Health Risks of Smoking. ትምባሆ ማጨስ የሚያመጣቸው የጤና እክሎች ምንድናቸው ? እንዴትስ ነው የ ትምባሆ ማጨስን ሱስ መግታት የምንችለው ?
Jul 15, 2020
ትምባሆ ማጨስ የሚያመጣቸው የጤና እክሎች ምንድናቸው ? እንዴትስ ነው የ ትምባሆ ማጨስን ሱስ መግታት የምንችለው ? በዚህ ፖድካስታችን ስለ ትምባሆ (ሲጋራ ) ማጨስ ጉዳቶች በሰፊው እንወያያለን ። የ ምናነሳቸው ሃሳቦች 📍 *የትንባሆ አይነቶች ምንድን ናቸው? አጠቃቀማቸውስ? 📍 * አንዱ ከሌላው በሚፈጥሩት ጉዳት ይለያያሉ ወይ? *📍 መደበኛ ሲጋራ ፣ ሺሻ ወይም ሁካ እና የ ኤለክትሮንክ ሲጋራ ያላቸውን ልዩነት እናያለን 📍*ሺሻ /ሁካህ ከ ተለመደው ሲጋራ በባሰ መልኩ እንዴት የጤና ችግር እንደሚያመጣ እንነጋገራለን 📍 *በ እርግዝና ጊዜ የሚያጨሱ ሴቶች ወይም ለሲጋራ ጭስ በተዘዋዋሪ የሚጋለጡ እናቶች በራሳቸው እና በሚወልዱት ልጅ ላይ የሚያስከትለውን ጉዳት አንስተን እንነጋገራለን 📍ከሁለተኛ እጅ የተጎዳኘ ጭስ መጋለጥ የሚፈጥራቸው የጤና ችግሮች ምንድን ናቸው? 📍አጫሾች ማጨስ ቢያቆሙ ምን የጤና ጥቅሞች ሊያገኙ ይችላሉ? 📍ከዚያ በኋላ ሲጋራ ማቆም ጥቅም የለውም የሚባልበት አድሜ አለ አንዴ? 📍ለአጫሾች ለምን ማቆም ይከብዳል? ለማቆም ምን ማረግ አለባቸው?
—
Send in a voice message: https://anchor.fm/yetenaweg/message
