By: Fisseha Mulugeta(C2 student at Myungsung Medical College)

ፍስሃ ሙሉጌታ(ሚዩንግሱንግ ህክምና ኮሌጅ የ፬ አመት ተማሪ)

Reviewed/Approved  by: Dr. Fitsum Tilahun (Editor at Yetena Weg/ Nephrologist)

 

ኩላሊት እና የኩላሊት ድክመት ምንድነው?

ኩላሊቶቻችን በሰዉነታችን ውስጥ የሚመረቱ ጎጂ እና መርዛማ ምርቶችን ያስወግዳሉበተጨማሪም ውሃ ፈሳሾች ማዕድናትኬሚካሎች እና ኤሌክትሮላይቶችን(እንደ ሶዲየም ፖታስየም ወዘተ)መጠን ሚዛን በመጠበቅ ያገለግላሉ።  

ኩላሊቶቻችን እንደበፊቱ መስራት ሲያቅታቸው ወይም ሙሉ በሙሉ መስራት ሲያቆሙ የኩላሊት ድክመት ይባላል። 

  • የኩላሊት እጥበት (ዳያሊስስ)

የኩላሊት እጥበት (ዳያሊስስ) ማለት በኩላሊት  መድከም ምክንያት ሰውነት ውስጥ የሚጠራቀመው መወገድ ያለበት ቆሻሻ ምርት እና ከመጠን በላይ የሆነን ውሃ ከሰውነት በሰው ሰራሽ መንገድ የማስወግድ ሂደት ነው።

  • የኩላሊት እጥበት አይነቶች
  1. በደም ስር የሚሰጥ (ሂሞ ዳያሊስስ)
  • ከደም ስር ወደ ዳያሊስስ ማሽን በተጣጣፊ ቱቦ ይገናኛል፡፡ 
  • ማሽኑ ደሙን ባሉት ማጣርያ አካላቶች  እና ዲያልያዘር የሚባል ልዩ ብጥብጥ በመጠቀም ደምን ያጣራል። 
  • ከተጣራ በኋላ በሌላ ተጣጣፊ ቱቦ ወደ ደም ስር ይመለሳል፡፡ 
  • ሄሞዳያሊስስ ከመጀመሩ 4-8 ሳምንታት በፊት በክንድ ላይ ደም ወሳጅ (Artery) እና ደም መላሽ (Vein) ቧንቧዎችን በቀላል ቀዶ ጥገና መገናኘት አለባቸው፡፡ 
  • ሄሞዲያልሲስ በአብዛኛው ጊዜ በሳምንት ሶስቴ  ይካሄዳል፡፡
  • እያንዳንዱ እጥበት አራት ሰዓታትን አካባቢ ይፈጃል።

2.የሆድ ውስጥ የሚደረግ ኩላሊት እጥበት (ፔሪቶኒያል ዲያላሲስ)

  • በመኖሪያ ቤት ውስጥ የሚደረግ የኩላሊት እጥበት አይነት ነው። ታካሚው ስራውን እየሰራ ቤት ሆኖ ይሄን አይነት ዳያልሲስ ማድረግ ይችላል። ይህ ሕክምና አገልግሎት በሀገራችን ውስጥ በአሁኑ ሰዓት የለም።
  • ፔሪቶንየም የውስጠኛውን የሆድ ክፍል የሚሸፍን ሽፋን ነው።
  • ፔሪቶንየም ፈሳሽ በከፊል የሚያሳልፍ ወንፊት መሳይ ሲሆን በደም ውስጥ የሚገኙ አላስፈላጊ የሰውነት ቆሻሻዎችንና መርዞችን ማሳለፍ ይችላል።
  • በሆድ ውስጥ አነስተኛ ቀዳዳ መከፈት አለበት፡፡ 
  • ካቴተር የሚባል ቀጭን ቱቦ ወደ ተከፈተው ቀዳዳ ውስጥ ይገባልይህ የዲያሊሲስ ፈሳሽ (ዲያልያዘር) በሆድዎ ውስጥ እንዲገባ ያስችለዋል
  • ፈሳሹ ከገባ በኋላ ቆሻሻ ምርቶች በፔሪቶንየም  አልፈው በሌላ ካቴተር ይወጣሉ፡፡

