የጡት ካንሰር በሴቶች ላይ ሊከሰቱ ከሚችሉ ካንሰሮች አንዱ ነው። በአለም አቀፍ ሁኔታ በሴቶች ላይ ከሚከሰቱ የካንሰር አይነቶች የጡት ካንሰር በ 1 ኛ ደረጃ ይቀመጣል። 

የጡት ሴሎች (ህዋሶች ) ከተለመደው ወጣ ባለ እና ጤናማ ባልሆነ መልኩ ሲያድጉ እና ሲባዙ ይፈጠራል ።

የጡት  ካንሰር በአብዛኛው የሚከሰተው በሴቶች ቢሆንም በወንዶች ላይም ሊከሰት ይችላል።