ዶ/ር ትንሳኤ አለማየሁ (ዲሴምበር 19, 2020 ላይ በምናውቀው ተመስርቶ)

 ክትባቶቹ እንዴት ነው የሚሰሩት 

የ BioNTech/Pfizer ክትባት የ RNA ክትባት ሲሆን የ SARS-CoV-2 ን RNA ወደ ሰውነታችን ህዋሶች (cells) በማስተዋወቅ በቫይረሱ ውጫዊ አካል የሚገኙትን ፕሮቲኖች የገዛ ህዋሶቻችን እንዲያመርቱ ያደርጋል፡፡ ያንን ተከትሎ ሰውነታችን በውስጣችን የኮቪድ19 ህመም ተከስቷል በሚል ተረድቶ የበሽታ መከላከያ እርምጃዎችን ተግባራዊ ያድርጋል፡፡

የ Pfizer  እና Moderna mRNA ክትባቶችን አሰራር ለማወቅ ይህችን አጠር ያለች ቪድዮ ይመልከቱ

https://youtu.be/oMXGGmBfkf8

 ውጤታማነታቸው ምን ያህል ነው ? ደህንነታቸውስ ?

በሶስት ሳምንት ልዩነት ሁለት ዙር ክትባቱን ከወሰዱ ሰዎች ውስጥ በነበራቸው የ 2 ወር ክትትል ጊዜ የኮቪድ19 ህመም ተጋላጭታቸው በ95 ከመቶ ቀንሷል፡፡ ይህም የመከላከል አቅም በተለይ ከበድ ያለ የኮቪድ19 ህመም መከላከል ላይ ታይቷል፡፡ ባብዛኛው የታዩ የጎንዮሽ ምልክቶች የተወጉበት ቦታ ህመም፣ ራስ ምታት፣ ድካም እና ቁርጥማት ናቸው፡፡ ከክትባቱ ጋር በተገናኘ ካልተመለሱ ጥያቄዎች አንደኛው ከሁለት ወር ክትትል በኋላ ያለው የክትባቱ የመከላከል አቅም ነው፡፡ ምክንያቱም የጥናቱ ተሳታፊዎች ክትትል የተደረገላቸው ለ2 ወር ብቻ ስለሆነ ነው፡፡ በዛው ልክ ግን ተመሳሳይ ውጤታማነትን ይዞ ከቀጠለ ታሪካዊ ከሆኑ (groundbreaking) የህክምና ግኝቶች ይመደባል፡፡ የCOVID19 ህመም ከተገኘ ዲሴምበር 1, 2019 በኋላ የመጀመርያዋ ሰው እስክትከተብ ድረስ 1 አመት ብቻ በመፍጀት (ዲሴምበር 11, 2020) ከሁሉም በፍጥነት የተገኘው ክትባት ያሰኘዋል፡፡  

የ Moderna ክትባት የ BioNTech እና የ Pfizer ካምፓኒዎች ካመረቱት ክትባት ጋር በተመሳሳይ ሁኔታ የሚሰራ ሲሆን ዲሴምበር 18, 2020 ለሰዎች እንዲሰጥ ፍቃድ አግኝቷል፡፡ በ1 ወር ልዩነት ሁለት ዙር ክትባቱን ከወሰዱ ሰዎች ውስጥ በነበራቸው የ 2 ወር ክትትል ጊዜ የኮቪድ19 ህመም ተጋላጭታቸው በ94.5 ከመቶ ቀንሷል፡፡ የ Moderna ክትባት የጎንዮሽ ምልክቶች ከ BioNTech/Pfizer ክትባት ጋር ተመሳሳይ ቢሆንም በመደበኛ ሙቀት የማይጎዳ እና እንደ አፍሪካ እና ደቡብ እስያ ላሉ የኤሌክትሪክ/የማቀዝቀዣ አገልግሎት በስፋት ለሌላቸው ቦታዎች ተመራጭ ይሆናል፡፡ የ BioNTech/Pfizer ክትባት እስኪሰጥ በ -70 ሴንቲግሬድ መቆየት ሲገባው የ Moderna ክትባት በመደበኛ ሙቀት ማቀዝቀዣ እስኪሰጥ በ +4 ሴንቲግሬድ መቆየት ይችላል፡፡ ልክ እንደ መጀመርያው ክትባት ግን ለረዥም ጊዜ መጥቀሙ አይታወቅም፡፡ ስለዚህም በእርግጠኝነት እስኪታወቅ ድረስ ማስክ ማድረግ ማቆም የለብንም፡፡ በሁለቱም ክትባቶች ጥናት ውስጥ ስላልተካተቱ ነፍሰጡሮች፣ ህፃናት፣ የከረመ የበሽታ መከላከያን የሚጎዳ ህመም ያለባቸው ሰዎች (Immunocompromised people) ላይ ክትባቱን የሚሰጡት ውጤት አይታወቅም፡፡

