በቤታንያ ፍፁም (በሀያት የህክምና ኮሌጅ  PC1 የህክምና ተማሪ)

 

ድህረ አደጋ ውጥረት ወይንም Post Traumatic Stress Disorder የአዕምሮ ጭንቀት በሽታ አይነት ሲሆን መጥፎ አጋጣሚን ወይንም አደጋን ተከትሎ ስሜት ላይ በመቀረፅ ጭንቀት፣ ፍርሃት፣ ወይንም ስጋትን በማነሳሳት የስሜት መዛባትን ባልተጠበቀጊዜና ሁኔታ ያስከትላል።

 ይህ ውጥረት የሚከሰተው በአብዛኛው ጊዜ ለአደጋ ተጋላጭ በሆኑ ግለሰቦች እና በከፍተኛ ተፈጥሮአዊም ሆነ ሰው ሰራሽ አደጋ ውስጥ እየኖሩ ባሉ የማህበረሰብ ክፍሎች በአብዛኛው የሚከሰት ቢሆንም ሌሎች ግለሰቦችና የማህበረብ ክፍሎች  ይህ በሽታ እንደማይደርስባቸው ሙሉ ዋስትና የላቸውም። የበሽታው ተፈጥሮ ለመገመት የሚያዳግት ስለሆነ በህይወታችን ያሳለፍናቸው  ተሞክሮዎች ከቤተሰቦቻችን እና ጓደኞቻችን ጋር ያለን ግንኙነት ንቃተ ህሊናችን (conscious mind) እንዲሁምውር ህሊናችን (sub-conscious mind) ተቀናጅተውአንድን ሰው በችግሩ የመጠቃት ዕድል ይወስኑታል የግለሰየአስተሳሰብ ሁኔ  እና ተጋላጭነት ዋነኛውን ሚና ስለሚጫወቱ የበሽታው ጠቋሚ ምልክቶች ከግለሰብ ግለሰብ ሊለያዩ ይችላሉ

 

ድህረ አደጋ ውጥረት (ቀውስ)  እንዴት ሊከሰት ይችላል?

 

ከፍተኛ ለሆነ አደጋ የተጋለጡ ሰዎች ለምሳሌ፣ ጦርነት፣ ግርፊያ፣ የመኪና አደጋ፣ የእሳት ቃጠሎ፣ የቤት ውስጥ ብጥብጥ፣ ፆታዊ ጥቃቶች፣ የተፈጥሮ አደጋዎች እንዲሁም ሌሎች ኢሰብዓዊ ድርጊቶች ድርጊቱ ካለፈ ከረጅም ጊዜ በኋላም ቢሆን ተጠቂው ፍርሃት እንዲሰማው ያደርጋሉ ነገር ግን ሁሉም ሰው ድህረ አደጋ ውጥረት ሊያስብል በሚችል ደረጃ ህመም ይገጥመዋል ማለት አይደለምአንዳንድ ሰዎች በተለያዩ መንገዶች አውቀውትም ሆነ ሳያውቁት ጉዳቱን ተቋቁመው ሊያልፉ ይችላሉ አንድ በዚህ ህመም የሚሰቃይ ሰው ጉዳቱ እና ጭንቀቱ ሁልጊዜ ላይመጣበት ይችላል። በአመዛኙ ጊዜ ህይወቱን እንደ ወትሮው  መምራት የሚችል ሲሆን አደጋውን የሚያስታውሰው ሁኔታ ሲከሰት ግን ግለሰብ ከቁጥጥሩ ውጪ በሆነ መልኩ ስሜታዊ ምላሾች ወይም ተግባሮች ያሳያ አደጋውን የሚያስታውሰው ነገር ሲከሰት  ግለሰየሚሰሙት ስሜቶች አደጋው ከመፈጠሩ ጥቂት ደቂቃዎች በፊት አደጋው ሲፈጠር እና አደጋው ከተፈጠረ ጥቂት ደቂቃዎች በኋላ የተሰሙት ስሜቶች ጋር ተመሳሳይ ይሆኑበታል።ምንም እንኳን በዛ ሰዐት አደጋው ያለፈ ነገር ቢሆንም። የነዚህ ስሜቶች ድግግሞሽ የሚወሰነው በአደጋው አይነት እና አደጋው ሲፈጠር በነበረበት አካባቢ  ሲሆን

ለምሳሌ አንድ በማታ አደጋ ያጋጠመው ሰው ብርሃን ባለበት ቦታዎች ላይ የመደናገጥ እድሉ አነስተኛ ነው።

 

የድህረ አደጋ ውጥረት ጠቋሚ ምልክቶች ምንድን ናቸው?

