ቅድመ ወሊድ እና በ እርግዝና ጊዜ የ ሚያስፈልገን ክትትል።

በእርግዝና ጊዜ የተለመዱ የህመም ምልክቶች

  • በእርግዝና ጊዜ የተለመዱ የህመም ምልክቶቸ የቶቹ ናቸው ?

         ከእርግዝና ጋር ተያይዞ የተለያዩ ለውጦች በሰውነት ላይ ይከሰታሉ፡፡ ይህም የሚሆነው የሰውነት ሆርሞኖችና የስራ ሂደቶች ስለሚጨመሩ ነው፡፡

  በሰውነት ላይ የሚፈጠረው ጫና አንዳንድ የህመም ምልክቶች ሊያመጣ ሲችል ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ዋናዎች ናቸው፡፡

የድድ መድማት

        ድዳችን በእርግዝና ጊዜ ለስላሳ ሲሆን ሊያብጥና ቆሻሻ የማጥራት አቅሙ ሊደክም ይችላል ይህም የሚሆነው በሆርምኖች መጨመር ሲሆን ይህ ሲያጋጥም የድድ

   መድማትና  መጠዝጠዝ ሊኖር  ይችላል፡፡ ይህንንም ለመከላከል በደንብ ጥርስን ማፅዳትና ለጥርስ ማጠንከሪያ የሚመከሩ  ምግቦች መመገብ ያስፈልጋል፡፡

ትንፋሽ መቆራረጥና የማዞር ስሜት

     የሳንባችንን ክፍል ከሆድ እቃችን የሚለየው  ዳያፍራም የተባለው ጡንቻ በእርግዝናው ጫና ምክንያት ወደላይ ሊገፋ ስለሚችል ትንፋሽ መቆራረጥ ያመጣል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞም የደም ማነሰ ወይም የደምግፊት መቀነስ የማዞር ስሜት ሊያመጣ ይችላል ይህ ሲሆን ቀና ብሎ በመተኛት ማዞር ሲኖር ደግሞ ቁጭ ባሉበት

ጭንቅላትን እግር መሀል በመቅበር እና ባጠቃላይ እረፍት በማድረግ መከላከል ይቻላል፡፡

በየጊዜው የሽንት ማስቸገርና የሽንት ማምለጥ

     ማህፀን ውስጥ የሚያድገው ህፃን የሽንት ከረጢት ላይ ጫና ስለሚፈጥር በተደጋጋሚ ሽንት መምጣትና በተለይ በመሳቅና በማስነጠስ ጊዜ ሽንት

ሊያመልጥ ይችላል፡፡ ይህ ብዙም ሊያሳስብ አይገባም፡፡ ከሰዓት ይምትጠጣውን የውሃ መጠን በትንሹ በመቀነስ መከለከል ይቻላል፡፡

የማህፀንና የሰውነት አካባቢ ማሳከክና ሸንተረር ምልክቶች መውጣት

     የሚያልቡ የሰውነት ክፍሎች አካባቢ ለምሳሌ አንገት ስር የሰውነት መገጣጠሚያ እንዲሁም የማህፀን በር ጋር መድረቅ ማሳከክና ማቃጠል ሊኖር ይችላል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞ ቆዳችን ሲወጠር ነጭ እና ጥቋቁር የሽንተረር ምልክቶች በተለምዶ እግርና ሆድ ላይ ይታያሉ፡፡ ይህ ተፈጥሮአዊ ለውጥ ስለሆነ ማሰብ አይገባም

የሆድ ድርቀትና የፋንጢጣ አካባቢ እብጠት (Hemorrhoid)

በእርግዝና ጊዜ የሚመረቱ ሆርሞኖች የምግብ አፈጫጨት ፍጥነትን ስለሚቀንሱ የሆድ ድርቀትን ያመጣሉ፡፡ ይህ ሆዳችን ላይ እርግዝናው ከሚያመጣው ጫና ጋር ተያይዞ

 የፊንጢጣ አካባቢ እብጠት (ኪንታሮት) ሊያመጣ ይችላል፡፡

    ይህ እንዳይከሰት የሆድ ድርቀትን የሚከላከል ምግቦች እንደ ጎመን ዝንጅብል የካስተር ዘይት የመሳሰሉትን ምግቦች በመዉሰድ መቀነስ ይቻላል፡፡

ቁርጥማትና የደምስሮች ማበጥና መወጣጠር (varicose veins)

      በእርግዝና ጊዜ የመገጣጠሚያ የእግር እንዲሁም የእጅ ጫፎች ቁርጥማት ሊከሰት ይችላል፡፡ ይህ ችግር ከካልስየም ወይም ቫይታሚን እጥረት ሊሆን

