የጡት ካንሰር በሴቶች ላይ ሊከሰቱ ከሚችሉ ካንሰሮች አንዱ ነው። በአለም አቀፍ ሁኔታ በሴቶች ላይ ከሚከሰቱ የካንሰር አይነቶች የጡት ካንሰር በ 1 ኛ ደረጃ ይቀመጣል።
የጡት ሴሎች (ህዋሶች ) ከተለመደው ወጣ ባለ እና ጤናማ ባልሆነ መልኩ ሲያድጉ እና ሲባዙ ይፈጠራል ።
የጡት ካንሰር በአብዛኛው የሚከሰተው በሴቶች ቢሆንም በወንዶች ላይም ሊከሰት ይችላል።
- የጡት ካንሰር አጋላጭ ምክንያቶች ምንድን ናቸው ?
- የጡት ካንሰር በቅርብ ቤተሰብ መኖር
- ለራዲዬሽን (ጨረር ) መጋለጥ
- ሲጋራ ማጨስ
- አልኮል መጠጣት
- ከፍተኛ ውፍረት
- ለኤስትሮጅን ሆርሞን ለረጅም ጊዜ ተጋላጭ መሆን – ማለትም
- -የወር አበባ በልጅነት መጀመር ( ከ12 አመት በታች ) እና እስከ ረጅም እድሜ መቆየት ( ከ 55 አመት በላይ)
- -ከማረጥ በኋላ የሆርሞን እንክብሎችን መውሰድ
- -ልጅ አለመውለድ ወይም የመጀመሪያ እርግዝና ከ30 አመት በኋላ መሆን
- የጡት ካንሰርን ለመከላከል ምን ማድረግ ይቻላል?
- የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ
- ክብደትን መቆጣጠር
- የከብት ስጋ አለማዘውተር
- ሲጋራን አለማጨስ
- የጡት ካንሰር ምልክቶች ምንድን ናቸው
- የጡት ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል እብጠት
- የጡት ቆዳ መሰርጎድ
- የጡት ጫፍ ወደውስጥ መገልበጥ
- በብብት ስር የንፍፊት እብጠት
- የጡት ፈሳሽ (ከወተት ውጪ)
- በጡቴ ላይ ያሉ ለውጦችን ለማወቅ ምን ማድረግ አለብኝ ?
ራስን በራስ ጡትን በመዳሰስ እብጠት መኖር አለመኖሩን መመርመር
ልብ በይ
- ጡት ላይ እብጠት ካለ ህመም ባይኖረውም እንኳን ሃኪም ማየት ያስፈልጋል።
- ይህ በህክምና ተቋማት በህክምና ባለሞያዎች የሚደረግ ምርመራን ስለማይተካ ቅድመ ምርመራዎችን በእጅ የሚዳሰስ እብጠት ባይኖርም እንኳን ማድረግ ያስፈልጋል ።( በእጅ በመዳሰስ ለመለየት የማይቻል እብጠት እና ጤናማ ያልሆነ እድገት ሊኖር ስለሚችል)
- የጡት ካንሰር ምርመራ አለው?
አዎ ። የጡት ካንሰር ካንሰር መኖር አለመኖሩን ለማወቅ፣ ካለም በዝቅተኛ ደረጃ ላይ ለማግኘት የሚያስችሉ ምርመራዎች አሉ።
- የጡት ካንሰር መፈተሻ ምርመራዎች ምንድን ናቸው ?
- ማሞግራፊ
ከአርባ አመት በላይ ያሉ ሴቶች በየአመቱ የማሞግራፊ ምርመራ ማድረግ አለባቸው
- እንደየአስፈላጊነቱ ሌሎች ምርመራዎችም ሊደረጉ ይችላሉ።
- የጡት ካንሰር ህክምና አለው?
አዎ። የህክምናው አይነት እንደ ካንሰሩ አይነት ይወሰናል
በዶ/ር ማህሌት አለማየሁ
ትዊተር: @MahletAlemayeh7
ምንጭ: https://www.cancer.gov/types/breast/patient/breast-screening-pdq