የሴቶች ጤና ክትትል። በዚህ የሴቶች ጤና ወጋችን በጡት ካንሰር እና በማህፀን በር ካንሰር ላይ እንወያያለን።
Mar 17, 2020
የዚህ ክፍል የሴቶች ጤና ውይይታችንን ዶ/ር ኤልሳቤጥ አሳረ እና ዶ/ር ማክዳ ካህሳይ ይመሩታል። ስለጡት ካንሰር እና ማህፀን በር ካንሰር ምልክቶች፣ የትኞቹ ሴቶች ለዚህ ካንሰር የበለጠ ተጋላጭ እንደሆኑ ፣ ምን ምርመራ እና ቅድመ ምርመራ እንደሚይስፈልገን እና ህክምናውስ ምን ይመስላል የሚሉት ርዕሶች ላይ ይወያያሉ። ዶ/ር ኤልሳቤጥ አሳረ በ በኒውዮርክ የሪችመንድ ዩኒቨርሲቲ የውስጥ ደዌ ህክምና ስፔሻሊስት ሬዚደንት ሀኪም ናት ። እና ዶ/ር ማክዳ ካህሳይ ደግሞ በኒውዮርክ ማውንት ሳይናይ ሆስፒታል የውስጥ ደዌ ህክምና ስፔሻሊስት ሬዚደንት ሀኪም ናት።
—
--- Send in a voice message: https://anchor.fm/yetenaweg/message
