ሲ/ር መቅደላዊት ወርቁ (ነርስ፣ በዳግማዊ ምኒልክ ህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የኤምፒኤች ጤና አገልግሎት አስተዳደር የ2ኛ ዓመት ተማሪ፣እና የ4ኛ ዓመት የኢኮኖሚክስ ተማሪ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ንግድ ስራ ኮሌጅ )
Sr. Mekdelawit Worku, BSC Nurse, 2nd year MPH in Health Service Management student at Menelik II Medical and Health Science College, and 4th year Economics student at Addis Ababa University School of Commerce
ቅድመ እርግዝና ክትትል ማለት ሊሻሻሉ የሚችሉ ነገር ግን ለበለጠ የጤና ችግር (ፅንሱ ላይ አካላዊ ጉዳት እንዲሁም ውጤታማ ያልሆነ እርግዝና) ተጋላጭ የሚያደርጉ ሁኔታዎችን ለመለየት ብሎም ለማስተካከል ከእርግዝና በፊት የሚደረግ እንክብካቤ ነው።
ይህ ክትትል አንድ እድሜዋ ከ15-49 የሆነች ሴት ነፍሰ ጡር ለመሆን(ለማርገዝ) ስታቅድ የምታደርገው የክትትል አይነት ሲሆን ሁሉም በዚህ እድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሴቶች ከትዳር አጋሮቻቸው ጋር በጋራ በመሆን ቢያደርጉት ይመከራል፡፡
የቅድመ እርግዘና ክትትል በይበልጥ ፡-
- ተጓዳኝ ህመም ላለባቸው (የስኳር፣የኩላሊት፣የልብ በሽታ፣የሆርሞን መዛባት)
- የእርግዝና ታሪክ (ተደጋጋሚ ውርጃ ፣ ከማህፀን ውጪ እርግዝና )
- የተለያዩ መድሃኒቶችን ለሚወስዱ እንዲሁም መድሃኒት ሊቀነስ ፣ ሊቋረጥ ይችላል ይህ ደግሞ በፅንሱ ላይ የሚደርሱትን አካላዊ ጉዳቶች እንዲሁም ሞትን ይቀንሳል፡፡
- እርግዝና የሚከለከልባቸው ሁኔታዎች ለምሳሌ የካንሰር ፣ የጨረር ህክምና
የሚወስዱ ፣ የመጨረሻ ደረጃ የኩላሊት በሽታ፣ ከፍተኛ የልብ ህመም ወ.ዘ.ተ.. ሲኖር ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው።
ቅድመ እርግዝና እንክብካቤ ምን ምን ያካትታል?
የሚከተሉትን ጥያቄዎች መጠየቅ
- የቀድሞ የእርግዝና ታሪክ
- በዘር የሚተላለፍ በሽታ ካለ
- አሁን ላይ ቋሚ በሽታ ካለ
- አሁን ላይ የሚወሰድ መድሃኒት ካለ
- የተለያዩ ምርመራዎች ይሰራሉ
እነዚህ ምርመራዎች ጽንሱ ላይ ሊተላለፉ የሚችሉ እንዲሁም የጽንሱ አስተዳደግ እና ጤና ላይ አሉታዊ አስተዋጾ ሊያደርጉ የሚችሉ የተለመዱ ህመሞችን ለመለየት ይረዳሉ።
ለምሳሌ፡-
- የደም ማነስ( Anemia)፣
- የደም አይነትን ማውቅ፣
- የአባላዘር በሽታዎችን ለማውቅ ፣
- የጉበት ቫይረስ ሄፐታይተስ(Hepititis)፣
- ኤች.አይ.ቪ(HIV) ፣
- የሆርሞን መዛባት ፣
- የደም ግፊት ፣
- የስኳር በሽታ አብዛኛውን ጊዜ ከሚደረጉ ምርመራዎች ውስጥ ተጠቃሾች ናቸው።
እንዲሁም ከእርግዝና በኋላ ለጽንሱ ጤናማ አስተዳደግ አሉታዊ አስተዋጾ የሚያደርጉ የአመጋገብ እና የአኗኗር ዘይቤዎች ላይ ለውጥ ማድረግ ወሳኝ ነው።
አላማውም
- የእናቶችን እንዲሁም እድሜያቸው ለወሊድ የደረሱ ሴቶችን ጤና መጠበቅ እና ማሻሻል
- የእናቶች እና የጽንሱን ጤና የሚያውኩ ግላዊም ሆነ አካባቢያዊ ነገሮችን ለመቀነስ እና ለመቆጣጠር
- በተጨማሪም የእናቶች እና የህጻናትን ጤና ለጊዜያዊም ሆነ በዘላቂነት ለማሻሻል
- የእናቶች እና በፅንሱ ላይ የሚደርሱ ማንኛውም የጤና ጉድለትና ሞትን ለመከላከል
- ጤናማ ምጥ እና ልጅ እንዲኖር አስተዋፅዖ ያደርጋል።
የሚወሰዱ መድሃኒቶች
ከላይ የተጠቀሱት አላማዎች እንዲሳኩ ጠቃሚ ማዕድናት (Vitamins, Minerals) እንዲሁም ክትባቶች (Vaccines) አስፈላጊ ናቸው።
ምሳሌ ፡
- ፎሊክ አሲድ (Folic Acid):– የፅንስ አካላዊ ጉዳቶችን ይከላከላል። ከእነዚህም መካከል በፅንሱ ጭንቅላት(አንጎልና ውስጥ ከፍተኛ ፈሳሽ መቋጠርን (Hydrocephalus) ፣ በፅንስ ጭንቅላት እና በጀርባ አጥንት ላይ የሚፈጠር ክፍተትን ይቀንሳል ፡፡
- ካልሲየም