 ስለሚችል እንደ ወተት ነጭ ሽንኩርት ወይም በየትኛውም የመድሀኒት መደብር የሚሸጡ የቫይታሚን እንክብሎች መውሰድ ይመከራል፡፡ ሌላው  ደግሞ

 የሚቆረጥመው  ቦታ በጣት ከፍ አድርጎ ከስር ማሸት ግዜያዊ ዕረፍት ያስገኛል፡፡ የደም ስሮች ማበጥ ሲኖር ደግሞ እግርን ከፍ አርጎ በመቀመጥ እንዲሁም

 ለዚሁ ብለው የተዘጋጁ ማሰሪያዎችን ከመድሀኒት ቤት በመግዛት ማድረግ ዕረፍት ያስገኛል፡፡

 

የጨጓራ ማቃጠል (ቃር), የማቅለሽለሽና ትውከት ህመም

      የምግብ ቱቦን ከጨጓራ የሚለየው ማሰርያ በሆርምን ለውጦች ስለሚለሰልስ የጨጓራ አሲድ ወደ ምግብ ቱቦ ሲመለስ  ቃር ያመጣል፡፡ ይህን ለመቀነስ

 ከባድና ቅባት የበዛባቸውን ምግቦች መቀነስ ይመከራል፡፡ ካሞሜላ ሻይ ዝንጅብል እና ንፁህ የተፈላ ወተት መጠጣት  ለጨጓራ ጥሩ ነው፡፡

በመጀመሪያዎቹ የእርግዝና ወራት በተለይ ምግብ ሲሸትና ጠዋት ጠዋት ማቅለሽለሽ እንዲሁም ማስታወክ ሊኖር ይችላል፡፡ ይህ ችግር ሲያጋጥም

የሚያስጠላትንና ከባድ ምግቦችን; በማቆም ደረቅ ብስኩቶችን, በዝንጅብልና በካሞሜላ የተሰሩ ሻዮችን መውሰድ አነስ ያሉ ምግቦችን በየሁለት ሰዓቱ መመገብ ከባሰም  የጤና ባለሙያ ማማከር  ያስፈልጋል፡፡

እነዚህ ከላይ የተጠቀሱ ምልክቶች በጣም በተደጋጋሚ ሊታዩ ስለሚችሉ ብዙ ሊያስጨንቆት አይገባም፡፡  

እርግዝና ሲከሰት የሚደረጉ ጥንቃቄዎች

ማጨስ መተው

     ማጨስ ለተረገዘው ህፃን የኦክስጅን እጥረት ያመጣል፡፡ ከዚህም ባሻገር ውርጃን ያለጊዜ የፅንስ መውረድንና ክብደታቸው ትንሽ የሆኑ ህፃናት

እንዲወለዱ ያደርጋልአፈጣጠራቸው ችግር ያለበት ህፃናትም እንዲወለዱ ያደርጋል፡፡ ስለዚህ ሲጋራ ካናቢስ እና ሺሻ ያሉ በመጨስ የሚወሰዱ

እፆችን ከናካቴው መተው ያስፈልጋል፡፡ በተጨማሪም ከቤተሰቡ ወይም ካካባቢዉ የሚያጨስ ሰው ካለ እነዚህ ኬሚካሎች አየሩ ውስጥ ስለሚገኙ

ይሄንም ከተሳቢነት ማስገባት ያስፈልጋል፡፡

አልኮል መተው

       ለአንዲት እርጉዝ ሴት በቀን ከአንድ ብርጭቆ ወይን በላይ አልኮል አይመከርም; አልኮል በብዛት ከመዉሰድ ጋር ተያይዞ የሚመጣ ይህፃናት

የአእምሮ አፈጣጠር ችግርና በሽታ አለ ስለዚህ ይህን ለመከላከል የአልኮል መጠኗን መቀነስ ከተቻለም ማቆም ያሻል፡፡

 

መድሀኒቶች

        ለሌላ ጊዜ በቀላሉ ምንም ችግር የማይኖራቸው እንደ አስፕሪን ያሉ መድሀኒቶች ለእርጉዝ ሴቶች የተለወጠ የሰውነት የሆርሞኖች መጠን ሊጎዱ

ስለሚችሉ ማንኛውም መድሀኒት ለዶ/ ሳያማክሩ መወሰድ የለበትም፡፡ የማይቋረጡ መድሀኒቶች አንደ ደም ግፊት ስኳር እና HIV ያሉ ህመሞች

ያለባቸው እርጉዝ እናቶች በተለየ የክትትል ሂደት መድሀኒታቸው / ባዘዘው መሠረት መወሰድ አለበት፡፡

ሌሎች

        ጥሬ ነገሮች ባለመመገብ በተለይ ስጋ እንዲሁም በቤት ውስጥ ድመቶች ወይም ውሾች የሚፀዳዱበትን አፈር በተገቢው መንገድና በንፅህና

በማስወገድ በእርግዝና ጊዜ ጐጂ የሆነ (toxoplasmosis) የተባለውን ተህዋስያን መከላከል ይቻላል፡፡

 

