የማህፀን በር ጫፍ ካንሰርየቅድመ ካንሰር ምርመራ
(ህዋሶች ) ከተለመደው ወጣ ባለ እና ጤናማ ባልሆነ መልኩ ሲያድጉ እና ሲባዙ ይፈጠራል ።
የማህጸን በር ካንሰር በማህጸን አካባቢ ያሉ የሰውነት ክፍሎችን ሊወር፣ ወደሌላ የሰውነት ክፍሎቻችንም ሊሰራጭ ይችላል
በአለማችን ያሉ ሴቶችን በብዛት ከሚያጠቁ የካንሰር በሽታዎች አራተኛውን ደረጃ የያዘው የማህፀን ጫፍ
ካንሰር የሚባለው የካንሰር ዓይነት ነው፡፡ ይህን በሽታ ለየት የሚያደርገው ከ80% በላይ የሚያጠቃዉ መካከለኛና
ዝቅተኛ ገቢ ካላቸው ሃገሮች የሚኖሩ ሴቶችን መሆኑ ነው፡፡ ነገር ግን ቅድሚያ በሚሰጡ ክትባቶች እንዲሁም በግዜ
አግኝቶ ለማከም የሚረዳውን (papsmear) የማህፀን ጫፍ ካንሰር ምርመራ በማድረግ መከላከል ይቻላል፡፡
- አጋላጭ መንገዶች
የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር ዋናዎቹ አጋላጭ መንገዶች የሚከተሉት ናቸው፡፡
- (HPV) ቫይረስ
ሂዩመን ፓፒሎማ ቫይረስ በግብረ ስጋ ግንኙነት ጊዜ የሚተላለፍ ቫይረስ ሲሆን የማህጸን በር ካንሰር ዋናው አጋላጭ ነው። ከ99% በላይ የሚሆነው የማህፀን በር ካንሰር ከዚህ ቫይረስ ጋር በተያያዘ የሚመጣ ነው። ምንጭ :WHO
ይህ ቫይረስ ብዙውን ጊዜ በሽታው ምልክቶች ሳይኖሩት በሰውነት ውስጥ ኖሮ የማህፀን ጫፍ ካንሰር ሊያመጣ ይችላል፡፡
ይህን ለመከላከል የሚረዳ ክትባት እድሚያቸው ከ 17 – 25 እንዲሁም ከ 25-40 ዓመት ላሉ ሴቶች መስጠት ተጀምሯል፡፡
. ሲጋራማጨስ
. የአባላዘር በሽታ የተያዙ ሴቶች (HIV) ጨምሮ
. ለረጅም ጊዜ ማለትም ከ5 አመት በላይ በክኒን የሚወሰዱ የወሊድ መቆጣጠሪያ እንክብል የሚወስዱ
እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩ መንገዶች በጥቂቱ ምክንያት ሊሆኑ ቢችሉም በተለይ በHPV ቫይረስ መጠቃት ግን በሁሉም
በበለጠ ተፅእኖ የሚያመጣ መንገድ ነዉ፡፡
ምልክቶች
የማህፀን ጫፍ ካንሰር ወደ ውስጠኛው የማህፀን በር ክፍል ገብቶ በደንብ ከመዛመቱ በፊት በተያዘችው ሴት ላይ ምንም ዓይነት ምልክቶች አያሳይም፡፡
ይህም ነው የማህፀን ጫፍ ምርመራ (papsmear) ለሁሉም ከ 22 ዓመት በላይ ለሆኑ ሴቶች ቢያንስ በዓመት አንዴ መመርመር በጣም አስፈላጊ እንደሆነ የሚነገረዉ፡፡
ከመዛመቱ በፊት ማወቅ ከተቻለ ከነጭራሹ ማጥፋት ይችላል፡፡ ይህ ሊሆን ካልቻለ ግን ምልክቶቹ
. ከወር አበባውጪከማህፀንየደምመፍሰስ
. በግንኙነት ጊዜ ህመም ወይም መድማት መኖር
. ሀይለኛ ሽታ ያለው የማህፀን ፈሳሽ መኖር
. እንዲሁም የማህፀን አካባቢ ህመም እንደ ምልክት ሊታይ ይችላል፡፡
ህክምና
አንዲት ሴት የማህፀን ካንሰር መያዟ ከታወቀ በኋላ በመጀመሪያ የተዛመተበት ደረጃ መታወቅ አለበት፡፡ ይህንን በመመርኮዝ ህክምናውን መምረጥና መስጠት ይቻላል፡፡
ደረጃውም የሚወስነው ከማህፀን ጫፍ ላይ ብቻ መሆኑን ወይም ከዛ አልፎ የሰውነት ማጣሪያ ዕጢዎች (lymphnodes) መግባቱን እንዲሁም ከዛም
አልፎ ወደ ሌሎች የሰዉኑት ክፍሎች መዛመቱን በማረጋገጥ ነው፡፡
እነዚህ ህክምናዎች የሚከተሉት ናቸው
በማህፀን ጫፍ ላይ የተወሰነ ከሆነ በቀዝቃዛ ናይትሮጅን አማካኝነት የካንሰሩን ቦታ የማጥፋት ህክምና (cryotherapy). ከዚህ አልፎ ወደ ሁለተኛው ክፍል ከገባ የጨረር እንዲሁም
የኬሞቴራፒ ህክምና ከማህፀን ጫፍ ቀዶ ጥገና ጋር በመጨረሻም ወደሌሎች የሰውነት ክፍሎች ከተዛመተ ሙሉ የማህፀን ማውጣት ቀዶ ጥገናን ጨምሮ የጨረርና
የኬሞቴራፒ ህክምና ሊያሳፈልግ ይችላል፡፡
ይህ ካንሰር ሳይከሰት ቀድሞ መከላከል ይቻላልን?
. የሂዩመን ፓፒሎማ ቫይረስ ክትባት በወቅቱ በመውሰድ
. የ HPV ቫይረስ ክትባት በመውሰድ ይህንን ከ270,000 በላይ ሴቶች በአመት የሚገድለውን አደገኛ ካንሰር መካላከል ትችላለች፡፡
. የአለም ጤና ጥበቃ ድርጅት ሁሉም ሴቶች አስራ አምስት አመት ሳይሞላቸው ክትባቱን እንዲውስዱ ይመክራል።
. የሂዩመን ፓፒሎማ ቫይረስ ክትባት የማህጸን በር ካንሰር አምጪ ከሆኑት የሂዩማን ፓፒሎማ ቫይረሶች ይከላከላል።
- የቅድመ ካንሰር ምርመራ
ማንኛዋም ሴት እድሜዋ 21 አመት ከሆነበት ወይም ግንኙነት ከጀመረችበት ከ3 አመት ጀምሮ በየ3 አመቱ ፓፕ ስሚር የተሰኘውን ምርመራ ብታደርግ።
ፓፕ ስሚር በማህጸን በር ላይ ጤናማ ያልሆኑ ቅድመ ካንሰር ለውጦች ካሉ ለመፈተሽ በጤና ባለሞያዎች የሚደረግ ምርመራ ነው። ጤናማ ያልሆኑ ለውጦች ከታዩ ክትትል እና አስፈላጊው ህክምና ይደረጋል ።