ይህ የመለዋወጥ ሂደት አብዛኛውን ጊዜ ለማጠናቀቅ 30 እስከ 40 ደቂቃዎችን ይወስዳል።

  • የኩላሊት እጥበት የሚያደርግ ሰው ማድረግ የሚገባው ጥንቃቄ
    • የደም ወሳጅ (Artery) እና ደም መላሽ (Vein) ቧንባ መገናኛ
      • በሳሙና እና በሞቀ ውሃ በየቀኑ ይጠቡ፡፡
      • ከዲያሊሲስ ሕክምና በፊት አካባቢውን አይቧጭሩ ወይም አይንኩ፡፡
      • ማንም ሰው ይህንን ክንድ ደም ለመውሰድ ወይም ደም ግፊት ለመለካት እንዲጠቀምበት አለመፍቀድ፡፡
      • በመደበኛነት ሲሰራ በአካባቢው ላይ ንዝረት ሊሰማዎት ይችላል፤ ንዝረት ካልተሰማዎት ለሐኪምዎ ወይም ለነርስዎ ያሳውቁ።
    • ሐኪም ወይም ነርስ ካቴተርዎን በፋሻ  ይሸፍናሉይህ ኢንፌክሽንን ለመከላከል አስፈላጊ ነው፤ ይህንን ለማስወገድ ወይም ለመቀየር ቤት ውስጥ አይሞክሩ፡፡
    • በየቀኑ ኪሎ ይመዘኑኩላሊትዎ በማይሰራበት ጊዜ ፈሳሽ በሰውነትዎ ውስጥ ይሰበሰባል። ኪሎዎ ከወትሮው የበለጠ ከጨመረ ለሐኪምዎ ወይም ለነርስዎ ያሳውቁ፡፡
  • ልዩ አመጋገብን ይከተሉየሚጠጡትን ፈሳሽ መጠን መወሰን ያስፈልግዎታል።  እንዲሁም ብዙ ሶዲየምፖታሲየም እና ፎስፎረስ የያዙ ምግቦችን መብላት የለቦትም፡፡

ለምን በዳያሊስስ ላይ ያሉ ሰዎች አመጋገባቸውን መከታተል አለባቸው?

  • ዲያሊሲስ የኩላሊትን ሥራ የሚተካ ሕክምና ነው። 
  • ዳያሊሲስ ግን እንደ ጤናማ ኩላሊት ያህል አያጣራም።
  • በተጨማሪም መደበኛ ኩላሊቶች ቀኑን ሙሉ በየቀኑ ይሠራሉ ነገር ግን  የኩላሊት ድክመት ያለባቸው ሰዎች ብዙውን ጊዜ የኩላሊት እጥበት በሳምንት 3 ጊዜ ብቻ በማዕከል ያደርጋሉ። 
  • በመብላትና በመጠጣት ብዙ ውሃ፣ ጨው ወይም ሌሎች ንጥረ ነገሮችን ስለሚያገኙ እነዚህ ነገሮች በሰውነት ውስጥ ሊከማቹ ይችላሉ።  
  • ብዙ ፈሳሽ የደም ግፊትን ከፍ ሊያደርግ እና ልብ ከአቅም በላይ እንዲሠራ ያደርገዋል። የሰውነት ክብደት መጨመር እብጠት እና የመተንፈስ ችግርም ሊያስከትል ይችላል፡፡

በአመጋገብ ላይ ምን ለውጦች ማድረግ አለብኝ?

ፈሳሾች 

  • አብዛኛዎቹ በዲያሊሲስ ላይ ያሉ ሰዎች ምን ያህል ፈሳሽ እንደሚበሉ እና እንደሚጠጡ መወሰን አለባቸው። ሲቀልጡ ፈሳሽ የሚሆኑትም (አይስ ክሬም) እንደ ፈሳሽ ይቆጠራሉ፡፡ 
  • አንዳንድ ፍራፍሬዎች እና አትክልቶች በውስጣቸው ብዙ ፈሳሽ አላቸው። ከእነዚህም መካከል ሐብሐብ፣ ኮክ ዱባ እና ሰላጣ ይጠቀሳሉ።
  • እብጠትና የሽንት ፈሳሽ መቀነስ ያጋጠማቸው ታካሚዎች የሚወስዱትን የፈሳሽ መጠን እንዲገድቡ ይደረጋል። እብጠትን ለመቀነስ 24 ሰዓታት ውስጥ የሚወሰደው የፈሳሽ መጠን በየቀኑ ከሚመረተው የሽንት መጠን ያነሰ መሆን አለበት።
  • እብጠት የሌላቸው ህመምተኞች ከመጠን በላይ ፈሳሽ እንዳይኖር እንዲሁም የፈሳሽ እጥረት እንዳይከሰት የሚወስዱት የፈሳሽ መጠን በቀን የቀደመውን ቀን የሽንት መጠን ላይ 500 ሚሊ ሊትር በመደመር ይሆናል።

ከተጠማሁስ?