የተለየ ክትትል የሚፈልጉ የዕርግዝና አይነቶች

     ብዙ የዕርግዝና ክትትሎች ከዚህ ቀደም ከተጠቀሱ የክትትል ሂደቶች ዉጪ የተለየ ምርመራ  ባያስፈልጋቸውም አንዳንድ ለየት ያለ ወይም በብዛት ቀጠሮ

እንዲሁም ምርመራ የሚያስፈልጋቸው የዕርግዝና ዓይነቶች አሉ፡፡ ይህም ለህፃናኑ እንዲሁም ለእናት አስጊ የሆኑ ችግሮችን ቀደሞ ለመከላከል ይረዳል

 

የደም ማነስ

      ብዙ እናቶች ከእርግዝና በፊት የደም ማነስ ሊኖርባቸው ይችላል፡፡ ይህ የደም ማነስ በቅድሚያ መስተካከል ይኖርበታል የእናቲቱን እና የህፃኑን እድገት ለማጎልበት

እንዲሁም በምጥ ጊዜ በሚመጣ መድማት ጉዳትን ለመከላከል በብረት የበለፀጉ ምግቦችን እንዲሁም በዶክተር የሚታዘዙ የብረት እንክብሎችን መውሰድ ያስፈልጋል፡፡

እነዚህ የምግብ አይነቶች ቀይ ስጋ.ቆስጣ አሳ ዶሮ እና ኮክ የመሳሰሉ ምግቦችን ያጠቃልላል፡፡

 

ስኳር በሽታ

      ከማርገዝ በፊትም ሆነ በእርግዝና ወቅት ብቻ የሚወጣ የስኳር በሽታ ተቆጣጥሮ መያዝ ይኖርበታል፡፡ ይህም የሚሆነው በየጊዜው የስኳር መጠንና ተያያዥ ምርመራ

በማድረግ, የመድሀኒት አጠቃቀምን በማስተካከልና መድሀኒቱ ስኳሩን መቆጣጠሩን በማረጋገጥ ነው፡፡ ኢንሱሊን የሚወስዱ እርጉዝ ሴቶች የሚወስዱት መጠን በዶ/

መስተካከል አለበት ምክንያቱም እርግዝና የሰውነት እንዲሁም የውስጣዊ የሰውነት አሰራርን ሊቀይር ስለሚችል ነው፡፡ከዚህ  ጋር ተያይዞ አመጋገብን እና የሰውነት ክብደትን መከታተልም ተመራጭ ነው፡፡

 

የማህፀን በር መሳሳት

          በጤናማ የእርግዝና ወቅት የማህፀን በር ምጥ እስኪመጣ ድረስ ተዘግቶ ይቆያል፡፡አንዳንድ እናቶች ግን ጊዜው ሳይደርስ በተለያዩ የጤና መታወኮች  ምክንያት

ተደጋጋሚ ውርጃ ሊያጋጥማቸው ይችላል፡፡ ይህን ለመከላከል ወደ ጤና ተቋም መሄድ ይመከራል፡፡

 

 የደም ግፊት

       ከእርግዝና በፊትም ሆነ በእርግዝና ጊዜ ብቻ የሚወጣ የደም ግፊት በሽታ የተለየ የእርግዝና ክትትል ያስፈልገዋል፡፡ በእርግዝና የመጀመሪያው ጥቂት ወራት የደም

ግፊት መጨመር በፈጥነት ክብደት መጨመር የእግር ማበጥ ራስ ምታት የዓይን ብዥታ የሆድ ቁርጠት ሲኖር የደም ግፊት በሽታ ምልክቶች  ሊታይ ስለሚችል ወደ

ሆስፒታል መምጣትና ክትትል ማደረግ ያስፈልጋል፡፡

    የግፊት በሽታ ያለመድሀኒት ወይም ክትትል በጣም ከፍ ካለ ለህፃኑ የአፈጣጠር እና አድገት ችግር እንዲሁም ለእናት ከፍተኛ የጉበት እንዲሁም የኩላሊት መጎዳት

ሊያመጣ ይችላል ፡፡ ከዚህም አልፎ ራስን እስከመሳት ሊያደርስ ይችላል፡፡ እነዚህ ችግሮች እንዳይከስቱ የሚሰጡ መድሀኒቶችን እና ምክሮችን ማግኘት ያስፈልጋል

                                                                       

