ዶ/ር ብሩክ አለማየሁ (የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት)

በአለማችን ከ38ሚሊየን የሚበልጥ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ከኤች.አይ.ቪ.(HIV) ጋር ይኖራሉ፡፡ ከዚህ ውስጥ ሁለት ሶስተኛው የሚገኙት በአህጉራችን  አፍሪካ ሲሆን የሀገራችንም ሁኔታ ብዙ የተለየ አይደለም፡፡ በኢትየጵያ ከ4 ወራት በፊት እንደተገለፀው በቫይረሱ እየተያዙ ያሉ አዲስ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ እንደሚገኝና ከሶስት ክልሎች ውጪ በቀሩት የአገሪቱ ክፍሎች በወረርሽኝ ደረጃ ይገኛል፡፡

ከሰሞነኛው የኮቪድ19 ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ የኤች.አይ.ቪ ታካሚዎቻችን የሚያነሷቸውን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክረናል፡፡

  1. ኤች.አይ.ቪ. (HIV)  በደሜ ውስጥ እንዳለ ተነግሮኛል:: ነገር ግን መድሃኒት አልጀመርኩም፡፡ ምን ላድርግ?
  • ከዚህ በፊትም ይሁን በአሁኑ ወቅት HIV በደማቸው እንዳለባቸው ተነገሯቸው የህክምና ክትትል ወይም መድሃኒት ያልጀመሩ ታካሚዎች በቶሎ ሀኪም አንዲያማክሩና እና ልዩ ምክንያት ከሌለ በስተቀር የፀረ ኤች.አይ.ቪ. (HIV) መድሃኒቶችን እንዲጀምሩ ይመከራል፡፡
  • ከኮቪድ አንፃር ልዩ መረጃ ባይኖርም አነዚህን መድኃኒቶች መጀመር የሰውነት የመከላከል አቅም እንዲጎለብትና ሰውነታችን ለተለያዩ ተጓዳኝ ኢንፌክሽኖች እንዳይጋለጥ ይረዳል፡፡
  • የፀረ ኤች.አይ.ቪ. መድሃኒት የሲደ4 (CD4) ቁጥር አነሰም በዛም በየትኛውም ደረጃ መጀመር አለበት፡፡

2. በኤች.አይ.ቪ. (HIV) የተያዙ ሰዎች በኮቪድ19 የመያዝ እድላቸው ከሌላው አንፃር የበለጠ ነው?

3. የ ኤች.አይ.ቪ. (HIV) ታካሚዎች ራሳቸውን ከኮቪድ19 ለመከላከል ምን ማድረግ አለባቸው?

  • ባሁኑ ሰዓት ኮቪድ19 ክትባት የለውም፡፡ ብቸኛው የመከላከያ መንገድ በቫይረሱ ላለመያዝ መሞከር ነው፡፡ ይህንም ለማድረግ መደበኞቹን የመከላከያ መንገዶች በአግባቡ መተግበር ለሁሉም የ ኤች.አይ.ቪ. (HIV) ታካሚዎች ይመከራል፡፡ እነዚህም፡-
    • ሳል፣ ትኩሳት እና ጉንፋን መሰል ህመም ካላቸው ሰዎች መራቅ
    • በአግባቡና በተደጋጋሚ እጅን መታጠብ/በአልኮል ማፅዳት
    • ባልታጠበ እጅ አፍ፣ አፍንጫ ወይም ዓይንን አለመንካት
    • ሰዎች በሚሰበሰቡባቸው ቦታዎች አለመገኘት
    • አላስፈላጊ ጉዞዎችንና እንቅስቃሴዎችን ማስቀረት
  • ከዚህም በተጨማሪ
    • የተመጣጠነ ምግብ መመገብ
    • በቂ እንቅልፍ/እረፍት ማግኘት
    • በተቻለ መጠን ውጥረትን መቀነስ
    • መድኃኒት ሳይረሱና ሰዓት ሳያሳስቱ በየዕለቱ መዋጥ
    • ለወራት የሚያቆይ በቂ መድኃኒት እጅ ላይ መያዝ
    • ልዩ ስሜት/ችግር ካለ ከሀኪም ጋር መመካከር

4. የ ኤች.አይ.ቪ. (HIV) ታካሚ ነኝ፡፡ ሁልጊዜ ማስክ ማድረግ አለብኝ ወይ?

5. የ ኤች.አይ.ቪ. (HIV) ታካሚ ነኝ፡፡ በኮቪድ19 እንደተያዝኩ እጠረጥራለሁ፡፡ ምን ማድረግ አለብኝ?

6. የፀረ ኤች.አይ.ቪ. (HIV) መድሃኒቶች ኮቪድ19ን ለማከም ይጠቅማሉ?

  • አንዳንድ የ ፀረ ኤች.አይ.ቪ. (HIV) መድሃኒቶች ኮቪድን ለማከም ጥናት እየተደረገባቸው እንደሆነ ተነስቷል፡፡
  • ከዚህ አንፃር በተለይ የሚነሳው ካሌትራ [Kaletra(Lopinavir boosted with Ritonavir (LPV/r))] ነው፡፡ መጀመሪያ ላይ አበረታች ውጤት እያስገኘ ነው ተብሎለት የነበረ ቢሆንም ከቻይና በወጡ አንዳንድ ጥናቶች መሰረት ግን የተጠበቀውን ያህል ውጤት አላሳየም፡፡
  • ይሄ እና ሌሎች የኤች.አይ.ቪ መድሃኒቶች ላይ ከ15 በላይ ጥናቶች እየተካሄዱ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ውጤቶቹን መጠበቅ መልካም ነው፡፡

7. በኮቪድ19 እንዳልያዝ የሚከላከልልኝ የፀረ ኤች.አይ.ቪ. (HIV) መድሃኒት አለ? የምወስደው መድሃኒት ሌላ ከሆነስ መድሃኒቴን ማስቀየር ይጠቅመኛል?

8. ሀገራት የፀረ ኤች.አይ.ቪ. (HIV) መድሃኒቶችን ኮቪድ19ን ለማከም ከተጠቀሙ እጥረት ሊከሰት አይችልም ወይ?

የጤና ወግ

በመረጃ የተመሰረተ ሕክምና ብቻ ።  

………………………………………………………………………………………………………………………..

ይህ የጤና ወግ ድረ ገፅ ነው።
ስለ ጤንነታችሁ ማወቅ የምትፈልጉትን መረጃ የምታገኙበት ፣ በህክምና ባለሙያዎች የሚዘጋጅ የመረጃ ምንጭ ነው።
ሁልግዜም ከሀኪማችሁ ተማከሩ፣ ተጨማሪ መረጃ ከፈለጋችሁ የኛን ድረ ገፅ ጎብኙ።

በጥናት የተደገፈ መረጃ ብቻ እናቀርባለን።

የህክምና ባለሙያዎች ለህሙማኖቻችሁ የሚሆን የሚነበብ መረጃ ከፈለጋችሁ ይህን ግፅ ጠቁሟቸው። ህሙማኖቻችሁ እንዲያውቁት የምትፈልጉትን ነገር መረጃ ጠቅሳችሁ ፃፉልን፣ ስምችሁን ጠቅሰን እናወጣለን። የህክምና ተማሪዎች እንዲጽፉ እናበረታታለን።

በተጨማሪም በጤና ወግ ፖድካስት፣  በ ዩትዩብ ፣በ ትዊተር ፣ በ ፌስቡክ ፣ በቴሌግራም የተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ ገፆቻችን ታገኙናላችሁ