 

ህመሙ ተጨባጭ የሆኑ በሁሉም ተጎጂዎች ላይ የሚታዩ ጠቋሚ ምልክቶች የሉትም። በዚህም ምክንያት ስውር ቁስል (the hidden wound) በመባልም  ይታወቃል። ይሁንና የሚከተሉት በአብዛኛው ሰዎች ላይ ከሚታዩት ጠቋሚ ምልክቶች የተወሰኑት ናቸው:

 

  1. ተደጋጋሚ ምልሰት እና ቅዠት መኖር

 

ምልሰት(flashback) በቀን የሚከሰት ሲሆን ቅዠት(nightmares) ደግሞ በምሽት በብሩህ ህልም መልክ ያጋጥማል። የምልሰት ባህሪያት የማለም የመጨነቅ የማልቀስ በፍርሃት የመዋስሜቶች ያሉበትን ቦታ እና ሰአት ማምታታትን ያካትታል። የቅዠት ባህሪያት ደግሞ ከምልሰት ባህሪያት በተጨማሪ ከእንቅልፍ እየጮሁ እና እያለቀሱ መባነንን ያካትታ::

 

  1. እራስን ማባበል

      

እራስን አደጋውን ከሚያስታውሱን ነገሮች ለመጠበቅ በሌላ ስራዎች መጥመድ፣ ተደጋጋሚ ጸሎት 

ማድረግ፣ ያረሳሳናል ብለን ያሰብናችውን ነገሮች ደግሞ ደጋግሞ ማድረግ፣ቸኝነትበተቻለን አጋጣሚ ማስወገድ፣ በፊልም እና በመጻህፍት ስራዎች እራስን ከተጨባጩ አለም መለየት ሌሎች አመልካቾች ናቸው።

 

  1. እራስን በተጠንቀቅ መጠበቅ

 

አደጋው እራሱን እንዳይደግም በመስጋት በማያስፈልቦታዎች ሁሉ የተጋነነ ጥንቃቄ ማድረግ፣ እንዲሁም አደጋ በማንኛውም ሰአት ሊከሰት እንደሚችል አስቦ መጨነቅ።

 

  1. ተደጋጋሚ ራስ ምታት፣ ተቅማጥ፣ በሱስ መሸበብ፣ እንቅልፍ ማጣት፣ የእንቅልፍ እና ጭንቀት ማስተባበያ እንክብሎች ያለባለሙያ ትእዛዝ መውሰድ።

 

  1. የመንፈስ ጭንቀት እና የቁጣ ስሜት

 

በተጎጂው ቤተሰቦ እና ጓደኞች መደረግ ያለባቸውና የሌለባቸው ምንድን ናቸው?

 

  • መደረግ የሌለባቸው

 

የታማሚውን ያልተለመዱ ባሕሪያት ሰይጣናዊ አካሎች እና ተግባሮች ጋር ማያያዝ የለባቸውም።

ህመምተኛው ከፍተኛ ስቃይ ላይ በመሆኑ ለይምሰል ያህል ‘ስሜትህን እረዳለሁ’ የሚሉ አይነት ንግግሮች ህመምተኛውን መልሰው እንዳይጎዱት መጠንቀቅ  ያስፈልጋል።

 

  • መደረግ ያለባቸው

 

ለታማሚው በቂ ጊዜ ሰጥቶ ሁኔታውን ለመረዳት መሞከር።

 

ታማሚው ደህንነቱ የሚጠበቅበት አካባቢ እንደሆነ እንዲሰማው ማድረግ።

 

የሚያስፈልገውን የህክምና ክትትል እንዲያገኝ ሁኔታዎችን  ማመቻቸት።

 

PTSD ተጠቂለሰብ የህክምና እርዳታ  ከየት እና በምን መልኩ  ሊያገኝ ይችላል?

 

በመጀመሪያ ታካሚው ለበሽታው እውቅና ሰጥቶት፣ እርዳታ እንደሚያስፈልገው አምኖበት ወደ ህክምና ሊሄድ ይገባል። ታማሚው ካመነበት የመረበሽ መታወክ ስሜቶቹን አክሞ ማዳን የሚቻል ሲሆን  ይህም በመድሃኒት ውይም አስተሳሰብን በመግራት ህክምና ሊደረግ ይችላል። ይህ አገልግሎትበአዕምሮ ህክምና በሰለጠኑ ባለሞያዎች የሚደረግ ሲሆን  በግልና በመንግስት የህክምና ተቋማት ሊደረግ ይችላል።

 

ከPTSD ህክምና አይነቶች ውስጥ

 

-Cognitive Behavioral Therapy ለበሽታው እና በሽታውን  የሚያነሳሱ ስሜቶች ያለንን አስተሳሰብ ቀስ በቀስ መቀየር፣ ማለማመድ፣ እና ስጋትን መቀነስ።

 

ሰውነትን የመቆጣጠር ዘዴዎች መማር እና መተግበር

 

መድሃኒት ጥታ PTSD ፈውስ ይችላል ነገር ግን ከስነ ልቦናዊ እርድታ ጋር ሲሆን ምልክቶችን በቁጥጥር ስር ለማዋል ያገለግላል።

 

ማጣቀሻዎች

 

Understanding PTSD’s effects on Brain, Body, and Emotions by Janet Seahorn TEDx Talks 

The Psychology of Post-Traumatic Stress Disorder TED-Ed

 በመረበሽ የመታወክ በሽታ ማለት ምንድነው? Embrace Mental Health