YetenaWegLogo

በቫይረሱ የተጠቃን ሰው (አዋቂ) እንከባከባለሁ ምን ጥንቃቄ ማድረግ አለብኝ?

Mar 25, 2020

በቫይረሱ የተጠቃን ሰው (አዋቂ) እንከባከባለሁ ምን ጥንቃቄ ማድረግ አለብኝ?

ዶ/ር ብሩክ አለማየሁ (የውስጥ ደዌ ስፒሻሊስት)

በኮቪድ19 እንደተያዘ የሚጠረጠር ታካሚ ውጤቱ እስኪታወቅ ድረስ ወይም ደግሞ ከተረጋገጠ በኋላ ቤት ውስጥ መንከባከብ የግድ ሊሆን የሚችልባቸው ሁኔታዎች ሊፈጠሩ ይችላሉ፡፡

ምን ምን ጥንቃቄዎች ማድረግ አለብን?

  • በተቻለ መጠን በጉዳዩ ላይ እውቀትና ልምድ ያለውን የጤና ባለሙያ ያማክሩ
  • የቆዩ የጤና እክሎች (ለምሳሌ ስኳር፣ ደም ግፊት፣ የሳንባ/ልብ/ኩላሊት/ጉበት በሽታ) ወይም ካለብዎት ወይም ነፍሰጡር ከሆኑ በተቻለ መጠን ሌላ ሰው እንዲንከባከብ ያድርጉ
    • አማራጭ ከሌለ የሚከተሉትን ጥንቃቄዎች ይተግብሩ
  • ታማሚው በተለየና በደንብ መናፈስ በሚችል ክፍል ውስጥ ይሁን፤ እርስዎ ሌላ ክፍል ውስጥ ይሁኑ
    • የሚጠቀሙት መኝታ ክፍልም ሆነ ባኞ ቤት ከታማሚው የተለየ ይሁን
    • ቤትዎ ባለአንድ ክፍል ብቻ ከሆነ በመሃከላችሁ ሁልጊዜ ቢያነስ የ2 ሜትር ርቀት በመሃከላችሁ ጠብቁ
    • ቤቱ በቂ አየር እንዲገባበት ያድርጉ፣ መስኮቶች በሁሉ ጊዜ ሁሉ ክፍት ይሁኑ
  • በተደጋጋሚ እጅዎን በሳሙናና በውሃ ቢያንስ ለ20 ሰኮንድ በደንብ ይታጠቡ፡፡ ወይም ቢያንስ 60 በመቶ አልኮል ባለው ሳኒታይዘር እጅዎን ያፅዱ፡፡
    • ዓይንዎን፣ አፍንጫዎን እና አፍዎን ባልታጠበ እጅ አይንኩ፡፡
  • ታማሚውን ለመንከባከብም ሆነ በሌላ አስገዳጅ ምክንያት በአንድ ክፍል መሆን ካለብዎት ሁለታችሁም የፊት ጭንብል (facemask) አጥልቁ
  • ታማሚውን ለመንከባከብ በሚነኩበት ጊዜ ወይም እንደ አክታ፣ ደም፣ ሰገራ፣ ሽንት የመሳሰሉ የሰውነት ፈሳሾችን መጥረግ/ማፅዳት ካለብዎት የፊት ጭንብል (facemask) እና የእጅ ጓንት ይጠቀሙ
  • የእጅ ጓንትዎን እና የፊት ጭንብልዎን (facemask) እንደተጠቀሙበት ያስወግዱ፤ በፍፁም መልሰው አይጠቀሙ
    1. በመጀመሪያ የእጅ ጓንትዎን ያስወግዱ
    2. ከዚያም እጅዎን በውሃና ሳሙና ከታጠቡ (ወይም አልኮል ያለው ሳኒታይዘር ካፀዱ) በኋላ የፊት ጭንብልዎን (facemask) ያስወግዱ
  • የመጠቀሚያ ቁሳቁሶችን ከሌሎች ሰዎች ጋር አይጋሩ (ምሳሌ፡ ሳህን፣ ብርጭቆ፣ ኩባያ፣ ማንኪያ፣ ሹካ፣ ሌሎች የመመገብያ እቃዎች፣ አንሶላ፣ ፎጣ፣ ልብሶች እና ሌሎችም)
    • ታካሚው እነዚህን እቃዎች ከተጠቀመ በኋላ ሁልጊዜ በሳሙናና ውሃ በደንብ ይጠቡ
  • በክፍልዎ ያሉ በተደጋጋሚ የሚነኩ ቦታዎችን በየቀኑ ማፅዳት (ለምሳሌ፡ ጠረጴዛ፣ የበር መክፈቻዎች፣ መብራት ማብሪያ/ማጥፊያዎች፣ ባኞ ቤትና ሽንት ቤት ውስጥ ያሉ እቃዎችእና የመሳሰሉት)
  • ልብሶችን በደንብ ማጠብ
    • በተለይም እንደ ደም፣ ሰገራ፣ ሽንት የመሳሰሉ ፈሳሾች የነኳቸውን አንሶላዎችንና ሌሎች ልብሶች ወድያውኑ ይጠቡ የእጅ ጓንት ይጠቀሙ
  • የእጅ ጓንቶቸንና የፊት ጭንብልዎን መዘጋት በሚችል ልዩ የቆሻሻ መጣያ ውስጥ ያስወግዱ
  • ታማሚው በቂ እረፍት እንዲያገኝ ያድርጉ፤ በቂ ፈሳሽና ምግብ እንዲያገኝ ያድርጉ
  • ከቤት ውጭ ያለዎትን እንቅስቃሴ ይገድቡ

ምንጮች

  1. https://www.health.harvard.edu/diseases-and-conditions/coronavirus-resource-center#Sick
  2. https://www.cdc.gov/coronavirus/2019-ncov/hcp/guidance-home-care.html
  3. https://multco.us/novel-coronavirus-covid-19/covid-19-guidance-taking-care-sick-person-home

Recent Posts