  Rh-ve (ሾተላይ) የደም ዓይነት ልዩነት

      ከአለማችን ሴቶች ወደ 15-20% ያሉት የደም አይነታቸው Rh-ve ሲሆን በመጀመሪያ ሳይሆን በሁለተኛው እርግዝናና ዉልደት ጊዜ ቀድመው የወለዱት ልጅ

 የተለየ የደምአይነት (Rh+ve) ከሆነ ለሚመጣው ሁለተኛ እርግዝና ችግር ሊፊጥር ስለሚችል የተለየ ክትትል መጀመር ያሻል፡፡ ይህን ችግር የሚከላከሉ መድሀኒቶች

ለማግኘትም ጥሩ አጋጣሚ ይሆናል፡፡

 

 ለእርግዝና ወራቸው በመጠን ያነሱ ወይም የበለጡ ህፃናት

     ለአያንዳንዱ የእርግዝና ወራት ተስተካካይ የሆነ የህፃን የመጠን መለኪያ  ስሌት ሲኖር  ከዚህ በላይ ወይም በታች ሲሆን አንዲት እርጉዝ ሴት የተለየ ክትትል መጀመር

አለባት፡፡ይህ የሚሆነዉ በተለያየ ምክንያት ሊሆን ስለሚችል የህፃኑን  ህልውና  እንዲሁም የእናቴቱን ጤንነት ለመጠበቅ ቅርብ ክትትል ያስፈልጋል፡፡

 

 መንታ እርግዝና

    ከማንኛውም እርግዝና በተለየ መልኩ የመንታ ወይም ከአንደ በላይ ህፃናት  በአንዴ እርግዝና በሰውነት ላይም ሆነ በህፃናቱ አቅምና አስተዳደግ ላይ

የተለየ ጫና ያሳድራል፡፡እነዚህን ጫናዎች ቀድሞ ለመከላከል እንዲሁም ከመጡም ለመቀነስ የተለየ ክትትል ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ለምሳሌ አንደ የደምግፊት መጨመር,

የሽንት ውሀ ቀድሞ መፍሰስበእርግዝና ወቅት የሚመጣ መድማት, የደም ማነስና ያለጊዜ የሚመጣ ምጥ ከማንኛውም እርግዝና በበለጠ የመንታ እርግዝናን የማጥቃት

መጠኑ ይጨምራል፡፡ ስለዚህ ስለአመጋገብስለሚደረጉ ጥንቃቄዎች እና ተያያዥ ጉዳዮች / ጋር መማከር ያስፈልጋል፡፡

 

በእርግዝና ጊዜ የሚከሰት የማህፀን ደም መፍሰስ

 

       በእርግዝና ጊዜ ማንኛውም የማህፀን የደም መፍሰስ ሲከሰት በፍጥነት የጤና ተቋም መሄድ ያስፈልጋል፡፡ 28 ሳምንት በፍት የውርጃ ምልክቶች ሊሆኑ

 ስለሚችሉ ከዛም በኋላበእንግዴ ልጁም ሆነ በሌላ ምክንያት ሊሆን ስለሚችል የጤና ተቋም መሄድና /ርዎትን ማናገር ያስፈልጋል፡፡ ምክንያቱም ብዙ የደም መፍሰስ

 ካጋጠመ ደም መውሰድ ሊያስፈልግ ይችላል፡፡ከዚህም ጋር በተያያዘ የህፃኑንና የእርግዝናውን ሁኔታ መከታተል ጠቃሚ ስለሆነ ነው፡፡

  ከእነዚህ ህክምናዎች በኋላ መድማት ካላቆመ ደግሞ በጥንቃቄ ጤናማ የሆነ የማዋለድ አገልግሎት ለማግኘትም ወደ ጤና ተቋም መሄድ አስፈላጊ ነው፡፡

 

በእርግዝና ጊዜ ሊታዩ የሚችሉ አደገኛ ምልክቶች

1. ከፍተኛ የሆነ ትኩሳት እና የሆድ ቁርጠት ከእምብርት በታች

2. ከፍተኛ የሆነ የራስ ምታት እና የአይን ብዥታ

3. የእጅና የፊት እብጠት

4. በማህጸን ደም መፍሰስ

5. የጽንስ እንቅስቃሴ መቀነስ ወይም መቆም

6. የሽርት ውሀ ከምጥ በፊት መፍሰስ

*እንዚህ ምልክቶች በማንኛውም ጊዜ ከታዩ በአፋጣኝ ወደ ጤና ተቋም መሄድ ያስፈልጋል

 

 

 

 

 

 

EMSA Digital Library

online platform where you can find resources

Fellowship Opportunities

International Opportunities For Young Leaders

ከአእምሮ ጤና ጋር በተያያዘ ድንገተኛ እርዳታ ካስፈለግዎ

በነዚህ ቁጥሮች እርዳታ ያግኙ

Subscribe