በኮሮና ቫይረስ አንዴ የተያዙ ሰዎች ተመልሰው በሽታው ሊይዛቸው ይችላል?
በቅርቡ በቻይናዋ ዋንዞ ግዛት ውስጥ የተደረግ ጥናት እንደሚያሳየው በኮሮና ቫይረስ ስንያዝ ሰውነታችን የሚያመነጫቸው በሽታን የመከላከል ሥራ የሚሰሩ ፕሮቲኖች (Antibodies ) ከሰውነታችን ውስጥ ከ ሁለት እስክ 3 ወር ባለው ጊዜ ተመልሰው ሊጠፉ ይችላሉ። ይህ ማለት ደግሞ ከዚህ በፊት በበሽታው የተያዝን ቢሆንም እንደገና የመያዝ እድል ሊኖረን ይችላል ማለት ነው። ጥናቱ የተሰራው በጥቂት ሰዎች ላይ ስለሆነ ተጨማሪ ሰፊ ምርምር ሊያሰፈልገው ቢችልም ከዚህ ጥናት የምንወስደው ዋና ነገር በሽታውን ለመከላከል የሚያስፈልጉ ዋና ነገሮች – በ ቤት መቆየት ፣ እጅን በየጊዜው መታጠብ ፣ አቅላው ርቀትን መጠበቅ ፣ የፊት ማስክ ማድረግ ሁሌም ማድረግ እና መከተል ያስፈልጋል ። ከዚህ በፊት በበሽታው የተያዝን እና የዳንን ቢሆንም።
ዋናውን ጥናት ለማንበብ ይሄን ሊንክ ይጫኑ
በዚህ ዙሪያ የተሰራውን ዜና ለማንበብ ይሄን ሊንክ ይጫኑ
የኮሮና ቫይረስ ምልክቶች ምንድናቸው
ማሳል
ትኩሳት
ብርድ ብርድ ማለት
የመቆረጣጠም ስሜት
ትንፋሽ ማጠር
የጉሮሮ ህመም
በአፍንጫችን የማሽተት ስሜት መጥፋት ወይም ከ ምላሳችን ላይ የጣእም ስሜት መጥፋት
ምልክቶች በሽታው ከያዘው ሰው ጋር ከተገናኘን /ንክኪ ከፈጠርን በሃላ ከ 2-14 ቀናት ባሉ ጊዜያት ለታዩ ይችላሉ።
እነዚህን ምልክቶች የበረታ /የከፋ COVID 19 ምልክቶች ስለሆኑ አስቸካይ ሕክምና ይሻሉ
ከፍተኛ የሆነ የትንፋሽ ማጠር
የማያቃርጥ የደረት ህመም
የመቃዘት ስሜት ፣መዳከም እንቅልፍ እንቅልፍ ማለት ወይም ከተኛንበት ለመነሳት አቅም ማጣት
ከንፈራችን ፣አፍንጫችን እና ፊታችን አከባቢ ከ ኦክስጅን እጥረት ጋር በተያየዘ ከወትሮው በተለየ ጠቆር ማለት
ለከፋ የ ኮሮና ቫይረስ ህመም ተጋላጭ የሆኑ ምን አይነት ሰዎች ናቸው?
በእድሜያቸው ገፋ ያሉ ሰዎች ; ከስር ያለው ግራፍ እንደሚያሳየው እድሜያችን ከፍ ባለ ቁጥር በፀና የኮቪድ 19 ህመም ሆስፒታል የመታከማችን እና በኮቪድ የተነሳ የመሞት እድላችን እየጨመረ ይመጣል። የአሜሪካው የበሽታ መቆጣጠሪያ ማዕከል CDC ያወጣው መረጃ በኮቪድ 19 ምክንያት ከሞቱት ሰዎች ከ 80 % በላዩ ሰዎች
ይሄ መረጃ የሚያሳየው አዛውንቶች ለዚህ በሽታ የበለጠ ተጋላጭ እና ተጎጂ ይሆናሉ ይላል እንጂ ታዳጊዎች እና ወጣቶች በዚህ ህመም አይያዙም ወይም ለሞት አይዳረጉም ማለት አይደለም። ስለዚህ ሁላችንም በማንኛውም ቦታ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርብናል። በቤተሰባችን ውስጥ ላሉ አዛውንቶች ሁሌም ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርብናል
ተጋዳኝ ህመም ያለባቸው ሰዎች ለምሳሌ
የኩላሊት ህመም ያለባቸው ሰዎች
የተለያየ አይነት የሳንባ ህመም ያለባቸው ሰዎች
ከፍተኛ የሰውነት ውፍረት ያላቸው ሰዎች
የልብ ድካም ወይም የተለያየ የልብ ህመም ያለባቸው ሰዎች
የስካር ህመም ያለባቸው ሰዎች
በተለያዩ ምክንያቶች የሰውነትን የበሽታ መከላከል አቅም የሚያዳክሙ መድኃኒቶች የሚወስዱ ሰዎች
ሌሎች በኮቪድ 19 ከፍተኛ ህመም ተጋላጭ ሊሆኑ የሚችሉ ሰዎች
የአስም ህመም ያለባቸው ሰዎች
የስትሮክ ህመም ያለባቸው ሰዎች
የደም ግፊት ያለባቸው ሰዎች
የጉበት ህመም ያለባቸው ሰዎች
እርጉዞች
የሚያጨሱ ሰዎች
HIV ያለባቸው ሰዎች
ዴክሳሜታዞን እና ኮቪድ 19
በቅርብ ከ እንግሊዝ የወጡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ዴክሳሜታዞን የተባለው መድሀኒት በኮቪድ 19 የተነሳ የሚከሰተውን ሞት የመቀነስ አቅም እንዳለው አሳይተዋል። የመድሃኒቱ ጥቅም በተለይም በኮቪድ 19 የተነሳ ከፍተኛ ህመም የገጠማቸው ሰዎች እና የ ኦክስጅን እና የ አርቴፊሻል መተንፈሻ ማሽን የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ላይ የተሻለ ጥቅም አሳይታል።
ጥናቱ የሚያሳየው ዴክሳሜታዞን በኮቪድ 19 የተነሳ ከፍተኛ ህመም የከ ገጠማቸው ሰዎች አንድ ሶስተኛውን ከሞት ሊያድን እንደሚችል እንጂ ፍፁም መድሃኒት እንደሆነ አይደለም። ስለዚህ ይሄን መድኃኒት ያለ ሐኪም ትዕዛዝ መውሰድ አይገባም ። መድኃኒቱ ብዙ የጎንዮሽ ጉዳቶች ስላሉት በሚሰጥበት ግዜ የቅርብ ክትትል ያስፈልገዋል።
ምንጭ RECOVERY trial