል።
- የስቴሮይድ ክሬሞች ካልሰሩ የፎቶ ቴራፒ (በብርሃን የሚደረግ ሕክምና) ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል።
- ሕክምናው የሁኔታውን መሰራጨት ማቆም አይችልም።
- በብርሃን ሕክምና ወይም በመድኃኒቶች ለአላገገሙ ወይም የተሻለ ለውጥ ለአላመጡ የለምጽ በሽተኞች የተለያዩ የቀዶ ሕክምና አማራጮች አሉ።
References
- https://www.nhs.uk/conditions/vitiligo/
- https://www.niams.nih.gov/health-topics/vitiligo
- https://www.aad.org/public/diseases/a-z/vitiligo-overview
- https://www.amboss.com/us/knowledge/vitiligo/