በቫይረሱ የተጠቃን ሰው (አዋቂ) እንከባከባለሁ ምን ጥንቃቄ ማድረግ አለብኝ?
Mar 25, 2020
በቫይረሱ የተጠቃን ሰው (አዋቂ) እንከባከባለሁ ምን ጥንቃቄ ማድረግ አለብኝ?
Tweet
ዶ/ር ብሩክ አለማየሁ (የውስጥ ደዌ ስፒሻሊስት)

በኮቪድ19 እንደተያዘ የሚጠረጠር ታካሚ ውጤቱ እስኪታወቅ ድረስ ወይም ደግሞ ከተረጋገጠ በኋላ ቤት ውስጥ መንከባከብ የግድ ሊሆን የሚችልባቸው ሁኔታዎች ሊፈጠሩ ይችላሉ፡፡
ምን ምን ጥንቃቄዎች ማድረግ አለብን?
- በተቻለ መጠን በጉዳዩ ላይ እውቀትና ልምድ ያለውን የጤና ባለሙያ ያማክሩ
- የቆዩ የጤና እክሎች (ለምሳሌ ስኳር፣ ደም ግፊት፣ የሳንባ/ልብ/ኩላሊት/ጉበት በሽታ) ወይም ካለብዎት ወይም ነፍሰጡር ከሆኑ በተቻለ መጠን ሌላ ሰው እንዲንከባከብ ያድርጉ
- አማራጭ ከሌለ የሚከተሉትን ጥንቃቄዎች ይተግብሩ
- ታማሚው በተለየና በደንብ መናፈስ በሚችል ክፍል ውስጥ ይሁን፤ እርስዎ ሌላ ክፍል ውስጥ ይሁኑ
- የሚጠቀሙት መኝታ ክፍልም ሆነ ባኞ ቤት ከታማሚው የተለየ ይሁን
- ቤትዎ ባለአንድ ክፍል ብቻ ከሆነ በመሃከላችሁ ሁልጊዜ ቢያነስ የ2 ሜትር ርቀት በመሃከላችሁ ጠብቁ
- ቤቱ በቂ አየር እንዲገባበት ያድርጉ፣ መስኮቶች በሁሉ ጊዜ ሁሉ ክፍት ይሁኑ
- በተደጋጋሚ እጅዎን በሳሙናና በውሃ ቢያንስ ለ20 ሰኮንድ በደንብ ይታጠቡ፡፡ ወይም ቢያንስ 60 በመቶ አልኮል ባለው ሳኒታይዘር እጅዎን ያፅዱ፡፡
- ዓይንዎን፣ አፍንጫዎን እና አፍዎን ባልታጠበ እጅ አይንኩ፡፡
- ታማሚውን ለመንከባከብም ሆነ በሌላ አስገዳጅ ምክንያት በአንድ ክፍል መሆን ካለብዎት ሁለታችሁም የፊት ጭንብል (facemask) አጥልቁ
- ታማሚውን ለመንከባከብ በሚነኩበት ጊዜ ወይም እንደ አክታ፣ ደም፣ ሰገራ፣ ሽንት የመሳሰሉ የሰውነት ፈሳሾችን መጥረግ/ማፅዳት ካለብዎት የፊት ጭንብል (facemask) እና የእጅ ጓንት ይጠቀሙ
- የእጅ ጓንትዎን እና የፊት ጭንብልዎን (facemask) እንደተጠቀሙበት ያስወግዱ፤ በፍፁም መልሰው አይጠቀሙ
- በመጀመሪያ የእጅ ጓንትዎን ያስወግዱ
- ከዚያም እጅዎን በውሃና ሳሙና ከታጠቡ (ወይም አልኮል ያለው ሳኒታይዘር ካፀዱ) በኋላ የፊት ጭንብልዎን (facemask) ያስወግዱ
- የመጠቀሚያ ቁሳቁሶችን ከሌሎች ሰዎች ጋር አይጋሩ (ምሳሌ፡ ሳህን፣ ብርጭቆ፣ ኩባያ፣ ማንኪያ፣ ሹካ፣ ሌሎች የመመገብያ እቃዎች፣ አንሶላ፣ ፎጣ፣ ልብሶች እና ሌሎችም)
- ታካሚው እነዚህን እቃዎች ከተጠቀመ በኋላ ሁልጊዜ በሳሙናና ውሃ በደንብ ይጠቡ
- በክፍልዎ ያሉ በተደጋጋሚ የሚነኩ ቦታዎችን በየቀኑ ማፅዳት (ለምሳሌ፡ ጠረጴዛ፣ የበር መክፈቻዎች፣ መብራት ማብሪያ/ማጥፊያዎች፣ ባኞ ቤትና ሽንት ቤት ውስጥ ያሉ እቃዎችእና የመሳሰሉት)
- ልብሶችን በደንብ ማጠብ
- በተለይም እንደ ደም፣ ሰገራ፣ ሽንት የመሳሰሉ ፈሳሾች የነኳቸውን አንሶላዎችንና ሌሎች ልብሶች ወድያውኑ ይጠቡ የእጅ ጓንት ይጠቀሙ
- የእጅ ጓንቶቸንና የፊት ጭንብልዎን መዘጋት በሚችል ልዩ የቆሻሻ መጣያ ውስጥ ያስወግዱ
- ታማሚው በቂ እረፍት እንዲያገኝ ያድርጉ፤ በቂ ፈሳሽና ምግብ እንዲያገኝ ያድርጉ
- ከቤት ውጭ ያለዎትን እንቅስቃሴ ይገድቡ
ምንጮች
