የማህፀን በር ካንሰርን መከላከል ይቻላል!!
በአለም አቀፍ ሁኔታ በሴቶች ላይ ከሚከሰቱ የካንሰር አይነቶች የማህፀን በር ካንሰር በ 4 ተኛ ደረጃ ላይ የሚቀመጥ ሲሆን ሲሆን በኢትዮጵያ ደግሞ በ2ኛ ደረጃ ይቀመጣል።
በ 2018 በዚህ ካንሰር ከ 570,000 በላይ ሴቶች ተጠቅተዋል። ምንጭ :WHO
- የማህፀን በር ካንሰር ምንድን ነው?
(ህዋሶች ) ከተለመደው ወጣ ባለ እና ጤናማ ባልሆነ መልኩ ሲያድጉ እና ሲባዙ ይፈጠራል ።
የማህጸን በር ካንሰር በማህጸን አካባቢ ያሉ የሰውነት ክፍሎችን ሊወር፣ ወደሌላ የሰውነት ክፍሎቻችንም ሊሰራጭ ይችላል።
- ሂዩመን ፓፒሎማ ቫይረስ ምንድን ነው?
ሂዩመን ፓፒሎማ ቫይረስ በግብረ ስጋ ግንኙነት ጊዜ የሚተላለፍ ቫይረስ ሲሆን የማህጸን በር ካንሰር ዋናው አጋላጭ ነው። ከ99% በላይ የሚሆነው የማህፀን በር ካንሰር ከዚህ ቫይረስ ጋር በተያያዘ የሚመጣ ነው። ምንጭ :WHO
- የማህፀን በር ካንሰር ማን ላይ ሊከሰት ይችላል?
ማንኛዋም ግንኙነት የጀመረች ሴት በማህፀን በር ካንሰር ልትያዝ ትችላለች። በግንኙነት ወቅት ኮንዶም የምትጠቀም ቢሆንም እንኳን!
- ለማህፀን በር ካንሰር እነማን የበለጠ ተጋላጭ ናቸው?
- በሽታ የመከላከል አቅማቸው በማንኛውም ምክንያት የተዳከመ ፦ ኤችአይቪ በደማቸው ውሰጥ ያለን ጨምሮ
- ሲጋራ የሚያጨሱ ፤
- ከተለያዩ ወንዶች ጋር ግንኙነት የሚያደርጉ ወዘተ….
- ይህ ካንሰር ሳይከሰት ቀድሞ መከላከል ይቻላልን?
አዎን
እንዴት?
- የሂዩመን ፓፒሎማ ቫይረስ ክትባት በወቅቱ በመውሰድ
የአለም ጤና ጥበቃ ድርጅት ሁሉም ሴቶች አስራ አምስት አመት ሳይሞላቸው ክትባቱን እንዲውስዱ ይመክራል።
የሂዩመን ፓፒሎማ ቫይረስ ክትባት የማህጸን በር ካንሰር አምጪ ከሆኑት የሂዩማን ፓፒሎማ ቫይረሶች ይከላከላል።
- የቅድመ ካንሰር ምርመራ
ማንኛዋም ሴት እድሜዋ 21 አመት ከሆነበት ወይም ግንኙነት ከጀመረችበት ከ3 አመት ጀምሮ በየ3 አመቱ ፓፕ ስሚር የተሰኘውን ምርመራ ብታደርግ።
ፓፕ ስሚር በማህጸን በር ላይ ጤናማ ያልሆኑ ቅድመ ካንሰር ለውጦች ካሉ ለመፈተሽ በጤና ባለሞያዎች የሚደረግ ምርመራ ነው። ጤናማ ያልሆኑ ለውጦች ከታዩ ክትትል እና አስፈላጊው ህክምና ይደረጋል ።
በዶ/ር ማህሌት አለማየሁ
ትዊተር: @MahletAlemayeh7
ምንጭ : Click here