ለሥር የሰደደ የኩላሊት ህመም ተጋላጭ ነዎት? Are you at Increased Risk for Chronic Kidney Disease
Tweet
እንዴት ያውቃሉ?
ለከባድ የኩላሊት መድከም የሚያጋለጡ ምክንያቶች ካሉዎት ሐኪምዎ ጋር ወይም ሆስፒታል ሔደው ምርመራ ማድረግ አለብዎት። እነዚህም፡
- የስኳር በሽታ
- ከፍተኛ የደም ግፊት
- በቤተሰብዎ ውስጥ የኩላሊት ህመም በተደጋጋሚ የሚታይ ከሆነ (ከቤተሰብ የዘር ውርስ)
- ዕድሜ መግፋት
- በተደጋጋሚ በሽንት ቧንቧ ኢንፈክሽን መጠቃት
- ከመጠን በላይ መወፈር
- ማጨስ
- ከዛም ባለፈ በአፍሪካውያን እና በአፍሪካን አሜሪካውያን ላይ አንዳንድ ከዘር ጋር የተያያዙ (ጄነቲክ) ምክንያቶች ለኩላሊት ህመም መጨመር ምክንያት ይሆናሉ። ለምሳሌ በቅርብ በጥናት የተገኙት እንደ APOL -1 ጂኖች (የዘረ መል ቅንጣቶች) በብዛት በአፍሪካውያን ላይ ስለሚገኙ ለኩላሊት ህመም የተጋለጡ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል።
እስከ 70% የሚደርሰው ዘላቂ የሆነ የኩላሊት ህመም ከስኳር ህመም እና ከደም ግፊት ጋር ተያይዞ ይከሰታል።
ስለዚህ እነዚህን እና ሎሌች ተዛማጅ ችግር ካለብዎት የቅርብ ክትትል ማድረግ፣ ማጨስ ማቆም ፣ጤናማ ክብደት መጠበቅ እና በቂ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ በጣም አስፈላጊ ናቸው።
የኩላሊት በሽታ እንንዳለብዎት ካወቁ ምን ማድረግ ይችላሉ?
ሓኪምዎ ጋር ወይም ሆስፒታል በመሔድ ምርመራ ማድረግ አለብዎት ። ምርመራዎ የሚከተሉትን ማካተት አለበት፡
- የደም ግፊትዎ መለካት
- በሽንትዎ ውስጥ ያለው ፕሮቲን ከልክ በላይ እንዳይሆን የሽንት ምርመራ ማድረግ። ፕሮቲን ለሰውነትዎ ግንባታ በጣም ጠቃሚ ንጥረ-ነገር ነው። ሆኖም ኩላሊትዎ ሲጎዳ ፕሮቲን ወደ በሽንትዎ ውስጥ ሊኖር ይችላል፡፡ ይህ የኩላሊት በሽታ ምልክት ነው ፡፡
- በደምዎ ውስጥ ያለው ክሬቲኒን(Creatinine) ከልክ በላይ እንዳይሆን ምርመራ ማድረግ። ክሬቲኒን በሰውነታችን ውስጥ የሚፈጠር ኣላስፈላጊ የሆነ ንጥረ-ነገር ነው። ከየኩላሊት ስራዎች ኣንዱ ይሄንን ንጥረ-ነገር ማስወገድ ነው። ስለሆነም የኩላሊት ችግር ሲኖር በሰውነታችን ይከማቻል። የክሬቲኒን መጠን የኩላሊቶች የማጣራት ኣቅም በምን ደረጃ እንደተዳከመ ለመገመት ያስችላል።
ምልክቶቹ ምንድን ናቸው?
ኣብዛኞቹ ሰዎች በሽታው ወደ የከፋ ደረጃ እስኪደርስ ድረስ ከበድ ያለ ምልክት ላይኖራቸው ይችላል። ሆኖም ግን እነዚህ ነገሮች ሊኖሮት ይችላሉ፥
- የድካም ስሜት
- የኣቅም ማነስ
- በደምብ ማሰብ ኣለመቻል
- የምግብ ፍላጎት መቀነስ
- የእንቅልፍ እጦት
- ደረቅ የሚያሳክክ ቆዳ
- የጡንቻ ውስጥ ሕመም
- የእግርና ቁርጭምጭሚት ማበጥ
- በዓይን ዙርያ የፊት ማበጥ፥ በተለይ ጥዋት ጥዋት
- ብዙ ግዜ ሽንት ሽንት ማለት፥ በተለይ ማታ
የኩላሊት በሽታ የምርመራ ውጤቱ ከታወቀ ቡሃላ ምን ሊደረግ ይችላል?
- ሓኪምዎ በመጀመሪያ በሸታው ከምን እንደመጣ ለማወቅ ይጥራል፥ የቀረው የኩላሊትዎ የመስራት ኣቅም ምን ያህል እንደሆነ ይገምታል፥ የህክምናውን እቅድ አብርዎት ያወጣል፥በተጨማሪም እነዚህ ነገሮችን ሊያደርግ ይችላል
- የኩላሊትዎ የማጣራት ኣቅም(GFR) ያሰላል; ይሄ የቀረው የኩላሊት የመስራት ኣቅምን ለመገመት ዋናው መንገድ ነው። ይሄንን ለማስላት የክሬትኒን መጠን፣ ዕድሜዎ፣ ጾታዎ፣ እና ሌሎች ነገሮች ኣስፈላጊ ናቸው። ዶክተርዎ ይሄንን ስሌት ተጠቅሞ ነው ሕክምናዎን ፕላን የሚያደርገው።
- ኩላሊቶችዎ ያሉበት ሁኔታ ለማወቅ የ ካት ስካን ( የረቀቀ የራጅ ምርመራ ) / CT ወይም የኣልትራሳውንድ ምርመራ ሊያደርግ ይችላል። ይህ ምርመራ የኩላሊት ጠጠር፥ እጢ ወይም ሌላ ችግር ካለብዎት ለማወቅ ያስችላል።
- የኩላሊት ናሙና(Biopsy) ተወስዶ ሊመረመር ይችላል። ይህ ምርመራ የኩላሊት በችታዎ በምን ምክንያት እንደመጣ ለማወቅ ትልቅ ሚና ኣለው።
ናሙናው ከኩላሊትዎ ተቆርጦ የሚወሰድ ሲሆን ምርመራው የሚደረገው በማይክሮስኮፕ ይሆናል።
ኣምስት የኩላሊት በሽታ ደረጃዎች
እንዳይባባስ መከላከል የቻላል?
ኣዎ ይቻላል። ቶሎ ተመርምረው ህክምና ከጀመሩ ባለበት ማስቆም ወይም መባባሱ ማዘግየት ይቻላል። ሕክምናዎ ምን ያህል ይሰራል የሚለው ቀጥለው ባሉት ሁኔታዎች ይወሰናል።
- ሕክምና ሲጀምሩ የነበረው የበሽታዎ ደረጃ፡ ቶሎ ከጀመሩ የመዳን ዕድልዎ ወይም ከህክምና የሚያገኙት ጥቅም ከፍ ይላል።
- ሕክምናዎን በጥንቃቄ መከታተልዎ፡ ስለበሽታዎ ሁሉም ነገር ለማወቅ ይሞክሩ፣ የተሰጥዎት መድሓኒት በደምብ ይጠቀሙ፣
- የበሽታው መንስኤ፡ ኣንዳንዶቹ የኩላሊት በሽታዎች ሕክምናቸው ኣስቸጋሪ ነው፥ ላይድኑም ይችላሉ።