በ ዶ/ር ኤርሚያስ ካቻ 

COVID-19 ወሳኝ ዝግጁነት እና ምላሽ እርምጃዎች በዶ/ር ኤርሚያስ ካቻ 

እ.ኤ.አ. ማርች  10 2020 የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) COVID-19ን በ ዓለም አቀፍ ደረጃ ወረርሽኝ  እንደሆነ አስታውቋል፡፡እስከ አሁን ባለው ሰአት ይህ ወረርሽኝ ከ 100 አገራት በላይ ተከስቶአል። ምንም እንኩዋን ይህ በሽታ በኢትዮጵያ እንዳልተከሰተ ቢገለፅም የመከሰቱ እድል በጣም ከፍ ያለ ነው። በሽታው የተከሰተባቸው በርካታ አገሮች COVID-19 ከአንድ ሰው ወደ ሌላ የሚተላለፍበትን  ፍጥነት ሊቀንስ ወይም ሊቆም እንደሚችል አሳይተዋል። ይህም መጠነ ሰፊ የሆነ ዝግጅትን ይጠይቃል።  ቀድሞ የታሰበባቸው የአደጋ ጊዜ ምላሽ ስርዓቶች ለዚህ በጣም ወሳኝ ናቸው። 

አነዚህ  የአደጋ ጊዜ ምላሽ ስርዓቶች ኣላማቸው

  • ወረርሽኝን ከመከሰት መከላከል፣ከተከሰተም በኃላ ስርጭቱን ማዘግየት ወይም ማቆም
  • ለጽኑ ህመምተኞች ተገቢውን እንክብካቤ መስጠት
  • ወረርሽኙ በጤና ሥርዓቶች፣ማህበራዊ አገልግሎቶች እና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ላይ የሚያስከትለውን ተፅእኖ መቀነስ

ወረርሽኝን ከመከሰት መከላከል፣ከተከሰተም በሁላ ስርጭቱን ማዘግየት ወይም ማቆም

  • የጤና ትምህርት በእጅ ንጽህና አጠባበቅ፤ 
  • ተገቢውን ርቀት በሰዎችም መሃከል መጠበቅ ፤ 
  • ብዙ ሰዎች በኣንድ ቦታ ሊሰበሰቡባቸው የሚችሉባቸውን ጉዳዮች ለጊዘውም ቢሆም ማቆም ወይም ማዘግየት። 

የተደራጀ በሽታው ያለባቸውን ሰዎች የማግኘት አርምጃ መውሰድ። ( Active Surveillance and Quarantine Cases/Suspects/Contacts)

  • ይህ በተለይ ከውጭ ሃገር ወደሃገር ቤት የሚገቡ ተጓዥን ይመለከታል። በተጨማሪም በሽታው ባንድ የሃገሪቱ ክፍል ከተከሰተ ከዚያም የሚመጡትንም ያካትታል። ሁሉም ወደ ሃገር ቤት የሚገባ ተጓዥ ራሱን ለሁለት ሳምንት ቢያገል ይመከራል። 
  • በሽታው የተገባቸው ሰዎች ለብቻ መነጠልና ከነሱም ጋር ግኑኝነት የነበራቸው ሰዎች አራሳቸውን አንዲያገሉ ማድረግ። 
  • በሆስፒታሎችና በጤና ጣቢያዎች የሚመጡ በሽተኞችን  ከ COVID-19 ተመሳሳይ ምልክቶች ካላቸው የበለጠ የነበሩበትንና የጉዞ ታሪካቸውን ማጣራት፤ ኣሳሳቢ ሁነታዎች ከታዩ ለሚመለከተውም ኣካል ማሳወቅ። 
  • ፈጣን የላቦራቶሪ ምርመራ እና ውጤትን ማግኘት

ለጽኑ ህመምተኞች ተገቢውን እንክብካቤ መስጠት

  • ኣገሪቱ ያላት ጽኑ ህሙማንን  ማከም የሚችሉ ተቁዋሞች ኣነስተኛ በመሆናቸው ያለውን መጠቀም የሚችሉኝ በሽተኞችን በሚገባ መለየት። 
  • ይህንን እንክብካቤ ብቻ የሚሰጡ የጤና ማዕከሎችንና ሆስፒታሎች መለየት
  • በሽታ በሚከሰትበት ጊዜ የምርጫ የቀዶ ጥገና (Elective Surgeries ) መሰረዝ ፤ የቀዶ ህክምና ክፍሎችን  አንደ ጊዚኣዊ ጽኑ ህሙማን ክፍል መጠቀም።
  • ለህክምና ባለሙያዎችም ተገቢውን የመከላከያ ቁስ ማቅረብ። 

ወረርሽኙ በጤና ሥርዓቶች፣ማህበራዊ አገልግሎቶች እና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ላይ የሚያስከትለውን ተፅእኖ መቀነስ

  • ሌሎች ሥር የሰደደ የሕክምና ችግሮች ላለባቸው ሰዎች ሌላ አማራጭ የህክምና መስጫ ቦታ መኖር  አለበት።
  • በሽታ መሰራጨት ሲጀምር ከቤት መስራትና የርቀት ትምህርት ክፍሎችና  እንደ አማራጭ ማቅረብ።
  • ከተቻለ ህዝብ የማይበዛባቸውን ተለዋጭ የመጓጓዣ መንገዶችን በመጠቀም ።
  • ሰዎች በበሽታ ምክንያት እራሳቸውን ቢያገሉ ድጋፍ ማድረግ።