Herd Immunity ምንድነው?
Apr 02, 2020
በዚህ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ጊዜ Herd Immunity ከበሽታ ሊጠብቀን አይችልም። መኖሩንም ማወቅ አንችልም። የተነገሩንን የመከላከል እርምጃዎች እንከተል። Tweet Herd Immunity ማለት በአንድ ማህበረሰብ ያሉ ሰዎች ውስጥ ለ አንድ ተላላፊ በሽታ ምን ያህሉ በሽታውን የመከላከል አቅም አላቸው የሚለውን ነው የሚነግረን። ሰዎች ይሄን የመከላከል አቅም ወይ ታመው ከበሽታው ሲያገግሙ ያገኙታል ወይም በ ሕብረተሰብ ጤና የሚመረጠው ደግም ማህበረሰብ አቀፍ በሆነ የክትባት ዘመቻ ሁልኑም ወይም አብዛኛውን ሕብረተሰብ ማዳረስ ሲቻል ነው። Herd Effect የምንለው ደግሞ በ ማህበረሰብ ውስጥ ከፍ ያለ የ Herd Immunity በመኖሩ የ አንድ በሽታ ከ አንዱ ሰው ወደ ሌላ ሰው የመተላለፍ እድሉ ሲቀንስ ነው። ምን ያህሉ ሰው ለ አንድ በሽታ የመከላከል አቅም ሲኖረው ነው ይሄን Herd Effect የምናየው የሚለው የሚወሰነው በሽታው ምን ያህል ተላላፊ ነው በሚለው ነው።
—
Send in a voice message: https://anchor.fm/yetenaweg/message
