ኑ እና ለአመት የሚሆን ደስታ ይዘው ይሂዱ
ደም ለግሰው @EthiopianBlood
የትምህርት መሳሪያዎች ለግሰው (በአይነት ወይም በገንዘብ)
ከተኪ @TekiPaperBags ጋር የምልክት ቋንቋ ተምረው
የበጎ ተግባር ተሳታፊ ይሁኑ
የጤና ወግ በፔንስልቬንያ ውስጥ በህጋዊ መንገድ የተመዘገበ ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት እንዲሁም በቦርድ የሚመራ እና በፍቃድኝነት የተደራጁ የጤና እና ሌሎች ባለሙያዎች ጥረት የተመሰረተ ትርፍ አልባ የሆነ ድርጅት ነው። ይህም ድርጅት የጤና ግንዛቤን በማስፋፋት ፣ የጤና ባለሙያዎች እርስ በርስ የሚማማሩበት እና የስራ ልምዳቸውን የሚካፈሉበት መድረክ በማዘጋጀት ላይ ተሰማርቶ የሚሰራ የበጎ አድራጎት ድርጅት ነው።
በዚህ አመት ላቀድነው ማህበረሰብ ተሳትፎ ተነሳሽነት ከኢትዮጵያ ደም ባንክ ጋር በመተባበር መደበኛ የደም ልገሳ ስራዎችን እንሰራለን፤ ይሄንንም ጳጉሜ 2-4, 2014 ባለው ጊዜ ውስጥ ይካሄዳል።
በዚህ አመት ከደም ልገሳ ዘመቻችን በተጨማሪ ብዙ ልጆችን ለሚደግፈው እና ለሚያሳድግ የስለ እናት በጎ አድራጎት ድርጅት የትምሀርት መማሪያ መሳሪያዎች ማሰባሰብ እንፈልጋለን።
ስለ እናት የበጎ አድራጎት ድርጅት በአዋጅ ቁጥር 1113/2011 በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ በሰርተፊኬት ቁጥር0089 ዳግም ተመዝግቦ ከ1994ዓ.ም ጀምሮ በህፃናትና በሴቶች ላይ እየሰራ ያለ የበጎ አድራጎት ድርጅት ነው፡፡ ስለእናት ወላጅ የሌላቸውንና ተጥለው የተገኙ ህፃናትን እንዲሁም የተለያዩ የአዕምሮና የአካል ጉዳት ያለባቸው ህፃናትን በመንከባከብና ድጋፍ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ድርጅቱ በአሁኑ ወቅት ከ1500 በላይ ህፃናት እና ሴቶችን እየደገፈ የሚገኝ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 60ዎቹ ህፃናት በተቋም አገልግሎት እና በቡድን ቤቶች ውስጥ የሚገኙ ሲሆኑ ከፊሎቹ ደግሞ ልዩ ፍላጎት ያላቸው (የአካል እና የአዕምሮ ጉዳት ያለባቸው) ናቸው፡፡
ባለፉት 3 ዓመታት በኮቪድ ወረርሽኝ በኑሮ ውድነትና በተለያዩ ምክንያቶች ከፍተኛ የሆነ ቀውስ በሀገራችን ብሎም በተቋሙ ላይ አጋጥሟል። ስለ እናት ከተለያዩ በጎ ፈቃደኞች ጋር በመሆን ለህጻናቱ ድጋፍ በመፈላለግ መሰረታዊ ፍላጎቶቻቸው እንዲሟሉ አስፈላጊው ጥረት እያደረገ ነው። በተቋም ለምናሳድጋቸው ልዩ ፍላጎት ላላቸው እና ተጥለው ተገኝተው ወደ ተቋሙ የመጡ ህጻናትን ሳር ቤት በሚገኘው ተቋም በመምጣት እንድትጎበኙ እንጠይቃለን፡፡
የህጻናቱን ዓመታዊ ለትምህርት እና አጠቃላይ ወጪ ለመደገፍ ወደ 10,000 ዶላር ለመሰብሰብ አቅደናል።
የአንድ ልጅ የአንድ አመት የትምህርት ወጪ ለመሸፈን የሚወጣው ወጪ ከ30-35 ዶላር ነው።
የአንድን ልጅ ሙሉ ዓመታዊ ወጪ ለመሸፈን ደግሞ ከ95-100 ዶላር ይፈጃል።
ሁሉም መዋጮዎች ቀጥታ ወደ ድርጅቱ ውስጥ ወዳሉ ህፃናት ይሄዳል። የጤና ወግ ከዚህ ምንም ክፍያ አይወስድም። እኛ ሙሉ በሙሉ የምንመራው በአስደናቂ በጎ ፈቃደኞቻችን ድጋፍ ነው።
በዩኤስኤ ለሚገኙ ለጋሾች በሙሉ፡ የሚያበረክቱት መዋጮ ታክስ ተቀናሽ ነውና ከየጤና ወግ ደረሰኝ ማግኘት እንደሚችሉ እንገልፃልን።
#BackPack Challenge
Be part of it!
Help Students get through the year by donating a single Backpack filled with school supplies (-worth ~ $35 USD )
OR
Cover one student’s whole year’s expenses for just – $100 USD.
YetenaWeg, a legally registered nonprofit Organization in Pennsylvania and governed by a Board of Directors, is a volunteer network of healthcare professionals and other experts engaged in creating and promoting health awareness and mentoring the next generation of healthcare professionals.
As part of our community engagement initiatives, we do regular blood donation drives in collaboration with Ethiopian Blood and Tissue Bank. The annual blood donation drive will be held at the National Blood bank between September 7 to 9, 2022. (ጳጉሜ 2-4, 2014)
This year along with our blood donation drive we want to raise funds /collect school supplies for Sele-Enat /ስለ እናት/ charity organization that supports and raises more than 1500 children including those who are living with autism.
Sele-Enat Charity Organization It is a charity organization that has been working for children and women since 1994. It is caring for and supporting orphaned and abandoned children as well as children with various mental and physical disabilities. Sele-Enat is currently supporting more than 1500 children and women, of which 60 children are in institutional services and group homes, and some of them have special needs (physical and mental disabilities).
In the last 3 years, due to the covid-19 epidemic, Sele-Enat has experienced a huge crisis due to the cost of living rising exponentially and other various reasons. Sele-Enat, together with various volunteers, seeks to support the children and is doing everything necessary to meet their basic needs.
We plan to raise about $10,000 to support the children’s annual education and general expenses.
A one-year backpack of school supplies is $35.
A whole year’s expenses for one child $100 USD
All donations go directly to the children in the organization. Yetena Weg takes no fees. We are run entirely by the support of amazing volunteers.
For donors in the USA, all your contributions are Tax deductible and you can get a reference/receipt from Yetena Weg.