YetenaWegLogo

በአዋቂዎች ላይ የሚከሰት የቫይታሚን ዲ እጥረት (Vitamin D Deficiency in Adults)

Oct 05, 2023

በእስራኤል ንጉሴ (ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የ5ኛተማሪ)

By Israel Nigguse, C2 student at Tikur Anbessa Specialized Hospital

Reviewed by- Dr. Lemma Zewde, Internal Medicine

የቫይታሚን ዲ እጥረት ስንል በሰውነት ውስጥ በቂ የሆነ የቫይታሚን ዲ ክምችት አለመኖር ማለት ነው። ቫይታሚን ዲ በዋነኝነት ሰውነታችን ካልሲየም እና ፎስፎረስ የተባሉትን ንጥረነገሮች ከአንጀትን ክፍል በደም አማካኝነት ወደ የተለያዩ የሰውነት ክፍሎቻችን እንዲዳረሱ ከፍተኛ ሚና የሚጫወት ሲሆን በተጨማሪም የበሽታ የመከላከል እና የመቋቋም አቅማችንን ይጨምራል፣ እንዲሁም ለህዋሳት እድገት አስፈላጊ የሆነ የቫይታሚን አይነት ነው።

 

በቂ ቫይታሚን ዲ በሰውነታቸውን ውስጥ በበቂ መጠን አለመኖር ለሚከተሉት ጉዳቶች ሊዳርገን ይችላል።

  • የአጥንት መሳሳት እንዲኖር እና በቀላሉ አጥንት እንዲሰበር እና ቅርፁን እንዲቀይር ያደርጋል።
  • ደካማ ጡንቻዎች እንዲኖረን፣ ይህም የሰውነት መተሳሰር እና የድካም ስሜት እንዲሰማን ያደርጋል።
  • የበሽታ የመቋቋም አቅማችንን እንዲቀንስና ቶሎ ቶሎ በበሽታ የመጠቃት እድላችንን ይጨምራል።
  • የድባቴ ስሜት እንዲሰማን ያደርጋል።
  • ለፀጉር መነቃቀል እና መሳሳት በጥቂቱ ሊጠቀሱ የሚችሉት ናቸው።

 

ለቫይታሚን እጥረት ምርመራ አለ?

አዎ። ዶክተርዎ በቂ ቫይታሚን ዲ እንዳለዎት ለማወቅ የደም ምርመራ ማድረግ ይችላሉ። ነገር ግን ይህ ምርመራ ሁልጊዜ ላያስፈልግን ይችላል። ዶክተሮች የቫይታሚን ዲ መጠን ምርመራን የሚያዙት ለቫይታሚን ዲ እጥረት ተጋላጭ ናቸው ብለው በሚያስቡት ሰዎች ላይ ብቻ ነው። ይህም የሚከተሉትን ሰዎች ያጠቃልላል፦

  • አብዛኛውን ወይም ሁሉንም ጊዜያቸውን በቤት ውስጥ የሚያሳልፉ (ለምሳሌ በአረጋውያን መንከባከቢያ ውስጥ ያሉ)
  • ቫይታሚን ዲ ወደ ሰውነታችን ክፍል ለማስገባት የሚከብዱ የሕክምና ችግሮች (እንደ ሲሊአክ በሽታ) ያለባቸው
  • አጥንትን መሳሳት ( ኦስቲዮፖሮሲስ) ላለባቸው ሰዎች
  • በቀላል አደጋዎች የአጥንትን መሰበር ላጋጠማቸው ሰዎች
  • ለህጻናት በአግባቡ ለፀሀይ ብርሃን ያልተጋለጡት እና ሌሎችንም ያካትታል።

 

ምን አይነት ምግቦች እና መጠጦች ቫይታሚን አላቸው?

ብዙ ቫይታሚን ዲ ያላቸው ምግቦች እና መጠጦች ዋነኞቹ

  • ወተት፣ ብርቱካን ጭማቂ፣ ወይም እርጎ
  • ዓሳ (ሳልሞን ወይም ማኬሬል ፣ የታሸገ ቱና)
  • በቫይታሚን ዲ የተጨመሩባቸው እህሎች እና
  • የአሳ ዘይት

በተጨማሪም ሰውነታችን ቫይታሚን ዲን ከፀሀይ ማግኘት ይችላል ይህም ሲባል ሰውነት ቫይታሚን ዲን ለማምረት ቆዳ ላይ የሚያርፈውን የፀሐይ ብርሃን በመጠቀም 7- ዳይሀድሮኮሌስትሮል የተባለውን በተፈጥሮ በቆዳችን ውስጥ የሚገኘውን ውህድ ወደ ቅድመ ቪታሚን ዲ3 በመቀየር ነው።

ፀሀይ እና ቫይታሚን

የፀሀይ ብርሃን በሰውነታችን ውስጥ ቫይታሚን ዲ አንዲመረት ከፍተኛ ሚና ይጫወታል። ሰለዚህ በቂ የፀሀይ ብርሃን ማግኘት ይመከራል።

 

ሰፕልመንትስ (ማሟያዎች) ምንድን ናቸው?

ሰፕልመንትስ ሰዎች ቫይታሚን ዲ የሚያገኙበት ሌላኛው መንገድ ነው። ሰፕልመንትስ በውስጣቸው ንጥረ ነገር ያላቸው ክኒኖች (እንክብሎች) ወይም ፈሳሾች ናቸው።

 

የቫይታሚን ሰፕልመንትስ መውሰድ አለብኝ?

ባለሙያዎች አብዛኛዎቹ አዋቂዎች በየቀኑ ከ600 እስከ 800 IU (አለምአቀፍ የቫይታሚን ዲ ዩኒት) ያላቸውን ሰፕልመንትስ እንዲወስዱ ይመክራሉ። ይህ ከ15 እስከ 20 ማይክሮ ግራም ቫይታሚን ዲ ጋር ተመሳሳይ ነው። በቂ ቫይታሚን ዲ ከምግባቸው ወይም ከፀሀይ ያላገኙ ሰዎች ከዚህ የበለጠ መጠን መውሰድ ሊያስፈልጋቸው ይችላል።

በዶክተርዎ የቫይታሚን ዲ ተጨማሪ መድሃኒቶችን እንዲወስዱ ከታዘዘ ፣ የትኛውን አይነት ፣ በምን ያህል መጠን እና ለምን ያህል ጊዜ እንደሚወስዱ መጠየቅ ተገቢ ነው።

ለእርስዎ የሚስማማዎትን የሰፕልመንት አይነት እና መጠን በእርስዎ የጤና ሁኔታ እና በሚወስዷቸው ሌሎች መድሃኒቶች ላይ በመነሳት ዶክተርዎ ይወሰናል። ስለዚህም ከታዘዘው መጠን በላይ ቪታሚን ዲ መውሰድ ለተለያዩ የህክምና ጉዳቶች እንደሚያጋልጥ በመረዳት ራስን መጠበቅ ይገባል።

 

ምንጮች

  1. https://www.uptodate.com/contents/vitamin-d-deficiency-in-adults-definition-clinical-manifestations-and-treatment
  2. Nair R, Maseeh A. Vitamin D: The “sunshine” vitamin. J Pharmacol Pharmacother. 2012 Apr;3(2):118-26. – PMC – PubMed
  3. https://www.hopkinsmedicine.org/health/wellness-and-prevention/vitamin-d-and-calcium

 

Recent Posts