የደም ግፊትን እንዴት መለካት ይቻላል?
የደም ግፊት፣ በአብዛኛው የጤና ጣቢያ ውስጥ፣ በጤና ረዳቶች እና ሃኪሞች ሲለካ ይታያል። ነገር ግን፣ የደም ግፊትን በቤት ውስጥ መለካት በሚያስችሉ ቀላል መለኪያዎች በመጠቀም መለካት ይቻላል። በዚህ ድረ ገጽ፣ በጤና ጣቢያዎች ውስጥም ሆነ በቤት ውስጥ የደም ግፊት በሚለካበት ጊዜ ሊደረጉ የሚገባቸውን ጥንቃቄዎች በዝርዝር ተቀምጠዋል።
ደም ግፊታችንን ስንለካ ልናደርጋቸው የሚገቡ ጥንቃቄዎች
-
1. ትክክለኛ መጠን ያለው የደም ግፊት መሳሪያ መጠቀም። እጃችን ላይ የጠበበ የደም ግፊት መለኪይ መጠቀም የደም ግፊታችንን ያለ አግባብ ከሁለት እስከ አስር ነጥብ ሊጨምረው ይችላል።
2. የደም ግፊታችንን የምንለካበት እጃችን በልብስ መሸፈን የለበትም። በልብስ ላይ ድርቦ መለካት የደም ግፊትን ከአምስት እስከ አስር ነጥብ ይጨምረዋል።
3. እጃችን ስእሉ ላይ እንደሚታየው በልባችን ትይዩ ሆኖ ጠረቤዛ ላይ ደገፍ ማለት አለበት። ደገፍ ያላለ እጅ አለ አግባብ እስከ አስር ነጥብ ድረስ የደም ግፊትን በመጨመር ሊያሳስተን ይችላል።
4. እግራችንን ማጣመር የለብንም። ስእሉ ላይ እነደሚታየው ዘና ብለን ነው መቀመጥ ያለብን። እግራችንን በምናጣምርበት ጊዜ አለ አግባብ ከሁለት እስከ አስር ነጥብ ድረስ የደም ግፊትን በመጨመር ሊያሳስተን ይችላል።
5. ጀርባችን ወንበራችን ላይ እና እግራችን መሬት ላይ ደገፍ ማለት መቻል አለበት። ይህን ሳናደርግ ስንቀር አለ አግባብ እስከ ስድስት ነጥብ አምስት ነጥብ ድረስ የደም ግፊትን በመጨመር ሊያሳስተን ይችላል።
6. መጸዳጃ ቤት መሄድ ካለብን ደም ግፊታችንን ከመለካታችን በፊት መሆን አለበት። ሽንታችን ይዞን ደም ግፊትን መለካት አለ አግባብ እስከ ስድስት አስር ነጥብ ድረስ የደም ግፊትን በመጨመር ሊያሳስተን ይችላል።
7. የደም ግፊታችንን በምንለካበት ጊዜ ማውራት የለብንም፣ የሚለካውም ሰው ዝም ማለት አለበት። ጫጫታ ያለበት ቦታ መሆን የለበትም። ማውራት እና ጫጫታ አለ አግባብ እስከ አስር ነጥብ ድረስ የደም ግፊትን በመጨመር ሊያሳስተን ይችላል።
8. ደም ግፊታችንን ከመለካታችን ሰላሳ ደቂቃ በፊት ሲጋራ ማጤስ ፣ ቡና መጠጣት ፣ የአካል እንቅስቃሴ ማድረግ፣ አልኮል መጠጣት ማናቸውንም አነቃቂ መጠጦች ወይም ቅጠሎች መጠቀም የለብንም ።
የደም ግፊት ንባብ
እንደ አሜሪካ የልብ ህክምና ማህበር አዲስ ጥናት፣ የደም ግፊት መጨመርን እንደ እንደሚከተለው ይከፋፍለዋል። በቤት ውስጥ የተለካችሁትን የደም ግፊት መጠን በመመዝገብ ሀኪምችሁን አማክሩ። ከእናንተ አናኗር ፣እድሜ እና አጠቃላይ ጤና ጋር የሚሄድ የህክምና እቅድ ሀኪማችሁ ይስጣቹሃል/ትሰጥችሁሃለች።
የደም ግፊት | ሲስቶሊክ (የላይኛው) | ደዳያስቶሊክ (ታችኛው) | |
---|---|---|---|
ትክክለኛ የደም ግፊት | 120 እና ከዛ በታች | 90 እና ከዛ በታች | |
በመጠኑ የጨመረ | ከ120 እስከ 130 | ወይም | ከ80 እስከ 90 |
አንደኛ ደረጃ | ከ140 እስከ 159 | ወይም | ከ90 እስከ 99 |
ሁለተኛ ደረጃ (በጣም ከፍ ያለ) | 160 ወይም ከዛ በላይ | ወይም | 160 ወይም ከዛ በላይ |