በዶክተር ቤተልሄም ተስፋስላሴ(ጠቅላላ ሀኪም)
የጤና ምርመራ | 18-39 የእድሜ ክልል | 40-49 የእድሜ ክልል | 50-64 የእድሜ ክልል | 65 አና ከዛ በላይ የእድሜ ክልል |
---|---|---|---|---|
ደም ግፊት ምርመራ | ከ21 ዓመት ጀምሮ ከዛን በየ 1‐2 ዓመቱ | ቢያንስ በአመት አንድ ግዜ | ቢያንስ በአመት አንድ ግዜ | ቢያንስ በአመት አንድ ግዜ |
የደም ኮሌስትሮል መጠን ምርመራ | ከ20 ዓመት ዕድሜ ጀምሮ ለልብ በሽታ ተጋላጭነት ካለ አዘውትሮ ምርመራውን ማድረግ | ቢያንስ በአመት አንድ ግዜ ለልብ በሽታ ተጋላጭነት ካለ አዘውትሮ ምርመራውን ማድረግ | ቢያንስ በአመት አንድ ግዜ ለልብ በሽታ ተጋላጭነት ካለ አዘውትሮ ምርመራውን ማድረግ | ቢያንስ በአመት አንድ ግዜ ለልብ በሽታ ተጋላጭነት ካለ አዘውትሮ ምርመራውን ማድረግ |
የስኳር በሽታ ቅድመ ምርመራ | ከ45 ዓመት ዕድሜ ጀምሮ እና ከዚያም ቢያንስ በአመት አንድ ግዜ | ቢያንስ በአመት አንድ ግዜ | ከ45 ዓመት ዕድሜ ጀምሮ እና ቢያንስ በአመት አንድ ግዜ |
|
የኩላሊት ምርመራ | የስኳር በሽታ ወይም የደም ግፊት ያለባቸው ሰዎች በዓመት አንድ ጊዜ የኩላሊት ምርመራ ማድረግ አለባቸው | የስኳር በሽታ ወይም የደም ግፊት ያለባቸው ሰዎች በዓመት አንድ ጊዜ የኩላሊት ምርመራ ማድረግ አለባቸው | ከ 60 ዓመት በኋላ በዓመት አንድ ጊዜ | በዓመት አንድ ጊዜ |
የጡት ካንሰር ቅድመ ምርመራ | ከ20 ዓመት ዕድሜ ጀምሮ፣ በየወሩ እርስዎ በሚያደርጉት ጡት ምርመራ | በየአመቱ በ ጤና ባለሙያ እና በየወሩ እርስዎ በሚያደርጉት ጡት ምርመራ | በየአመቱ በ ጤና ባለሙያ እና በየወሩ እርስዎ በሚያደርጉት ጡት ምርመራ | በየአመቱ በ ጤና ባለሙያ እና በየወሩ እርስዎ በሚያደርጉት ጡት ምርመራ |
ማሞግራም | ከ40 ዓመት ዕድሜ ጀምሮ፣ በየ 1‐2 ዓመቱ | በየ 1‐2 ዓመቱ | በየ 1‐2 ዓመቱ እስከ 74 ዓመት እድሜ 75 እና ከዚያ በላይ ከሆነ, ሐኪምዎን ያማክሩ |
|
የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር ቅድመ ምርመራ | ከ21ዓመት ጀምሮ ከዛን በየ 3-5 ዓመቱ ሌሎች አጋላጭ ሁኔታዎች ካሉ ምርመራው ቀደም ብሎ ሊጀመር ይችላል | በየ 3-5 ዓመቱ | በየ 3-5 ዓመቱ | በየ 3-5 ዓመቱ |
የኤች አይ ቪ ቫይረስ ምርመራ | በየ 3 ወሩ | በየ 3 ወሩ | በየ 3 ወሩ | በየ 3 ወሩ |
የአንጀት ካንሰር | ከ50 ዓመት ዕድሜ ጀምሮ፣ በየ 10 ዓመቱ | በየ 10 ዓመቱ | ||
የጥርስ ጤና | በዓመት 1-2 ጊዜ | በዓመት 1-2 ጊዜ | በዓመት 1-2 ጊዜ | በዓመት 1-2 ጊዜ |
የዓይን ጤና | አንድ ጊዜ በ 20 እና በ 39 ዕድሜ | በየ 2-4 ዓመቱ | በየ 2-4 ዓመቱ | በየ 2-4 ዓመቱ |