ትናንት ከኢትዮጲያ ጤና ጥበቃ ሚንስቴር እንደተረዳነው የተረጋገጠ የመጀመሪያው የ COVID 19 ህመምተኛ በአዲስ አበባ ተገኝቷል።
ከህመምትኛው ጋር ቀጥታ ግንኙነት ያላቸውን ሰዎች የማግኘት እና ከህብረተስቡ የመለየት ስራ እየተካሄደ እንደሆነ የጤና ጥበቃ በመግለጫው አሳውቆናል።
የኮሮና ቫይረስ አሁን ያልበትን ደርጃ ለማወቅ ይሄንን የአለም የጤና ድርጅት ድረገፅ ማየት ትችላላችሁ ፡፡ ወይም ይሄንን የኒውዮርክ ታይምስ የ ኮሮና ቫይረስን በተመለከተ የሚያወጣውን መርጃ መከታተል ትችላላችሁ ፡፡
በ አገራችን ያለውን ሁኔታ ለማወቅ የ ጤና ጥበቃ አና የኢትዮጵያ ህብርተሰብ ጤና የሚያወጧቸውን መረጃዎች ይከታተሉ ፡፡
ትክክለኛ መረጃን ብቻ አናጋራ
ከ በሽታው አዲስነት አንፃር በላብራቶሪ የማረጋገጥ አቅም እኛም ጋር ሆነ በአደጉት ሀገራት የተወሰነ ነው። በአሁን ሰአት ተጨማሪ ምርመራ የሚደረግላቸው ሰዎች የሚከተሉትን የሚያሟሉ ናቸው ።
በቅርብ ዶ/ር ትንሳኤ 10 ነጥቦችን ጠቅሶ እንዳስረዳን በኛ ሀገር ተላላፊ በሽታዎችን የመከላከል እና የመቆጣጠር አቅማችን ደካማ ነው።
እነዚህን ችግሮች ነቅሶ አውጥቶ ቀጣይ እርምጃዎችን ማቀድ ያስፈልጋል።
በሽታው ከተከሰተ እና ከተስፋፋም በኋላ በየቀኑ በሽታውን የመከላከል እና የመቆጣጠር እርምጃዎች መውሰድ አለብን። የኮሮና ቫይረስን የመስፋፋት ፍጥነት መቀነስ ( Flattening The Curve) የህክምና ተቋሞቻችን በህሙማን እንዳይጨናነቁ ፣ ያሉን ውስን የፅኑ ህሙማን መታከሚያ አልጋዎች እና የአርቴፊሻል መተንፈሻ ማሽኖች (Mechanical Ventilators) በተገቢው መልኩ ለህሙማን እንዲዳረሱ ይረዳል።
በየቀኑ እጃችሁን ስትታጠቡ ፣ ተገቢውን ርቀት በመሀከላችሁ ስትጠብቁ እራሳችሁን ከበሽታ ከመከላከል ባለፈ የበሽታውን ስርጭት ፍጥነት በማለዘብ ህሙማን ተገቢውን ህክምና እንዲያገኙ እያገዛችሁ ነው።
ይሄንን ፈተና አብረን እንወጣዋለን።