የደም ግፊት ማለት ደም በሰውነታችን የደም ስሮች ውስጥ ሲዘዋወር የሚፈጥረው ግፊት ነው። የደም ግፊት መጨመርን የህክምና ምርመራ በምናደርግበት ጊዜ በባለሙያ ወይም ቤትታችን ውስጥ ባሉ በተፈቀዱ መሳሪያዎች በመለካት ብቻ ነው ልናውቅ የምንችለው።

High blood pressure concept

እንደ አለም ጤና ጥበቃ ድርጅት መረጃ (መረጃውን ከምንጩ ለማየት ይህን ይጫኑ) በአለም ላይ ከ አራት ወንዶች አንዱ ፣ ከአምስት ሴቶች አንዷ የደም ግፊት መጨመር አለባቸው። በኢትዮጲያ ውስጥ የተሰሩ መለስተኛ ጥናቶች (መረጃውን ከምንጩ ለማየት ይህን ይጫኑ) እንደሚያሳዩት እስከ 20 % ሰው የደም ግፊት አለበት ።

የደም ግፊት መጨመር ካልታከመና ክትትል ካልተደረገበት ለሞት ፣ ለተለያዩ ድንገተኛ እና
ዘላቂ የልብ ህመሞች፣ ለስትሮክ፣ ለጭንቅላት ደም መፍሰስ እና ለ ድንገተኛ እና ዘላቂ
የኩላሊት ህመም ያጋልጣል።

በመሆኑም በመደበኛነት የደም ግፊት መጠንን ሁኔታ በመመርመር አስፈላጊውን ሕክምና ማግኘት ጠቃሚ ነው፡፡

የከፍተኛ ደም ግፊት መንስዔዎች ምን ምን ናቸው?

ትክክለኛዎቹ የደም ግፊት መንስዔዎች አይታወቁም፡፡ ነገር ግን ለበሽታው ምክኒያት ከሆኑት መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡-

  • ማጤስ
  • ያልተመጠነ ውፍረት
  • የአካላዊ እንቅስቃሴ ማነስ (አብዝቶ መቀመጥ)
  • በምግብ ውስጥ ጨው አብዝቶ መጠቀም
  • ከመጠን ያለፈ አልኮሆል መጠጥ
  • የዕድሜ መግፋት
  • ከቤተሰብ በደም የሚወረስ
  • በዘር ( ለምሳሌ በአሜሪካን ሀገር የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከነጭ አሜሪካውያን ይልቅ ጥቁር አሜሪካውያን ለከፋ የደም ግፊት በሸታ የተጋለጡ ናቸው)
  • ሥር የሰደደ የኩላሊት ሕመም
ከፍተኛ የደም ግፊት አዳጊ ሕፃናትን ሊያጠቃ ይችላልን?

ምንም እንኳ ብዙ የተለመደ ባይሆንም፤ ከፍተኛ የደም ግፊት አዳጊ ሕፃናት ላይም ሊታይ ይችላል፡፡ በመሆኑም የደም ግፊት መጠንን በየጊዜው መታየት እና ይህንም የሕይወት ዘመን ልማድ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

ከፍተኛ የደም ግፊት ያለብኝ መሆኑን እዴት ማወቅ እችላለሁ?

ከፍተኛ የደም ግፊት ያለባቸው ሰዎች ምንም ዓይነት የሕመም ስሜት አይሰማቸውም፡፡
ከፍተኛ የደም ግፊት እንዳለብዎ ሣያውቁት ለዓመታት ሊቆዩ ይችላሉ፡፡ ከዚም የተነሣ
በሽታው “አድብቶ ገዳይ” ከሚባሉት መካከል ነው፡፡ ከፍተኛ የደም ግፊት እንዳለብዎ ለማወቅ የሚረዳው ብቸኛ መንገድ በመደበኛነት የደም ግፊት መጠን ልኬት ማድረግ ነው፡፡

በማንኛውም ጊዜ ሐኪምዎን ሲጎበኙ የደም ግፊት መጠንዎን መለካት ይችላሉ፡፡ ለሁሉም ሰው፤ ጎልማሶችም ሆኑ አዳጊ ሕፃናት በመደበኛነት የደም ግፊት መጠን መለካት
ያስፈልጋል፡፡

ምንጭ

Source : The National Kidney Foundation

ይህን የጤና መረጃ ከአሜሪካን የኩላሊት ህክምና ማህበር ድረ ገፅ ላይ ምንጭ አድርገን ስናቀርብ ፅሁፉን በመተርጎም የተባበርንን አቶ ኤያልቅበት አደምን ( twitter: @Ademo51108267 ) ከልብ እናመሰግናለን ።
If you want to read the original article in English please click here.