ሌሎች ክትባቶችስ ?

ሶስተኛው ክትባት የAstrazeneca ክትባት ሲሆን የህመም መከላከያ መንገዱ ከበፊቶቹ ይለያል፡፡ ሰውነት ውስጥ ገብተው መባዛት የማይችሉ ቫይረሶችን የያዘ ክትባት ሲሆን በ1 ወር ልዩነት ሁለት ዙር ክትባቱን ይሰጣል፡፡ የመጨረሻ ሪፖርቱ ማርች 23, 2021 ይጠበቃል፡፡ 

በቻይና የተመረተው የ Sinopharm ክትባት ከAstrazeneca ክትባት ጋር ተመሳሳይ አሰራርን ይከተላል፡፡ በራሽያ የተዘጋጀው የ SputnikV ክትባትም በሶስት ሳምንት ልዩነት ሁለት ዙር ክትባቱን ይሰጣል፡፡ የሁለቱም መሰረታዊ የጥናት መነሻ ሀሳብ ከሌሎቹ ጋር ቢቀራረብም ልክ እንደ Astrazeneca ክትባት የመጨረሻ ሪፖርታቸው ስላልተገመገመ ዝርዝር ውጤታማነታቸው (መቼ ሪፖርታቸው እንደሚወጣ ጭምር አይታወቅም፡፡

እስካሁን ለ ሰዎች በመሰጠት ላይ ያሉ  የ ኮቪድ 19 ክትባቶች በንፅፅር ሲታዩ

የጤና ወግ

በመረጃ የተመሰረተ ሕክምና ብቻ ።  

………………………………………………………………………………………………………………………..

ይህ የጤና ወግ ድረ ገፅ ነው።
ስለ ጤንነታችሁ ማወቅ የምትፈልጉትን መረጃ የምታገኙበት ፣ በህክምና ባለሙያዎች የሚዘጋጅ የመረጃ ምንጭ ነው።
ሁልግዜም ከሀኪማችሁ ተማከሩ፣ ተጨማሪ መረጃ ከፈለጋችሁ የኛን ድረ ገፅ ጎብኙ።

በጥናት የተደገፈ መረጃ ብቻ እናቀርባለን።

የህክምና ባለሙያዎች ለህሙማኖቻችሁ የሚሆን የሚነበብ መረጃ ከፈለጋችሁ ይህን ግፅ ጠቁሟቸው። ህሙማኖቻችሁ እንዲያውቁት የምትፈልጉትን ነገር መረጃ ጠቅሳችሁ ፃፉልን፣ ስምችሁን ጠቅሰን እናወጣለን። የህክምና ተማሪዎች እንዲጽፉ እናበረታታለን።

በተጨማሪም በጤና ወግ ፖድካስት፣  በ ዩትዩብ ፣በ ትዊተር ፣ በ ፌስቡክ ፣ በቴሌግራም የተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ ገፆቻችን ታገኙናላችሁ