  • ከተጠማቹ ነገር ግን ፈሳሽን መገደብ ካለባቹ እነዚህን ምክሮች ሞክሩ፡
    • ከመጠጣት ይልቅ በረዶ ይምጠጡ። ምክንያቱም በረዶ ለረጅም ጊዜ ይቆያል(ነገር ግን በረዶም ፈሳሽ መሆኑንስተውሉ)።
    • ማስቲካ ያኝኩ ወይም ጠንካራ ከረሜላ ይምጠጡ፡፡
    • የቀዘቀዙ ወይኖች ይብሉ፡፡
    • አፍዎን በውሃ ይግሞጥሞጡ ነገር ግን አይዋጡ፡፡

 ሃይል ሰጪ ምግቦች /ካርቦሃይድሬት

  • ካርቦሃይድሬት ለሰውነት ዋናው የሃይል ምንጭ ነው። ከስንዴ ጥራጥሬ ሩዝ ድንች ፍራፍሬዎች ስኳር ማር ኩኪሶች ኬኮች ጣፋጮች እና ከመጠጦች ውስጥ ይገኛሉ።
  • የስኳር ህመምተኞች እና ከመጠን በላይ ውፍረት ያላቸው ታካሚዎች ሃይል ሰጪ ምግቦችን መጠን መገደብ ያስፈልጋቸዋል፡፡

ሶዲየም 

  • ይህ በጠረጴዛ ጨው ውስጥ ዋናው ንጥረ ነገር ነው፡፡
  • አብዛኛዎቹ በዳያሊስስ ላይ ያሉ ሰዎች የሚበሉትን የሶዲየም መጠን መገደብ አለባቸው።
  • ምክንያቱም ብዙ ሶዲየም መብላት የደም ግፊትን ስለሚጨምር ነው።
  •  እንዲሁም ከሚገባው በላይ ውሃ ሊያስጠማዎት እና ሊያስጠጣዎት ይችላል፡፡
  • የጠረጴዛ ጨው(የምግብ ጨው) የመጋገሪያ ዱቄት፣የታሸጉ ምግቦች፣ቅመማ ቅመሞች የሶያ ሶስ አኩሪ አተር እና ክኖር ፣ አትክልቶች(እንደ ጎመን አበባ ጎመን ስፒናች ራዲሽ ቢትሮት እና የበቆሎ ቅጠል) የመሳሰሉት በሶዲየም የበለጸጉ ምግቦች ናቸው፡፡

ፖታስየም

  • ይህ የልብ ምትዎን የሚቆጣጠር ንጥረ ነገር ነው። 
  • ዳያሊስስ ላይ ያሉ ሰዎችፖታስየም መጠን መወሰን አለባቸው፡፡
  • በጣም ብዙ ፖታስየም በሰውነት ውስጥ ከተከማቸ የልብ ምት መዛባት ሊያመጣ ይችላል፡፡
  • የበሰለ ሙዝ፣ኮኮናት ካስታርድ አፕል ጉስቤሪ ጉአቫ፣ ብሮኮሊ፣ጣፋጭ ድንች፣ ቀይ እና ጥቁር ባቄላ የመሳሰሉት በፖታስየም የበለጸጉ ምግቦች ናቸው፡፡

    ፎስፈረስ 

  • ይህ በብዙ ምግቦች ውስጥ የሚገኝ ንጥረ ነገር ነው፡፡
  • እንደ ወተት፣ ሌሎች የወተት ተዋህጾዎች፣ ለውዝ፣ ባቄላ፣ ጉበት እና ቸኮሌትን የመሳሰሉት ምግቦች ከፍተኛ መጠን ያለው ፎስፈረስ አላቸው፡፡
  • በዲያሊሲስ ላይ ያሉ ሰዎች ከፍተኛ መጠን ያለው ፎስፈረስ ያላቸውን ምግቦች መተው አለባቸው፡፡

የገንቢ /ፕሮቲን

  • ፕሮቲን ጡንቻዎ ጠንካራ ሆኖ እንዲቆይ ይረዳል፡፡ 
  • ብዙ ፕሮቲንላቸው ምግቦች መካከል ስጋ፣ ዶሮ፣ አሳ እና እንቁላል ይገኙበታል።

የኩላሊት ህመምተኞች ከፍተኛ የገንቢ/ ፕሮቲን አመጋገቦች ከመውሰድ መቆጠብ አለባቸው።

 

የጤና ወግ 

ጠቃሚ እና የተረጋገጠ መረጃ ለጤናዎ ።

የጤና ወግን በነዚህ ሊንኮች መከታትል ይችላሉ ።

https://linktr.ee/Yetena_Weg