የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል ማህበራዊ ኃላፊነትዎን ይወጡ።
መቆየት
በጣም አስፈላጊ ለሆነ እንቅስቃሴ በስተቀር በ ቤት ውስጥ በመቆየት የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል ማህበራዊ ኃላፊነትዎን ይወጡ። የራስዎንም ሆነ የሌሎችን ሕይወት ከበሽታ ይከላከሉ ።

መራራቅ
ወደውጭ በሚወጡበት ማንኛውም አጋጣሚ አካላዊ ርቀትዎን ጠብቀው መቆየት እራስዎንም ሆነ ሌሎችን ከኮሮና ቫይርስ መከላከል ይችላሉ።

መሸፈን
ወደውጭ በሚወጡበት ማንኛውም አጋጣሚ ሁልግዜም የፊት መሸፈኛ ማስክ በማድረግ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል ማህበራዊ ኃላፊነትዎን ይወጡ። የፊት መሸፈኛ ማስክ በማድረግ የራስዎንም ሆነ የሌሎችን ሕይወት ከበሽታ ይከላከሉ ።

መታጠብ
ስዎችንም ሆነ ሌሎች የኮሮና ቫይረስን ሊያስተላልፉ የሚችሉ ግዑዝ ነገሮችን በነኩበት አጋጣሚ ሁሉ እጅዎትን በአግባቡ በመታጠብ እና ፊትዎን ባለመንካት እራስዎን ከበሽታ ይከላከሉ ።

መተሳሰብ
ይሄን የጋራ የሆነ ፈተና እርስ በርስ በመተጋገዝ እና በመረዳድት እንወጣ።
በዚህ ወረርሽኝ ከስራቸው የቀሩ እና የተቸገሩ ወገኖችን እንርዳ።
በበሽታው የተያዙትን ሰዎች ምንም ማግለል ሳይኖር በተገቢው ጥንቃቄ እንከባከባቸው ።
ከበሽታው አገግመው ከመታከሚያ ማእከል የወጡ ሰዎች በሽታውን ወደኛ ስለማያስተላልፉ ከማንኛውም ማህበራዊ ተሳትፎ አናግላቸው ።
ለብቻቸው የተቀመጡ ወገኖቻችንን በመደወል እና በሌሎችም መንገዶች ከብቸኝነት እንጠብቃቸው ። ስንጠሳሰብ የሁላችንም የአእምሮ ጤና ይጠበቃል።
