ከማህፀን ውጭ የሆነ እርግዝና(Ectopic Pregnancy)
በሔርሞን እስራኤል (በሀያት ህክምና ኮሌጅ PC1 የህክምና ተማሪ)
Approved by: Dr. Misikir Anberbir (Gynecologist/Obstetrician)
ጤናማ እርግዝና ማለት የሴት ልጅ እንቁላል ከወንድ ልጅ ዘር ጋር በሚዳቀልበት ጊዜ በሴት ልጅ ማህፀን ውስጥ የዳበረ እንቁላል ተፈጥሮአዊ እድገቱን የሚቀጥልበት ሂደት ሲሆን ከዚህ ውጭ የሚፈጠር እርግዝና ከማህፀን ውጭ እርግዝና ይባላል፡፡
ከማህፀን ውጭ የሆነ እርግዝና ስንል ምን ማለታችን ነው?
ከማህፀን ውጭ የሆነ እርግዝና ስንል ምን ማለታችን ነው?
ከማህፀን ውጭ የሆነ እርግዝና ማለት ከወንድ ዘር ጋር የተዳቀለው እንቁላል (የዳበረ እንቁላል) በማህፀን ቱቦ (እንቁላልን ከኦቫሪስ ወደ ማህፀን የሚወስደው ቱቦ) ውስጥ በመጣበቅ እድገት የሚፈፅምበት ሂደት ነው። በማህፀን ቱቦዎች ውስጥ እርግዝና ሲከሰት ፅንሱ እድገቱን መቀጠል የማይችል እና በቱቦዎቹ ውስጥ በቆየ ቁጥር ደግሞ በእናትየው ጤና ላይ አደጋ የሚያስከስት ይሆናል፡፡
1000 ከሚሆኑ እርግዝናዎች ውስጥ ከ5-7 በሚሆኑ እናቶች ላይ ይህ ችግር የሚታይ ሲሆን ችግሩ ከዚህ ቀደም አጋጥሙዋቸው የነበሩ ወይም የማህፀን ኢንፌክሽን ችግር የነበረባቸው እናቶች፤ሴቶች ላይ የመፈጠር እድል አለው።
ከማህፀን ውጭ እርግዝና እንዲፈጠር ተጋላጭ የሚያደርጉ ሁኔታዎች ምን ምንድን ናቸው?
የተለያዩ ችግሮች ለበሽታው አጋላጭ መንስኤ ቢሆኑም ከብዙዎቹ ዋነኞቹ ግን
- በቀዶ ህክምና ወቅት የሚደርስ የማህፀን ቱቦ ጉዳት
- በማህፀን ቱቦዎች ላይ የሚከሰት ኢንፌክሽን
- የሆርሞን መዛባት
- ከዚህ ቀደም የተከሰተ የማህፀን ውጭ እርግዝና
- ሲጋራ ማጨስ
- የአባላዘር በሽታዎች ጥቂቶቹ ናቸው።
ከማህፀን ውጭ የሚፈጠር እርግዝና ምልክቶች ምን ምንድን ምናቸው?
- ያልተለመደ ቁርጠት
- ደም ወይም ቡናማ ፈሳሽ በማህፀን መፍሰስ
- ጐን አካባቢ እንዲሁም ሆድ ላይ ያልተለመደ ህመም
- ማቅለሽለሽ፤ማስመለስ
እነዚህ ምልክቶች የተለመደና ጤናማ እርግዝና ላይ የሚከሰቱ ቢሆኑም እነዚህ ምልክቶች የታየባቸው እናቶች ክትትል እንዲያረጉ ይመከራል።
ከማህፀን ውጭ የሆነን እርግዝናን እንዴት መከላከል ይቻላል?
ይህን የእርግዝና አይነት ሙሉ በሙሉ መከላከል ባይቻልም ሊፈጠር የሚችልበትን እድል መቀነስ ይቻላል። ከእነርሡም ውስጥ በግብረስጋ ግንኙነት ጊዜ መከላከያን መጠቀም፣ በማህፀን ቱቦዎች ላይ የሚከሰቱ ኢንፌክሽኖችን በጊዜው መታከም እና ሲጋራ የሚያጨሱ ከሆነ ለማጨስ ማቆም መሞከር ዋነኞቹ ናቸው።
ከማህፀን ውጭ የሆነ እርግዝና (ectopic pregnancy) የማህፀን ቱቦ መቀደድን ሊያስከትል ይችላል ይህም በሚሆንበት ጊዜ ዘላቂ ችግር ስለሚያስከትል በጊዜ ህክምና ማድረግ ተገቢ ነው።
የጤና ወግ
ጠቃሚ እና የተረጋገጠ መረጃ ለጤናዎ ።
የጤና ወግን በነዚህ ሊንኮች መከታትል ይችላሉ ።
https://linktr.ee/Yetena_Weg