March 13 ,2020

መጋቢት 3 ቀን 2012 አ.ም. የአለም የጤና ድርጅት ባስተላለፈው ሰርኩላር መሰረት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በ109 ሀገራት (9 የአፍሪካ ሀገራትን ጨምሮ) ተሰራጭቷል፡፡  ይሄ ቁጥር በየጊዜው አየጨመር የሚሄድ ስለሆነ በየጊዜው የሚውጡትን መረጃዎች መከታጥል ይጠቅማል ፡፡

ከነዚህ 109 ሀገራት ውስጥ የኢትዮጵያ የአየር መንገድ በቀጥታ በረራ (በሌሎች የአየር መንገዶች በቦሌ አለምአቀፍ ኤርፖርት ትራንዚት የሚያደርጉትን ሳይጨምር) ከ42 ሀገራት ጋር ይገናኛል፡፡

ዛሬ ጥዋት ደግሞ በ ኢትዮጲያ አና በ ጎረቤት ሀገሮች ኬንያ አና ሱዳን ጨምሮ መከሰቱ ተረጋግጧል ።

አሁን ያልበትን ድርጃ ለማወቅ ይሄንን  የአለም የጤና ድርጅት ድረገፅ ማየት ትችላላችሁ  ፡፡ ወይም ይሄንን የኒውዮርክ ታይምስ የ ኮሮና ቫይረስን በተመለከተ የሚያወጣውን መርጃ መከታተል ትችላላችሁ ፡፡

በ አገራችን ያለውን ሁኔታ ለማወቅ የ ጤና ጥበቃ አና የኢትዮጵያ ህብርተሰብ ጤና የሚያወጧቸውን መረጃዎች ይከታተሉ ፡፡

ትክክለኛ መረጃን ብቻ አናጋራ 

መደናግጥ ሳይሆን ጥሩ ጥንቃቄ አና  የመስፋፋት አድሉን መቀንስ የሚያስችሉ አርምጃዎች መውሰድ ብቻ ነው የሚያስፈልገው ፡፡

የህመሙ ምልክቶች አነዚህ ሲሆኑ 

የ ኮሮና ቫይረስ እንዴት እንደሚሰራጭ የባለሙያዎች ግንዛቤ አሁንም ውስን ነው ፣ ግን አነዚህ አራት ምክንያቶች ለህመሙ አንደሚያጋልጡ አስካሁን ያሉ ጥናቶች ያሳያሉ ፡፡

ከህመምተኛው  ምን ያህል ርቀት ላይ ነዎት?

ከ ታመመ ሰውጋር ለምን ያህል ጊዜ ቆይተዋል? 

የታመመ ሰው በቅበርት አርስዎ ላይ በማሳል ወይም በመንነካካት የቫይረስ ነጠብጣቦችን ወደ አርስዎ አሰራጭታል ወይ? 

እና ፊትዎን ምን ያህል ጊዜ ይነካሉ ?

ስርጭቱን ለመቀነስ አና አርሳችንን ከበሽታ ለመከላከል 

አጃችንን መታጠብ በውሃ በትንሹ ቢያንስ ለ 20 ሰከንዶች ከዚያም በንጹህ ፎጣ ያድርቁ ወይም በአየር እንዲደርቁ ያድርጓቸው ፡፡

ከታመሙ ሰዎች ይራቁ ፡፡ ጉንፋን ወይም ጉንፋን የሚመስሉ ምልክቶችን ከሚያሳይ ከማንኛውም ሰው ስድስት ጫማ ወይም ሁለት ሜትር ያህል  ለመራቅ ይሞክሩ እና

ከታመሙ ወደ ሥራ አይሂዱ ፡፡

በሚያስነጥሱበት እና በሚያስሉ ጊዜ አፍና አፍንጫዎን ይሸፍኑ፡፡ 

ፊትዎን ባልታጠበ እጅዎ አይነካኩ፡፡ 

8335 ላይ በመደወል እና በማሳወቅ የህመሙ ምልክቶች ከታዩ ሪፖርት መደረግ እና አስፈላጊው መከላከል እንዲሁም ህክምና መደረግ አለበት፡፡ 

የዛሬው እለታዊ መልእክት በተጨማሪ በ ኢትዮጲያ  የለይቶ ማቆየት ህክምና ማእከሉን በጎ ስራዎች እና ያጋጠሙትን ችግሮች ይመለከታል፡፡ 

ዮአና ሉንጉ የተባሉ አንዲት የወጭ ሀገር ዜጋ በትዊተር ገፃቸው ላይ በማእከሉ የተደረገላቸውን ህክምና አጋርተውናል

በህመሙ ተጠርጥረው የተለዩት ተጓዥ ለአንድ ለይቶ አቆይቶ የማከም ማእከል የሚያስፈልጉት ብቁ ባለሙያዎችን እንዳዩ መስክረዋል፡፡ ተገቢ በሆነ ስነምግባር እንደተስተናገዱ ገልፀዋል፡፡ እያንዳንዱ የተጠረጠረ ተጓዥ ለብቻው ክፍል ይሰጠዋል፡፡ ነገር ግን የመፀዳጃ ቤቶችን በጋራ ይጠቀማሉ፡፡ የኮሮና ቫይረስ በማስነጠስ እና በማሳል ከመተላለፍ በተጨማሪ ያስነጠስናቸው ብናኞች እጃችን ላይ በማረፍ እጅ ለእጅ በሚደረግ እንዲሁም በእጅ እና በግኡዝ አካል (የመፀዳጃ ቤቶች እቃዎችን ጨምሮ) በሚደረግ ንክኪም ይተላለፋሉ፡፡ ስለዚህም በተቻለ የመፀዳጃ ቤቶችን የጋራ አጠቃቀምን ማስቀረት ያስፈልጋል፡፡